>

ከአሶሳ ወደ አዲሲስ አበባ ሲጓዙ ከነበሩት አማሮች ተለይተው በኦነግ ሸኔ ታገቱ...!!! (ባልደራስ)

ከአሶሳ ወደ አዲሲስ አበባ ሲጓዙ ከነበሩት አማሮች ተለይተው በኦነግ ሸኔ ታገቱ…!!!

ባልደራስ

“… በመታወቂያቸው ከተለዩ በኋላ ስድስት  አማሮች አድራሻቸው ጠፍቷል…!!!

ከቤንሻንጉል ጉምዝ፤ አሶሳ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ መለስተኛ አውቶብስ ውስጥ መታወቂያቸው እየተነበበ ከተለዩ በኋላ ስድስት  አማሮች ተመርጠው በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ታግተዋል። የታገቱት ሜጃ የተባለ ቦታ ላይ ሲደርሱ እንደሆነም የታጋች ቤተሰቦች አረጋግጠዋል። ከታገቱት መካከል 4ቱ ወንዶች ሲሆኑ ሁለቱ ሴቶች ናቸው።

ከአራቱ ወንዶች መካከል ሁለቱን ከመኪና ሲያስወርዷቸው ልብሳቸውን አስወልቀው እንደነበረ የገለፁት የዓይን እማኞች፣  ወደ ጫካው በአስገቧቸው ቅፅበት ሁለት ጊዜ የጥይት ድምፅ መሰማታቸውን ተናግረዋል።

መኪናው ውስጥ የነበሩ ሌሎች 12 ተሳፋሪዎች መታወቂያቸው ተነቦ አማራዎች አለመሆናቸው ስለተረጋገጠ ሰላማዊ ጉዟቸውን ቀጥለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ሰዎችን ከማገቱ በፊት በእጃቸው ያገኘውን ገንዘብ ሁሉ ነጥቋቸዋል። ቡድኑ በአካባቢው ባሉ አንዳንድ የአገዛዙ ባለሥልጣናት ይደገፋል።

/

Filed in: Amharic