>

ከዐማራ ጋር ጦርነት የገጠሙ ኃይሎች ስም ዝርዝር እነሆ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

ከዐማራ ጋር ጦርነት የገጠሙ ኃይሎች ስም ዝርዝር እነሆ!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ


የዛሬውን ጽሑፌን ማን እንደሚያስተናግድልኝ ከወዲሁ ሳስበው ይጨንቀኛል፡፡ ባህላችን ባብዛኛው የመሸፋፈንና እውነትን የመደበቅ በመሆኑ ትንሽ ገለጥ ያለ ነገር ሲገጥመን በ“ከነገሩ ጦም እደሩ” ብሂላችን እየተጋረድን ብዙዎቻችን ከእውነቱ እንርቃለን፡፡ እውነት ግን ምን ጊዜም እውነት ናትና የትም አትሄድም፤ እኛ ብንሸሻትም እርሷ ግን እኛኑ ትከተለናለች፤ ከኛው ጋርም ትኖራለች፡፡ ይህ ሁሉ ዳር ዳርታ አንዲት አይነኬ ጉዳይ ልናገር ስላቆበቆብኩ ነው – ወረድ ሲል ታገኟታላችሁ፡፡ 

እንደውነቱ ዐማራ ያልታደለ ሕዝብ ነው፡፡ ምናልባት እርግማን ይኖርበት ይሆናል፡፡ እርግማን ደግሞ ጊዜውን ጠብቆ ቢነሳም እስከዚያው ግን አሣርን ያበላል፤ እያየነው ስለሆነ ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልገንም፡፡ እኔ ሳውቅ እንኳን ላለፉት 40 ዓመታት ገደማ ዐማራ በገጠርም በከተማም ፍዳውን ሲቆጥር እንጂ አንድም ጊዜ እፎይ ሲል አላስተዋልኩም – በአንጻራዊነት አንዱ አገዛዝ ከሌላው ሻል ሊል ቢችል እምብዝም አትታዘቡኝ፡፡ ይሄ መከራና ስቃዩ ደግሞ ለዐማራ የሚሞቀው የሚበርደው አይመስልም፡፡ በጣሙን ተለማምዶታል፡፡ እንደበግ መታረዱንም፣ እንደፍልስጥኤም መሳደዱንም፣  በሀሰት ትርክት የተነሣ እንደ አይሁዳውያን መጠላቱንም … ተለማምዶት ደንዝዟል፡፡ “ለዚህ ሕዝብ ይህ ሁሉ ይገባዋል ወይ?” የሚለው ጥያቄ ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡ ዕውቀቱ ያላችሁ ፈትሹና ንገሩን፡፡

የዐማራ ጠላቶች በስም ይታወቃሉ፡፡ የተወሰኑትን አሁን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በክፋት ደረጃቸው ቅደም ተከተል ስለመጥቀሴ እጠራጠራለሁና ደረጃ ውስጥ አልገባም፡፡

  1. ኢሕዲን – ብአዴን – አዴፓ፡፡ ይህ ሳይወለድ የጨነገፈ ሕወሓት ሠራሽ የሆዳሞች ጥርቅም ላለፉት 40 ምናምን ዓመታት በዐማራ ስም በወያኔ ተሰፍሮና ተለክቶ ለዐማራ በተሰጠው ክልል ውሰጥ ዐማራን እንደሚወክል የክልል መንግሥት ተቆጥሮ በዐማራ ላይ ጢባጢቤ ሲጫወት ከረመ፤ አሁንም በዐማራ ስም የዐማራ አለኝታዎችን እያሳደደ በመግደልና በማሰር መላውን የዐማራ ሕዝብ ለተረኞች አስረክቦ ዐማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እየተጋ ይገኛል፤ የጭራቁ አቢይ ኦነግ-ሸኔ አማራን አርዶ እንዲጨርስ ከተፈለገ ለአማራ የሚቆረቆር አንድም ኃይል የትም