>

የፋኖ ም/ሻለቃ አዛዥ ሹመት አምባቸውን ጨምሮ ሁለት ሰላማዊ ነዋሪዎች በጎንደር ዙሪያ ተገደሉ!!

የፋኖ ም/ሻለቃ አዛዥ ሹመት አምባቸውን ጨምሮ ሁለት ሰላማዊ ነዋሪዎች በጎንደር ዙሪያ ተገደሉ!!

ባልደራስ

ፋኖ ም/ሻለቃ አዛዥ ሹመት አምባቸውን ጨምሮ ሁለት ሰላማዊ ነዋሪዎች በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማ ተገደሉ።

ትጥቅ ለማስፈታት ያረፉበትን ቤት የከበበው የመንግስት ጦር በአር ቢጂ ፣በቦምብና በሞታራይዝድ ተተኳሽ አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች ጭምር በመደገፍ፣ ከፍተኛ ድብደባ በማድረግ፣ ቤቱ በእሳት እንዲጋይ እና ፋኖ

ም/ሻለቃ ሹመት አምባቸውን ጨምሮ መሳፍንት ጥላሁን እና በየነ ማንደፍሮ የተባሉ ሁለት ሰላማዊ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በእሳት ተለብልበው ተገድለዋል።

ፋኖ ሹመት አምባቸው በህልውና ጦርነቱ ግዳጁን ተወጥቶ የተመለሰ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አባል እና የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የፊትአውራሪ ሽፈራው ማመጫ ም/ሻለቃ አዛዥ በመሆን ጠንካራ ትግል እያደረገ የነበረ ጓድ ነው።

ምንጭ:-  የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር!

Filed in: Amharic