>

ፋኖ አለወንጀሉ እንዲሳደድ ምክንያት የሆኑ  ገፊ እዉነታዎች...!!! ( ሸንቁጥ አየለ)

ፋኖ አለወንጀሉ እንዲሳደድ ምክንያት የሆኑ  ገፊ እዉነታዎች…!!!

 

ሸንቁጥ አየለ


 

ፋኖ ከኦህዴድ መከላከያ ሀይል ጋር ተሰልፎ ህዉሃትን በመዋጋት የአቢይን ስልጣን ያረጋገጠ ሀይል ሆኖ ሳለ ለምን በአቢይ አህመድ መንግስት እንደጠላት ተፈርጆ ይሳደዳል? ለዚህ  ገፊ እዉነታዎች አሉ፥-

1፡ የምእራባዉያን ጫና፥- 

ምእራባዉያን አቢይ የመንግስት ጦርነቱን እንዲያቆም ጫና ማሳረፍ ሲጀምሩ ፈሪዉ እና ብልጡ ኦህዴድ ማምለጫ ፈለገ፥፥ “የጦርነቱ ዋና አቀጣጣዮች የአማራ እክራሪዎች እና ኤርትራ ናቸዉ፥፥ እኛ ሰላም ነዉ የምንፈልገዉ ”  ሲልም ለምኣራባዉያን ሪፖርት አደረገ፥፥ ምእራባዉያንም  እንግዴዉ ከአርትራም ተነጠል አክራሪዉ ፋኖንም ምታ ሲሉ ግፊት እደረጉ፥፥

2፡ የኦህዴድ የስልጣን ጥም፥- 

ኦህዴድ ፋኖ የታጠቀ ሀይል ነዉና አንድ ቀን የስልጣኔ ተቀናቃኝ ይሆናል ሲል ኦፌኮን፥ ኦነግን እና እክራሪ የአልቃይዳ አይሲስ መሰረት ያላቸዉን ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ በኦሮሚያ ሰብስቦ ፋኖን ለመምታት አግዙኝ ሲል ጥያቄ እቀረበ፥፥ እነሱም ተስማሙ፥፥ እክራሪዎቹ በሀይማኖት ስም የእማራ ክልልን ሲያተራምሱት መራራ ጉዲና ደግሞ ፋኖን ደምሡ ፋኖ ወንጀለኛ ነዉ የሚል መግለጫ በተከታታይ አወጣ፥፥

– ለፋኖ ድምጽ ይሆናሉ የተባሉ ጋዜጠኞች እና ምሁራን ቀድመዉ ተለይተዉ እንዲታሰሩ ሆነ

3፡- የአማራን ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ዘሩን የማጥፋት የተወሳሰበ እቅድ፥- 

የኦህዴድም ሆነ የኦነግ የመጨረሻ ግብ አማራ የሚባለዉን ዘር ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ነዉ፥፥ ለዚህ ደግሞ አንድም የታጠቀ የእማራ ሀይል መኖር የለበትም፥፥ አማራ ተግሎ  እና ተፈናቅሎ አይበቃዉ፡፥፥ ስጋዉ የተበላ ደሙ የተጠጣ ነገድ ነዉ፥፥

4፡የምቀኝነነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ፥

ኢዜማን የመሳሰሉ በኢትዮጵያዊነት ማልያ የሚጫወቱ ሀይሎች ከዛሬ አራት እመት ጀምሮ ፋኖ መመታት አለበት እያሉ ብዙ ቀስቅሰዋል::በነዚህ ምቀኞች ስሌት መሰረት አማራ ወደ ስልጣን እንዳይመጣ ሁሉም ክፋቶች መሰራት አለባቸዉ፥፥

5፥ የምቀኝነት ፖለቲካ በአማራ ወንዘኞች መሃከል ፥- 

የአምራ ወንዘኞች ጎንደር ጎጃም የፖለቲካ ቅርቃር ዉስጥ ገብተዉ አንዴ እንዱ ለጠላት የበለጠ ሲያጎበድድ ሌላ ጊዜ ሌላዉ ሌላዉን ለማስንቅ ሲሰራ የጎጃ፡ ጎንደር ፖለቲካ እስከ ወሎ ሸዋ የሰፈር ክፍፍል ዘልቆ ብዙ የጠላት መሳሪያ የመሆን ስነልቦና ተንሰራፍቷል

6፥ ፋኖዎች የተከተሉት የተደበላለቀ አካሂያድ፥- 

ፋኖ ወጥ ሆኖ ሀገራዊ ሆኖ ከመደራጀት ይልቅ በወንዝ ከመታጠሩም በላይ ቀሪዉ ፋኖም እራሱን እንደ መንግስት አጋር የሚመለከት ነዉ፥፥ በዚህም ህዉሃትን ብቻ እንደጠላት የወሰደዉ ፋኖ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነዉ፥፥ ዋናዉን ጠላት ኦህዴድን ተሸክሞ እየሮጠ ዋና ጠላቴ ህዉሃት ነዉ የሚለዉ ብዙ ነዉ፥፥ ይሄኛዉ ፋኖ ኢትዮጵያን የመረከብ፥ የመምራት አላማ ፈጽሞ የለዉም፥፥ ኢትዮጵያን የመረከብ እና የማዳን አላማ ያነገቡት ፋኖዎች በቁጥር ትንሽ ናቸዉ፥፥ በእጠቃላይ የፋኖዎች መስመር የተለያዬ ነዉ፥፥ ሆኖም ኦህዴድ የሚያሳድዳቸዉ እና እየገደላቸዉ ያለዉ ሁሉንም ፋኖዎች ነዉ፥፥ማንም እማራ ከሆነ ጠላት ነዉ በሚለዉ የኦህዴድ/ኦነግ መርህ መሰረት መሆኑ ነዉ፥፥

