>

በአምስት ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶች ጉዳይ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ...!!!" (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በአምስት ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶች ጉዳይ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ…!!!”

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአምስት ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶችን ጉዳይ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ለነገ ማክሰኞ ግንቦት 30፤ 2014 ቀጠሮ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተመስገን ደሳለኝ፣ ያየሰው ሽመልስ፣ መዓዛ መሐመድ፣ መስከረም አበራ እና ሰለሞን ሹምዬ ናቸው።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮውን ከመስጠቱ በፊት መርማሪ ፖሊስ በተፈቀደለት የምርመራ ጊዜ አከናውኛችኋለሁ ያላቸውን ዝርዝር ተግባራት አቅርቧል። በፖሊስ ማብራሪያ ላይ በመንተራስ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎቹን የወከሉ ጠበቆች ያቀረቡትን መከራከሪያዎች እና የዋስትና ጥያቄዎችንም ፍርድ ቤቱ አድምጧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አምስቱንም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች “ሁከት እና ብጥብጥብ በማነሳሳት ወንጀል” እንደጠረጠራቸው ከዚህ ቀደም በነበራቸው የፍርድ ቤት ውሎ ቢገልጽም፤ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ ዛሬ ችሎት ፊት የቀረበው ግን በተለያየ መዝገብ ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7071/

Filed in: Amharic