>

መነበብም መደመጥም ያለበት መንግሥት መራሹ ጭፍጨፋ!

ይሄን እንኩ…!!

ዘመድኩን በቀለ /የኔታ ቲዩብ

“…የዘር ጭፍጨፋው መዋቅራዊ ነው። በትእዛዝ ነው፣ መመሪያው ከአራት ኪሎ የሚመጣ ነው የምንለው እኮ ወደን አይደለም። ወደ ምዕራብ ወለጋ ያቀናው የሃገር መከላከያ ሠራዊት በዚያ ባየው የኢትዮጵያውያን ዐማሮች የሬሳ ክምር ደንግጧል። የሚያለቅሱ፣ የሚያደርጉትን ያሳጣቸው የመከላከያ አባላትም ነበሩ ተብሏል። አራስ ህጻናት በኦሮሞዎቹ የወለጋ ፕሮቴስታንቶች ተጨፍጨፈው ያዩ ሁሉ ታመዋል።

“…የሃገር መከላከያው ይሄ ሁሉ ሲፈጸም ምን ስትሠሩ ነበር በማለት የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ እና የቀበሌዋ ሚሊሻ  ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳኔ ወርዋን በቁጥጥር ስር አውሎ ቆይቶ በአራተኛ ቀናቸው ዛሬ በቶሌ ቀበሌ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ እውነታውን ከሞት የተረፉት ዐማሮች ፊት በመቅረብ እንዳናዘዟቸው ተሰምቷል።

“…የቀበሌዋ አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ  ኑዛዜያቸውን እንዲህ በማለት ነበር የጀመሩት። ” የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ  አቶ ባጫ እና የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ በስልክ ደውለው ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም አሉኝ፡፡ ሰራዊታችን ( ኦነግ ሸኔን ማለታቸው ነው) ቅዳሜ የሚያካሂደው ኦፕሬሽን አለ። እናም አስፈላጊውን ትብብር እንድታደር ብለው አዘዙኝ ብሏል አቶ ንጋቱ፡፡

“…አቶ ንጋቱ እንደሚሉት አቶ ባጫ እና የጸጥታ ኃይሉ ሓላፊ፤ ሰራዊቱ ቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ማታ እንደሚገባ፤ እኔ፤ አቶ ኪዳነ መርዋ እና ሳጂን አሰፋ የፖሊስ አባላቱን እና የሚሊሻ አባላቱን ከቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ዕለት እንድናስወጣቸው አዘዙን፣ ሰራዊቱ ወደ ቶሌ ቀበሌ ሲገባም ሰንጋ እንዲታረድለትም ስለታዘዝን የታዘዝነውንም ፈጽመናል ብለዋል፡፡

…የጸጥታ ኃይሉን ጨምሮ የቶሌ ቀበሌ ዋና ዋና አመራሮች ሐሙስ ዕለት ቀበሌዋን ለቀው እንዳደሩ የተናገሩት አቶ ንጋቱ ከቀበሌዋ በቅርብ ርቀት ሂደው ማደራቸውንም ገልጠዋል፡፡ ሰራዊቱ ሐሙስ ማታ ከገባ በኋላ በቀበሌዋ የተጣለለት ሰንጋ እየተመገበ ሲጨፍር እንዳደረም ተናግረዋል፡፡

“…አርብ ዕለት ቀበሌዋ ምንም አይነት የመንግሥት መዋቅር የሌለባት ቀበሌ ሆነች የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ቀኑን ሙሉ የቶሌ ቀበሌ ሰፊ በመሆኑ እኛም ራሳችንን ቀይረን ከቀበሌው  አንድም ሰው እንዳይወጣ  ከሰራዊቱ ጋር ከበባ አደረግን ይላሉ፡፡ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና ሰላም እና ጸጥታ ሃላፊው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይከታተሉ ነበር የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ዕለት ደውለውልኝ ቅዳሜ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጭፍጨፋው እንደሚጀመር እና ስምንት ሰዓት ውስጥ እንደሚያልቅ ትዕዛዝ አስተላልፈውልኛል ብለዋል፡፡

“…የወረዳ አመራሮቹ ሲደውሉልኝ ሌሎች አመራሮችም ከጎኔ ነበሩ እንደ እኔ ራሳቸውን ቀይረው ከሰራዊቱ ጋር ተሰልፈዋል ብለዋል፡፡ አቶ ባጫ ቅዳሜ ጠዋት ሁለት ሰዓት ይጀመራል ባሉት መሰረት ጭፍጨፋውን እና ዝርፊያውን ጀመርን እስከ ስምንት ሰዓትም ቆየን ብለዋል አቶ ንጋቱ።