7፥ በአንድ ሌሊት ጨረቃ ሰባት ጊዜ ምሎ ሰባት ጊዜ የመክዳት ክህሎት ያለዉ ኦህዴድ ከህዉሃት ጋር የጀመረዉ አዲስ ፍቅር፥-

ኦህዴድ ከብአዴ  ጋር ሆኖ ህዉሃትን እንደቀጠቀጣ ሁሉ አሁን ደግሞ የህዉሃት ወዳጅ ሆኖ ብእዴንን አጣብቆ ማጥፋት ስለፈለገ ህዉሃትን ደስ እንዲላት ህዉሃት አምርራ የምትጠላዉን ፋኖን በማጥፋት ህዉሃትን ለማስደሰት ቆርጧል፥፥

8፥ የብአዴን ንዝህላልነት፥-

ለኦህዴድ የጥፋት እቅዶች ሁሉ የብአዴን ባንዳ ስነልቦናና  ንዝህላልነት ቁልፍ ሚና ተጫዉቷል

9፥ ወልቃይት ወደ ትግራይ ፥-

በተራ ቁጥር 1 እንደተብራራዉ ምእራባዉያን ጦርነቱ መቆም አለበት ሲሉ ወስነዋል፥፥ የጦርነቱ መነሻ የህዉሃትና የኦህዴድ የስልጣን ሽኩቻ ቢሆንም ለምእራቦች ኦህዴድ የነገራቸዉ ምክንያት ግን ሌላ ነዉ፥፥ ይሄም ወልቃይት የጦርነቱ መነሻ ነዉ፥፥ ስለዚህ በምእራባዉያን ስሌት ወልቃይት ወደ ትግራይ ቢከለል ጦርነቱ ይቆማል ብለዉ እስበዋል፥፥ ሆኖ ይሄን ዉሳኔ የሚቃወመው የታጠቀዉ ፋኖ ስለሆነ መጀመሪያ ፋኖን ለመምታት ስምምነት ላይ ተደርሷል፥፥

ለዚህም አማራ ፖለቲከኞች መሃከል ያለዉን የወንዘኝነት ስነልቦና በመጠቀም መጀመሪያ ጎጃምን መምታት የሚል ስትራቴጅ ተነድፏል፥፥ከዚህ በተጨማሪም ወልቃይት የሚገኘዉን የአማራ ልዩ ሀይል እና ፋኖን ለስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ በሚል ሽፋ  አግባብቶ የማስለቀቅ እና ቦታዎን በኦህዴድ መከላከያ የማሲያዝ ቅድመ ስራ ተሰርቷል፥፥

በጎጃም ወሎ እና ሸዋ ያለዉ ፋኖ ከተመታ በማንኛዉ፡ ጊዜ ወልቃይትን ወደ ህዉሃት ጉያ መወርወር ይቻላል፥፥ ይሄን የሚቃወም ሀይል ከጎንደር ከተነሳ ብቻዉን መቀጥቀጥ ይቻላል የሚል ስትራቴጅ ተነድፏል፥፥ ጎንደር ላይ የሚገኙ እና የጎጃም ወሎና ሸዋ ፋኖዎችን መመታት የሚቃወሙትን ፋኖዎችን ከወዲሁ ለይቶ የመምታት ስራ እየተሰራ ነዉ

10፥ ሸዋ አዲስ አበባ፥-

ከአስራ እምስት ሚሊዮን በላይ ነዋሪ እንዳላት የሚገመተዉ አዲስ አበባ የኦህዴድ/ኦነግ ሌላዉ ቅዠት ነች፥፥ እዲስ አበባ ላይ የሚነሳ አመጽ የኦህዴድን እስትንፋስ ጸጥ እንደሚያደርገዉ ሁሉም ያዉቃል፥፥ ይሄን እዉነታ ይበልጥ እስፈሪ የሚያደርገዉ ታዲያ የታጠቀ ፋኖ በመላ ሀገሪቱ ከኖረ ነዉ፥፥ ስለሆነም በየቀኑ በእዲስ አበባ ጉዳይ ሲቃዥ የሚያድረዉ ኦህዴድ ለእዲስ እበባ የጀርባ አጥንት የሚሆናት ፋኖ እንዳይኖር ወስኗል::

——–

ፍጻሜው ምን ሊሆን  ይችላል?

ኦህዴድ እንደተመኘዉ ፋኖን ማክሰም ይችላል? ወይስ ከዚህ ሂደት ኢትዮጵያን የሚያድን የነጻነት ሰራዊት ይወለዳል?

እመለስበታለሁ

Filed in: Amharic