>

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትልቅ የተቃውሞ ትእይንተ ህዝብ ተካሄደ...!!! (አለማየሁ ማ ወርቅ)

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትልቅ የተቃውሞ ትእይንተ ህዝብ ተካሄደ…!!!

አለማየሁ ማ ወርቅ


*… ወያኔ ባሳደገው ጨቅላ ነው የዘር ማጥፋት እየተካሄደብን ያለው…!!!

*…. ይህ ስርአት ጸረ አማራ ነው በቃን!

*… አብይ አህመድ በፓርላማ “የአማራ ፋኖ የቆሰለ መከላከያን ገድሎ ጥቁር ክላሽ ታጠቀ!” ብሎ የዘር ፍጅት ባወጀብን ማግስት ነው ወገኖቻችን የታረዱት፤ ነፍሰጡሯ ሆዷ ተዘርግፎ ልጇ የተጣለው፤ ህጻን አዛውንቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የተጨፈጨፉት፤ እናም ጥቃቱ የዘር ማጥፋቱ መዋቅራዊ ነው ከስሜት ወጥተን በስሌት ትግሉን መቀላቀል አለብ።

ዛሬ የኛ መማር ማስተርስና ኢንጅነሪንግ እህታችንን  እናታችንን ከጅምላ ጭፍጨፋ ካላዳናት ምን ዋጋ አለው? ነገ እኮ ይመጡልናል በየተራ ይፈጁናል ተቀምጠን ልንጠብቃቸው አይገባም፤

ትግሉን እንቀላቀል እነ ዘመነ ካሴን ምሬ ወዳጆን ሌሎችንም እናግዝ ፋኖዎች ተያዙ ተገደሉ ሳይሆ እኔም ፋኖ ነኝ እንበል ፤ እነርሱ እኮ መተኪያ የሌላትን ህይወት እየገበሩልን ነው እስኪ እኛ ደረቅ ብስኩት እንኳ እናቀብላቸው… እና የመሳሰሉት ሀሳቦች ተንሸራሽረዋል።

ሌላው የግቢው ተማሪ ወጣት ወያኔ ባሳደገው ጨቅላ ነው የዘር ማጥፋት እየተካሄደብን ያለው በመሆኑም  ይህን የዘር ፍጅት የምናስቆመው በትግላችንና በትግላችን ብቻ መሆኑን አውቀን እኔ ትግሉን በምን ላግዝ እንበል ፤ እኛ እኮ በሺዎች ተገለውብን ታርደውብን በፓርላማ  የሁለት ደቂቃ የህሊና ጸሎት የተከለከልን ነን፤ ባንዲራ ዝቅ ማለትማ ቅንጦት ነው፤  ለዜና ፍጆታ እንኳ የማንበቃ ሆነናል ይህንን እንደሰው አለመቆጠር ፤ ይህንን ውርደት ልንቀለብሰው የሚገባው በትግላችን ብቻ ነው፤ ሌላው ከጎንህ ያለው ወንድምህ ላይ እጅህን በማንሳት ወይም ንብረት በማውደም የሚመጣ ውድቀት እንጂ ድል ስለሌለ ትግሉን እናግዝ እንቀላቀል አመሰግናለሁ።

ሌላው ተማሪ በበኩሉ ሲሻቸው ገዳይ ሲሻቸው አሳሪ ፖሊስ ሌላም ጊዜ ፈራጅ ዳኛ በመሆን ማልያቸውን እየቀያየሩ የሚገድሉን የሚያስገድሉን መንግስት ብለን በፌደራል በተለይም በክልል ሌላ ጋር አንሄድም የእኛዎቹ ጉዶች ናቸውና ትግሉን ከዚሁ ነው መጀመር ያለብን ፤

የሚሉ በርካታ ሀሳቦች ተንሸራሽረው የጋራ የትግል ስትራቴጂ ለመንደፍ እቅድ ተይዞ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ሰልፉ ተጠናቋል።

https://fb.watch/dRfZVTEtdJ/

Filed in: Amharic