ሥፍራ መኖር የለበትም፡፡ ስለዚህም ዐማራን የሚያርደው ሸኔ እየፋፋና እየለመለመ፣ አርፎ የተቀመጠው ፋኖ ግን መወገድ አለበት፡፡ ከዚህ መሪር እውነት በተጓዳኝ ያለው ሃቅ ደግሞ አንድ የብአዴን አባል ሆዱ አይጉደልበት እንጂ የዐማራ ማለቅ ሲያሳስበው አይታይም፡፡ እንደምገምተው የዚህ ቡድን አባላት የሰውነትን ቅርጽ ተላብሰው በሰው አምሳል የተፈጠሩ ዓሣሞችና ጅቦች ይመስሉኛል፡፡ በዚህን አሳሳቢ የኅልውና ወቅት እንኳን ከአራጆቹ ጋር ተባብረው ዐማራን እያሳደዱት ነው – የሚገርም ተፈጥሮ ነው፡፡ ለወደፊቱ ቢቻል በሕይወት ተይዘው አለበለዚያም ሬሣቸው/አፅማቸው ተለይቶ መመርመርና ሥነ ተፈጥሯቸው መታወቅ አለበት፡፡ ዓለም እስከዛሬ እንደነዚህ ያለ ጉግማንግ ፍጡር አይታ አታውቅም፡፡ ሁሉም በመጨረሻ ከነዘር ማንዘሩ ዋጋውን ማግኘቱ ባይቀርም አሁን ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ዐማራውን ከውስጥ ሆኖ እያስጠቃና የዐማራን የነጻነት ዐውደ ግንባር በአንድ ቁጥር ጨምሮ ሀገራችንን እያወደመ ያለው ብአዴን ነው፡፡ ይህ ድርጅት ከሁሉ አስቀድሞ መጥፋት ያለበት መሆኑን ላስምርበትና ወደሌላ የጠላት ጎራ ልለፍ፡፡
  2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን – ይህች ቤተ ክርስቲያናችን በመሠረቱ በብዙ ቁም ነገሮችና በሀገር ባለውታነት ትጠቀሳለች፡፡ እኔም ከዲቁና እስከ አርሶ ፈረስ አወዳሽነት አገልግያታለሁና ባውለታነቷን አልረሳም፡፡ አሁንም በርሷው ሥር ነኝ – አማራጭ በማጣት ጭምር፡፡ እንጂ የዚህች ተቋም በደል ተነገሮም ሆነ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ የሚታወቅን መናገር ኃጢኣትም ነውርም አይደለምና እባካችሁን ልደመጥ፡፡ ዝም ብሎ የሚያወግዝ – ሳይገባው የሚቃወም – ብልኅነቱን አልገለጠም፡፡ 

2.1 ከግብጽ እንደመጣ በሚነገር የበዓል አከባበር የወሩ 30 ቀናት ሁሉምና እንዲያውም በድራቦሽ የሚከበሩ በዓላትን በመደረት ሕዝቡ ሰነፍ እንዲሆን አድርጋለች፡፡ እግዚአብሔር “በላባችሁና በወዛችሁ ለፍታችሁ ደክማችሁ ብሉ፤ ጠጡም” ያለውን ህግ ወደጎን በመተው በሕዝብ ላይ ብዙ የስንፍናና የሥራ ማቆም አድማ እንዲሰፍን ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ከወር እወር በማያቋርጡ የበዓላት ጋጋታዎች ርሀብና ችግር እንዳይለቀን ከመደረጉም በተጨማሪ ህገ እግዚአብሔርን ጥሰናል፡፡ ምዕመናንን በረጃጅም የጸሎት መርሐ ግብሮች ሌት ተቀን እያደከምን እንቅልፋምነትን አበረታትተናል፡፡ አላስፈላጊ ድግሶችንና የፍትሃት ሥነ ሥርዓቶችን በመተግበር ዜጎችን አደኽይተናል፡፡ ሁሉን ነገር በአንተ ታውቃለህ ለፈጣሪ እየሰጠን ከእኛ የሚጠበቀውን ልፋትና ጥረት እንድንቀንስ ተገደናል፡፡ ….

2.2 በአምልኮት ደረጃ ካየን ብዙ ህፀፆችን መንቀስ ይቻላል፡፡ መነሻችንም መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ራሷን ከሀዲስ ኪዳን ጋር ማስተካከል አቅቷት ወይም ለማስተካከል ባለመፈለግ በብሉይ ኪዳን ብቻ እየተጓዘች ሕዝቡን አደንቁራና ከእውነተኛው አምልኮ እንዲያፈነግጥ በማድረግ ኮድኩዳ አስቀምጣዋለች፡፡ በዚያም ምክንያት ራሷ ተፈረካክሳ ለሌሎች መጤ ሃይማኖቶች ዋና መጋቢ ሆነ ትገኛለች፡፡ የርሷን ዶግማ የሚቃወም ሁሉ እንደጴንጤ ወይም እንደመናፍቅ እየተቆጠረ በዐውደ ምሕረት ላይ ስለሚሰደብና ስለሚሳቀቅ በርካታው ሊቅ በየቤቱ ቀርቷል ወይንም ቀልቡ ወዳልፈለገው ሌላ ቤተ እምነት እየሄደ የሌላ ቀማኛ ቡድን አድማቂ ሆኗል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግትር ባትሆንና ለውጥና ዕድሳት ቢያውቃት ኖሮ፣ ሰዎቿም ከምዕመኑ የበለጡ አንባቢና ተመራማሪ ቢሆኑ ኖሮ፣ ከተራ አቡነ ዘበሰማያትና “ይምሃረነ ይሰሃለነ…”  ባለፈ ቀሳውስቷ በሃይማኖቱ ገፋ ያለ ዕውቀትና ግንዛቤ ቢኖራቸው ኖሮ፣ የኦሪትን ብቻ ሣይሆን የሀዲሳት መጻሕፍትን የኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮዎች ብንከተል ኖሮ ….ይሄኔ ቤተ ክርስቲያናችን ኅልውናዋን የሚፈታተን ነገር ውስጥ ባልገባች ነበር፡፡ ምዕመናን ጠያቂ አእምሮ አላቸው – የሚያድግ የሚመነደግ አንጎልም አላቸው፡፡ ያን የሚመጥን የሃይማኖት አመራርና አገልጋይ ደግሞ ያስፈልጋል – ዘመናዊ ማኅበረሰብን ባረጀ ባፈጀ ሥርዓተ ቀኖና ለማገልገል መሞከር ውኃ መውቀጥ ነው፤ አይሆንም፡፡ ሕዝብ ይጠይቃል፡፡ በዱሮው በሬ እያረሱ፣ ፈታኝ ጥያቄዎችን ሲጠየቁ ደግሞ በ“ትቀሰፋለህ!” ጥንታዊ የሞኝ ፈሊጥ እያስፈራሩ በልብሰ ተክህኖ በተጀቦነ አላዋቂነት ማገልገል ሃይማኖትን ለማጥፋት ካልሆነ ለማልማት እንደማይጠቅም ካህኖቻችን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ይህን የምለው የሚሉትን የማይሆኑ ጳጳሣትንና ቀሳውስትን ውስጣዊ ችግር እዚህ ላይ መጥቀስ ባለመፈለግ ነው፡፡ እንጂ ወደዝርዝሩ ብገባ ጨዋው ከሊቅ ተብዬው የሚበልጥባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ፖለቲካና ቤተ እምነት በተስተካከለ የማጭበርበርና የማስመሰል ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማሳየት ይቻላል፡፡ ይቅር ይበለን፡፡

2.3 ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለገንዘብ ካደረች ቆየች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ አፍ አውጥቶ ይናገራል፤ እግር አውጥቶም ይራመዳል፡፡ በገንዘብ የሚጸደቅ ይመስል ስብከቱም ዐውደ ምሕረቱም ብዙ ጊዜያቸውን የሚያባክኑት ስለገንዘብ በማውራት ነው – ያቺን የፈረደባትን ከመቀነቷ ያላትን አውጥታ የሰጠች የመጽሐፍ ቅዱስ ባልቴት በመጥቀስ፡፡ ካህኑም ሆነ ደብተራው በገንዘብ ፍቅር ተጠምዶ ቃለ እግዚአብሔርን ዘንግቷል፡፡ በየቦታው የሚተከሉ ቤተ ክርስቲያናት ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ “ሕዝቡ የትኛውን ጽላት ይፈልጋል?” ተብሎ የሚተከል ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት ጽድቅ እንደሚኖረው እግዜር ይወቅ፡፡ አንድ አካባቢ ለምሣሌ የቅዱስ ገብርኤል ጽላት ሊገባ ቢል በአካባቢው የሚገኝ የሌላ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ይከለክላል፡፡ ምክንያቱ ሲጠየቅ “ሕዝብን ይወስድብናል” ነው፡፡ በዚህና በመሰል ርዕሰ ጉዳዮች የምንሰማው ሁሉ ይሰቀጥጣል – የካህናቱንና የአድባራቱን በጠብ መናከስ፣ የደባትሩን የድግምትና የአስማት ቱማታና የደብር አለቆችን የሙስና ባህርና ውቅያኖስ ትተነው ሊያውም፡፡ ሠጋር በቅሎና አምባላይ ፈረስ በነበሩበት ዘመን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በውርንጭላ አህያ የሄደው ለዛሬዎቹ ካህናትና ጳጳሣት በቪ8 እና በፕራዶ መሄድ ሃይማኖታዊ ጽድቅን እንደሚያስገኝ(ላቸው) ለማስገንዘብ አልነበረም፡፡ የኞቹ አባቶች ብዙዎቹ አልታደሉም፡፡ ያሳዝናሉ፡፡ አንድ እንኳን ጴጥሮስን ፈልጌ በመሃላቸው አጣሁባቸው፤ አንድ እንኳን ጳውሎስን ዳስሼ አጠገባቸው አላገኘሁም፡፡ እምነት በገንዘብ ከተለወጠ አዲዮስ ፈጣሪ፡፡ በዚህ ረገድ ተበለሻሽተናል፡፡ በዚህ በዚህ ሁኔታችን ጴንጤ ጥርሱን ተነቅሶ ቢስቅብን መብቱ ነው፡፡ ሃይማኖት ሸቀጥ ከሆነ የለየላቸው ኢአማኒያን (ኤቲስቶች) ይሻላሉ፡፡ ኤቲይስት ሁኑ እያልኩ ግን አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክለን እንያዝ፤ አለበለዚያ ተሳስተን እናሳስታለንና የሥራ መስክ እንቀይር ማለቴ ነው፡፡ አሁን ያለነው ደግሞ በቸርነቱ ብዛት እንጂ በቤተ እምነቶቻችን ጥረትና ፆም ጸሎት አይደለም፡፡ እንዲያ ቢሆን ኖሮ በየቀኑ የዐማራን ደም ካልጠጣ በሕይወት የሚቆይ የማይመስለው ጭራቅ (ቫምፓየር) ጠ/ሚኒስትር አይኖረንም ነበር፡፡ መጽሐፉ አስቀድሞ “ሁሉም በኃጢኣት ሥር ወድቋልና አንድስ እንኳ ፃዲቅ የለም” ስለሚል ይህ ዓይነቱ ክስተት ለኔ ምንም ማለት አይደለም – ሀገርን እያጠፋ መሆኑ ግና ይሰመርበት፡፡ ይህ ሁሉ ነውረኝነት የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነው፤ በዘመኑም ውስጥ እንገኛለንና ብዙ አንደናገጥ፡፡ ይልቁንስ ራሳችንን በቶሎ እንፈትሽና ወደ ደገኛይቱ መንገድ እንመለስ፡፡

2.4 ጽላትን በተመለከተ ብዙ ገፍቼ አልናገርም፡፡ ነገር ግን ይታሰብበት፡፡ ትምህርተ ክርስቶስን እናስታውስ፡፡ ሕዝብን አደንቁረን አንያዘው፡፡ ስግደትን ለፈጣሪ ብቻ እንዲያደርግ ሕዝብን እናስተምር፡፡ ከመጽሐፍ ቃል አናፈንግጥ፡፡ ከሃይማኖታዊ ባህልና ልማድ ፈጥነን እንውጣ፡፡ በጸሎት እርዝመትም የሚገኝ ጽድቅ እንደሌለ ከኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮ እንማር፡፡ አሁን ክርስቶስ ቢመጣ በምድር ሳለ “የአባቴን ቤት መሸቀጫ አደረጋችሁት” በማለት ቤተ ክርስቲያንን በካልቾ ብሎ ሁሉን ነገር እንደበታተነው የኛንም አብያተ ክርስቲያን በመነቃቀራቸውና ጉዳችንን አደባባይ አውጥቶ ባሰጣው ነበር፡፡ በዚህ ነጥብ ዙሪያ ብዙ ገባ እንዳላልኩ ይታወቅልኝ፡፡ ቤቴን ሰድቤ ለሰዳቢ አልሰጥም፡፡ ግን ውስጣችንን እንመርምር፡፡ የሰው መሣቂያም አንሁን፡፡ ከእውነተኛው መንገድ በእጅጉ መውጣታችንን እንረዳ፡፡

  1. ሕወሓት – ሕወሓት አብዛኛውን የትግራይ ሕዝብ በመርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ጠልፋ ፀረ ዐማራ አድርጋዋለች፡፡ በዚያም ምክንያት ለዐማራ አንዱና ትልቁ ተግዳሮት ከትግራይ ምድር ይፈልቃል፡፡ እነዚህ አንድ ሊሆኑ የሚገባቸው ሁለት ማኅበረሰቦች ዕርቅ ቢያወርዱ ግን ማንም አይፈነጥዝባቸውም ነበር፡፡ የሀገራችንም ችግር በቀናትና በወራት ውስጥ በተፈታ፡፡ ይህ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀርም፡፡ ነቀርሣ ነቀርሣው ይቆረጥና ሣምራውያን ዐማሮችና ተጋሩ ወደፊት ከሌሎች ደጋግ ዜጎች ጋር በመቀናጀት  የዚህችን ሀገር መፃዒ ዕድል ያሳምሩታል፡፡ አሁን ግን እውነቱ ሌላ ነው፡፡ አንድዬ ይማረን፡፡
  2. ሻዕቢያ – ዐማራ ጠሉ ኢሳይያስ በሰጠን የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ውስጥ እንደምንገኝ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ኦነግ ወለዱ ጭራቅ ጠ/ሚኒስትርም ለአያቱ ሻዕቢያ አድሮ ኢትዮጵያን በሻዕቢያ ወሮበሎች እያስፈነጨባት ነው – የትግሬና የዐማራ በሤራ ፖለቲካ መፋጀት ለሻዕቢያና መሰል የሀገራችን ጠላቶች ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ የነፃነት ትግል ከሻዕቢያም ጋር ነውና እንዘጋጅ፡፡  ድራማዎቹን ተዋቸው፡፡ ጭራቁ አቢይም ሆነ ኢሳይያስ በድራማ የሰለጠኑ፣ እውነተኛ ተፈጥሯቸውን ግን በምንም መንገድ የማይቀይሩ እባቦች ናቸውና በትያትር አትጠለፉ፡፡ እውነቱን ተገንዝባችሁ ለማይቀረው አርማጌዴዖን ተዘጋጁ፡፡ የአርማጌዴዖን ሰዓት ቀርባለች – በየበራችንም ደርሳለች፡፡ ወለጋ ጊምቢ ቶሌ ቀበሌና አጣዬ ተወስና የምትቀር ከመሰለህ ክፉኛ ተጃጅለሃልና ከጮቤ ረገጣህ ተመለስ፡፡ 
  3. ኦነግ – ኦህዲድ – ኦሮሙማ፡፡ አንድም ብዙም የሚመስሉት የኦሮሙማ ቤተሰቦች ቀላል እንዳይመስሏችሁ፡፡ በ27 ዓመት የሰለጠኑትን ዐማራን የማረድ “ጥበብ” በአራት ዓመታት ውስጥ እንዴት እያቀላጠፉት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ የሥልጠናቸው ግዝፈት ደግሞ ቦርቀው ያልጠገቡት አቢይና ሽመልስ በዚህ ለጋ ዕድሜያቸው ስንቱን ዶክተርና ፕሮፌሰር ነኝ ባይ ሁላ በንክኪ በሚተላለፍ አፍዝ አደንግዛቸው እያነሆለሉና በግሩም ንግግር እያማለሉ ከጎናቸው ማቆማቸው ዋና ምሥክር ነው፡፡ አሁን ድረስ ለነሱ የሚንሰፈሰፍ ዐማራና የሌላ ነገድ አባል