>

"ቤት ንብረታችንን አውድመው የ85 ዓመት እናታችን ላይ ከፍተኛ እንግልትና ዝርፊያ አካሂደዋል...!!!"  (የዘመነ ካሴ ወንድም ፋኖ ንብረት ካሴ)

 

“ቤት ንብረታችንን አውድመው የ85 ዓመት እናታችን ላይ ከፍተኛ እንግልትና ዝርፊያ አካሂደዋል…!!!” 

 

የዘመነ ካሴ ወንድም ፋኖ ንብረት ካሴ


የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ የሆነውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለማጥቃት ከሰሞኑ ወደ ምዕራብ ጎጃም፤ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፤ መርዓዊና በአካባቢ ባሉ ጫካዎች የተሰማራው የአገዛዙ ሰራዊት በዘመነ ካሴ ቤተሰቦች ብሎም በመርዓዊ ንፁሃን ኗሪዎች ላይ በርካታ ግፎችን እንደተፈፀመ ተዘገበ።

የአርበኛ ዘመነ ወንድም ፋኖ ንብረቱ ካሴ ለኢትዮ 360 ሚዲያ እንዳረጋገጠው፣ በዚሁ ጥቃት ከሕዝብ ወገን 4 ሰዎች በጥይት ተመተዋል። ከእነዚህ መካከል 3ቱ ተሰውተዋል፤ አንዱ በከፍተኛ ደረጃ ቆስሎ በሕክምና ላይ  ናቸዉ። ወታደሮቹ ስናይፐር፣ ብሬን እና መትረየስ የታጠቁ ናቸው።

“የዘመነ ካሴ የ85 ዓመት እናት ቤት በከባድ መሳሪያ ተደብድቦ፣ ከመቀነቷ የቋጠሩትን የማዳበሪያ መግዣ ስድስት ሺህ ወስደውባቸዋል” ብሏል ፋኖ ንብረቱ።

የአካቢቢው ኗሪ በየቤቱ ፋኖዎችን አሳልፎ ላለመስጠት አፋኙን ቡድን ተዋግቷል። በተለይም ከአጎራባቹ ይልማና ዴንሳ ወረዳ በፍጥነት የደረሱ ፋኖዎችና ሌሎች ኗሪዎች በርካቶች እንዲነሱ ምክንያት ሆነዋል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic