>

“ሰሞኑን በጎንደር ማክሰኝት ላይ የተወሰደው የከባድ መሳሪያ እርምጃ መንግስታዊ ሽብር ነው...!!! (ሻለቃ ሰፈር መለስ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰብሳቢ

“ሰሞኑን በጎንደር ማክሰኝት ላይ የተወሰደው የከባድ መሳሪያ እርምጃ መንግስታዊ ሽብር ነው…!!!

   ሻለቃ ሰፈር መለስ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰብሳቢ


“ሰሞኑን በጎንደር ማክሰኝት ከተማ በመንግስት ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ የተወሰደው የከባድ መሳሪያ እርምጃ ለእኔ መንግስታዊ ሽብር ነው” ሲሉ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰብሳቢ ሻለቃ ሰፈር መለስ በስልክ ባደረጉት ቃለምልልስ ተናገሩ።

“በተለያዮ ግንባሮች ከመንግስት ጋር አብረን ወራሪን ስንመክት ቆይተናል።በቀጣይም፣ በአማራ ክልልም ይሁን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገጥሙንን ማናቸውም የፀጥታና የሰላም ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ በሰላም እየመከርን በነበረበት ወቅት ይህ መፈፀሙ ክህደት ነው” ብለዋል።

አያይዘውም፣ “አሁን ላይ ህግ በማስከበር ሽፋን በፋኖዎች፣በአክቲቪስቶች፣በጋዜጠኞች እና በፖለቲካ ደርጅት ኃላፊዎች እና አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው ጅምላ እስር፣እገታና የንፁሃን ግድያ አሳዝኖናል።በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል” ብለዋል።

“ከሰሞኑን በድርድር ስም የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን እየሰማን ነው። እንቅፋት ሊሆን ይችላል ተብሎ የታሰበውን ፋኖን አስቀድሞ ለማሸማቀቅ እና ለማዳከም የተሸረበ ሴራ መሆኑን ተረድተናል፣ ግን አይሳካም”ብለዋል።

“የአማራ አፅመ ርስት የሆኑትን ወልቃይትና ራያን  ከዚህ በኋላ ለህወሓት መስጠት የመጨረሻውን ቀይ መስመር መርገጥ ነው” ብለዋል ሻለቃ ሰፈር መለስ።

Filed in: Amharic