ሞልቷል፡፡ በቀደምለት ወለጋ ላይ ከ3000 የማያንስ ዐማራ በኦነግ-ሸኔ ጦር ተከብቦ እንደዐይጥ ሲጨፈጨፍና ለዚያም ዕውቅና በመንፈግ የኅሊና ጸሎትም እንደብርቅ ተቆጥሮ ሲከለከል እያዩ “ዐቢይ ብቻውን ምን ያድርግ? ከሥሩ ያሉት እኮ ናቸው ሥራውን የሚያበላሹበት …” የሚሉ አሽቃባጭ-አሸርጋጆችን ማየት ከዐቢይ ሰይጣናዊ ዕኩይ ድርጊት ይበልጥ ያሳምመናል፡፡ ጊዜያቸው ነው ብለን ግን ተቀምጠናል – ፍርዱን ለፈራጁ ሰጥተን፡፡ እንጂ አያያዛቸው ሁላችንንም ሳይፈጁ አካላዊም ሆነ ኅሊናዊ ዕረፍት የሚያገኙ አይመስሉም፡፡ ለማንኛውም ይህም አንዱና ትልቁ ዐውደ ግንባር ነውና ይታሰብበት፡፡ ከታሰበበት ቀላል ነው፡፡ አለማሰባችን ነው ችግሩ – ዝምታችን፡፡ 
  4. ግብጽና ልጆቿ፡፡ ይህም የታወቀ ነውና ዝርዝሩ አያስፈልግም፡፡ የግብጽ እጅ በጣም ረጂም ነው፡፡ ወጥነት ያለው አቋም የሌላቸውን ሱዳንን የመሰሉ ሀገራትን እንደልቧ የምታዘውና ከአሜሪካ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚደረግላት ይህች የመርገምት ፍሬ ግብጽ ለኢትዮጵያ ተኝታ አታውቅም፤ ወደፊትም ቢሆን መቼም አትተኛልንም፡፡ ኢትዮጵያውያንን በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በመግዛት ከመከፋፈሏ በተጨማሪ በሱዳኖችና በሌሎች ሀገራት በኩልም የምትከፍትብን ጦርነት በቀላሉ የሚታይ አይደለምና ጠንቀቅ ነው ደጉ፡፡ የዐዋጁን በጀሮ አትሉኝም መቼም፡፡ ለማስታወስ ያህል ብቻ ነው፡፡
  5. ምዕራባውያን – በአሜሪካን መንግሥት የሚመራው ይህ ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ዐውደ ውጊያ እጅግ ከባድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያና አሜሪካ ማለት ጎልያድና ዳዊት እንደማለት ነው በመሠረቱ፡፡ በዚያ ላይ በዚሁ ጎራ ውስጥ የምትገኝን እንግሊዝን የመሰለች ማሽንክ ሀገር በጠላትነት ይዘን ትግላችን ፈጣሪ ካልታከለበት አደጋ ውስጥ ነው፡፡ እርግጥ ነው ዳዊትን አንረሳም፡፡ ጦርነትን እግዚአብሔር ካልተዋጋ ወታደር በከንቱ ይደክማል፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህ የምዕራቡ ዓለም የኢሉሚናቲዎች ስብስብ በሀገራችን ወቅታዊና መፃዒ ዕድል ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ የጦር መሣሪያንና ሌላውን ሎጂስቲክስ ጨምሮ በገንዘብም በማቴሪያልም በሰው ኃይልም በሥልጠናም በመረጃም ጠላቶቻችንን እያስታጠቁ ስለሚያሰማሩብን ብፁዓን የሃይማኖት አባቶች ኖረውን በምህላና በፆም በሱባኤ ባንታገዝም ጸሎትን ጨምሮ ሁል-አቀፍ ዝግጅት ማድረግ አለብን፤ አለበለዚያ ትግላችን ረጂም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ “ረጂም ጊዜ ሊወስድ ይችላል” ነው ያልኩት – ሌላ አላልኩም፤ አልልምም፡፡

