4 የፖሊስ አባላት “ስንታየሁን ትደግፋላችሁ” በሚል ከሥራ ታገዱ!!
ጌጥዬ ያለው
ፖሊሰእ ስንታየሁ ቸኮልን ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ቀረ!!
4 የፖሊስ አባላት “ስንታየሁን ትደግፋላችሁ” በሚል ከሥራ ታገዱ!!
ከአለፈው ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በባሕር ዳር በግፍ እስር ላይ የሚገኘው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል እስከ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ አለማወቁን ጠቅሶ፣ ጠበቃው አካሉ ነፃ እንዲወጣና ከእስር እንዲፈታ ጠይቋል።
ጠበቃው ትናንት ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ለባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው ጥያቄ፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር ፖሊስ መምሪያ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ችሎት እንዲጠራና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታሰረውን ስንታየሁን በነፃ እንዲለቅ ፍርድ ቤቱ እንዲያዝዝ ጠይቋል።
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ለቀረበበት አካልን ነፃ የማውጣት ክስ ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ፤ ሳይቀርብ ቢቀር ግነ ጉዳዩን በሌለበት እንደሚዳኘው ጠቅሶ የመጥሪያ ደብዳቤ ልኳል።
ሆኖም፣ ፖሊስ መጥሪያው ትናንት አልቀበል ካለ በኋላ ዛሬ ችሎት ሳይገኝ፤ ስንታየሁንም ሳያቀርብ ቀርቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የባሕር ዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አባላቱነእ ሰብስቦ ገምግሟል። ከስብሰባው ቦኃላም፣ “አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ትደግፋላችሁ” በሚል ማሸማቀቂያ አራት የፖሊስ አባላትን ከሥራ አግዷል።