“…ጥቂት ዐማራዎች በአልሞትባይ ተጋዳይነት መከላከል ሲያደርጉ የሰራዊታችን አባላት ሲመቱ ከወረዳ አምቡላንስ ተልኮልን፤ የሰራዊታችንን ቁስለኞች ወደ ጊምቢ ሆስፒታል ስታመላልስ የዋለች አምቡላንስም ነበረች ያሉት አቶ ንጋቱ ኡመታ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ሲሆን “በቃችሁ” የመከላከያ ሰራዊት ወደ ጊምቢ እየመጣ ስለሆነ አምልጡ የሚል ትዕዛዝ ተላልፎልን ተመልሰን ከሰራዊታችን ጋር ወደ ጫካ ሄድን። ከዚያም እኔ እና ባልደረቦቼ መሳሪያችንን እና ልብሳችንን ቀይረን ወደ ቶሌ ቀበሌ ሰላማዊ ሰው መስለን…

ከዚያም እኔ እና ባልደረቦቼ መሳሪያችንን እና ልብሳችንን ቀይረን ወደ ቶሌ ቀበሌ ሰላማዊ መስለን መጣን ሲሉ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝብ በተሰበሰበበት ተናዘዋል፡፡ የቶሌ ቀበሌ የሚሊሻ ጽ/ቡት ሃላፊ አቶ ኪዳነ መርዋም በተመሳሳይ የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ የሰጡትን መረጃ ተናግረዋል፡፡ ከጭፍጨፋው የተረፉት የዐማራ ተወላጆችም ይህንን ከሰሙ በኋላ በከፍተኛ ዋይታ እና ጩኸት ውስጥ እንደነበሩ የአካባቢው የአይን እማኞች መናገራቸውም ተዘግቧል።

“…አሁን ላይ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና  የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በአካባቢው መኖሩን የገለጡት ነዋሪው ገዳዮቹን መከላከያ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እየተቃወሙ ነው ብለዋል፡፡ ‘’ጨፍጫፊዎች ሲያዙ ፤ ልዩ ኃይሎቹ ያለቅሳሉ ይቆረቁራሉ የሚያዝኑት ለእነሱ ነው ለእኛ አይደለም ‘’ ሲሉ ገልጸውታል። መከላከያው ከልዩ ሃይሉም ጋር ተፋጧል የሚሉት የአይን እማኙ ጫካ የገባውም ሆነ ያልገባው አንድ ናቸው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

“… አሁን ከጭፍጨፋ የተረፈው ሜዳ ላይ ነው ያለው። የሚልሰው የሚቀምሰው የለም የሚሉት ነዋሪው ለመሳፈሪያ ገንዘብ ያለው ዐማራ በመኪና እንኳን ተሳፍሮ እንዳይሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ሹፌሮቹ ሁሉ አኩርፈዋል አድመውብናል ብለዋል። ከቶሌ ቀበሌ ሸሽተው በአጎራባች ግንቢ አቅራቢያ የተፈናቀሉ 3ሺ የሚደርሱ ዐማራዎች ባለቻቸው ብር እንኳን ምግብ ገዝተው እንዳይመገቡ ብራቸውን ከፍለው እንኳን የሚሸጥላቸው ነጋዴ አላገኙም ስቃይ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡”…ዐማራ እዚህ መኖር የለበትም መልሰን ስንመጣ እንዳናገኛችሁ ተብለናል የሚሉት የአካባቢው ነዋሪ የተረፍነውን አዲስ አበባ ድረስ እንኳን የሚወስደን እና እሩሃችንን የሚታደገን ወገን ይድረስልን፤ ድምጻችንን አሰሙልን ሲሉ ተማጽነዋል

“…ዛሬም ድረስ አስከሬን እየተቀበረ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪው፤ እኔ ራሴ እንኳን የ20 ቀን ህጻናትን ጨምሮ 19 ህጻናት ከተቃጠሉበት እና ታርደው ከተጣሉበት፤ በጥይት ተመተው ከወደቁበት አንስቼ 20 ህጻናትን ጉድጓድ ቆፍሬ አንድ ላይ ቀብሬያለሁ ብለዋል፡፡ በቶሌ ጉትን ቀበሌ ብቻ ከአስር ሺ የማያንስ ጠቅላላ ብሬል እና መትረየስ የታጠቀ ሰራዊት ነው የጨፈጨፈን ብለዋል ነዋሪው። ለዚህ ነው ዐብይ አህመድ በኦሮሚያም በየትም ለሚደርስ የዘር ጭፍጨፋ አጣሪ ይግባ ሲባል እምቢዮ የሚለው።

https://youtu.be/343y2WwjOzA

“…አዲስ አበባ ሰምተሻል…!!

Filed in: Amharic