>

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ታዘዘ ...!

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ታዘዘ …!

አሳዬ ድርብ

 የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2014 በዋለው ችሎት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ አዟል።

በትላንትናው ዕለት በዋለው ችሎት ላይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራ መጨረሱን ገልፆ መዝገቡን ለክልሉ አቃቤ ህግ ሊልክ መሆኑን አስታውቆ የነበረ ሲሆን፤ የክልሉ አቃቤ ህግም ምርመራው በማለቁ የክስ መመስረቻ የ15 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።

የተከሳሽ ጠበቃም ምርመራው ካለቀ ዋስትና የሚያስከለክል ክስ ባለመኖሩ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎትም የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ተሰይሟል።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ዋስትና የሚከለክል ሆኖ ስላላገኘው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ አዟል ሲል የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታዉቋል።

Filed in: Amharic