>

ጎታች"ተብለው የተገመገሙት የአ/ክ/ፕሬዝዳንት ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል ገቡ...!!!" (አሚኮ)

ጎታች”ተብለው የተገመገሙት የአ/ክ/ፕሬዝዳንት ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል ገቡ…!!!”

አሚኮ


*… የምስራቅ ጎጃም ዋና አስተዳዳሪ እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እንዳይታፈኑ አድርገሃል በሚል ከሃላፊነቱ ተባረረ…!!!

*…. አቶ ደመቀ መኮንን ዶክተር ይልቃልን ተክተው የባህርዳሩን አፋኝ ቡድን እየመሩ ነው…!!!

ዶክተር ይልቃል ራሳቸውን የሳቱት በሰሞኑ በህግ ማስከበር ዘመቻ “ጎታች” ተብለው በጓዶቻቸው በመገምገማቸው ነው።

ዶክተር ይልቃል “ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በምንጥርበት በዚህ ሰዓት ኘሬዝዳንቱ ወደ ሗላ ጎትተውናል፣ በእቅዳችን መሰረትም ፋኖን እንዳናፍንና እንዳንገድል አድርገውናል” በሚል የተገመገሙት በክልሉ የፀጥታ ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ እና በክልሉ ብልፅግና ሃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ ነው።

በዚህ የተቀናጀ ግምገማ ወቅት ነው ዶክተር ይልቃል ከፋለ ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል የገቡት። በምርመራም የስኳር መጠናቸው ጭምር ከፍ ማለቱ ተረጋግጧል።

ዶክተር ይልቃል በአሁኑ ሰዓት በህክምና ላይ ሲሆኑ፣ የክልሉን የፀጥታ ግብረ ሀይል የውሎ ሪፖርት ለማስገምገም ዶክተር ይልቃልን ተክተው፣ አቶ ደመቀ መኮንን ባህርዳር ገብተዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዋና አስተዳዳሪ እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እንዳይታፈኑ አድርገሃል በሚል ከሃላፊነቱ ተባረረ…!!!

አቶ አብርሃም አያሌው የምስራቅ ጎጃም ዋና አስተዳዳሪ ሲሆን፣ የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልም ነበር።

ነገር ግን በሰሞኑ ፋኖን የማሳደድ ዘመቻ፣ ሃላፊነትህን በሚገባ አልተወጣህም፣ እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ በቁጥጥር ስር እንዳይውሉም መረጃ አሳልፈህ ሰጥተሃል በማለት ከግንቦት 20/09/2014 ጀምሮ ከሃላፊነቱ ተባሯል።

የብልፅግና አመራሮች መጠጊያችሁ ህዝብ ነውና፣ ለአንድ ሰሞን ስልጣን መጠጊያ ጎጇችሁን አታፍርሱ የሚል ጥሪ እናቀርባለን።

Filed in: Amharic