8. የኑሮ ውድነቱ – ሆን ተብሎ በየቀኑ የሚያሻቅበው የኑሮ ውድነት ትልቅ ዐውደ ግንባር ነው፡፡ ሰዎች በኑሮ ውድነቱ እየተጠበሱ ነው፤ በርሀብ እያለቁ ነው፡፡ የብር አሥር ሽህና 20 ሽህ ደመወዝ ሊቋቋመው ያልቻለ የኑሮ ውድነት ገጥሞናል፡፡ የግል ህክምናውና ንግዱ እሳት ሆኗል፡፡ በእግርህ ወይ በመኪና ሮጠህ የገባህበት የግል ሆስፒታል በህክምና ስህተት ከገደለህ በኋላ ቤተሰቦችህን “ የታከመበትንና የዋለ ያደረበትን 700 ሽህ ብር ካልከፈላችሁ ሬሣችሁን አንሰጥም” ሲላቸው በተዓምር ብትሰማ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆንህ ይገለጥልሃል፤ ነጋዴውም የአንድ ሽህ ብሩን ዕቃ “20 ሽህ ብር ካልሸጥኩ ምኑን አተረፍኩ!” ብሎ ቡራ ከረዩ የሚለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው – የጉዶች ሀገር፡፡ የአብዛኛው የመንግሥትና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ደሞዝ ደግሞ ግፋ ቢል ሁለትና ሦስት ሽህ ነው – ይህ ማለት ደግሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዘመን አንድ ብርና ሁለት ብር፣ የደርግ ዘመን ሃያና 30 ብር እንደማለት ነው፡፡ በ1969ዓ.ም በወር ስድስት ብር የነበረው የበየቀኑ አንድ ሊትር ግሩም የላም ወተት አሁን ጥራቱ የተጓደለ ዝንቅ ወተት በወር 2000 ብር ነው፡፡ ስድስት ብር ወደ 2000 ብር ማደጓን አስላና ሌላውንም ሁሉ በዚሁ ስሌት አስቡት – በ1957ዓ.ም በሰባትና በስምንት ብር ይገዛ የነበረው ሠንጋ በሬ አሁን ከ50 ሽህ ብር በታች አታገኘውም – በቅርቡ እኮ የደለበ በሬ በብር 250 ሽህ እንደተሰሸጠ ሰምተናል፡፡ የዐርባ ሣንቲም ምሥር ክክ 140 ብር መግባቷንም አትዘንጉ ታዲያ – የሃምሣ ሣንቲሙ የአፄው ዘመን የብሩንዶ ቁርጥ አሁን ከ1000 እስከ 1500 ብር መግባቱን ጭምር፡፡ አንድ ኪሎ ቡና ብር አምስት መቶን መታከኩንም አትርሱ፡፡ መብራት ኃይልም በበኩሉ ወብርቶ በወር ሃምሣና ስልሣ ብር እከፍል የነበርኩትን ሰውዬ አሁን ብር 2400 ገደማ ሰቅሎታል፡፡ ጉድ ነው ብቻ፡፡ የአምስት ብሩ አንድ ማዳበርያ ከሰል ብር 550 መሆኑን ደሞ ማንም እንዲያስታውሳችሁ አትጠብቁ፡፡ የአርባ ሣንቲሙ ቢራም በትንንሽ መሸታ ቤቶች ከ40 ብር በታች አታገኙትም፡፡ ይሄው ነው፡፡ ሰው እንዴት እየኖረ ነው ታዲያ ብለህ ብትጠይቀኝ መልስ የለኝም፤ ባጭሩ “በተዓምር እየኖርን ነው” ብልህ አታምነኝምና፡፡ ሲዖልም ገነትም ያሉት ሌላ ሥፍራ ሣይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ኦሮሙማዎችና ጥገኞቻቸው ግን በዊስኪ ሲራጩና ልጆቻቸውን በዓመት 2 ሚሊዮን ብር ገደማ በሚከፈልባቸው አይሲኤስን በመሳሰሉ ትምህርት ቤቶች እንደሚያስተምሩ አውቃለሁ፡፡ የምትገርም ሀገር ከሚገርም በቁሙ የሞተ ሕዝብ ጋር፡፡ በነገራችን ላይ አሁን ቤት የሚሠራው፣ መሬት የሚቀማውና የሚዘርፈው፣ ሕንጻ የሚገነባው ኦሮሞነቱን ካለሀፍረት እስከጥግ እየተጠቀመበት ያለው የኦሮሙማ ደቀ መዝሙር እንጂ ሌላው ልትወድቅ የደረሰች ዛኒጋባውን እንኳን ማደስ አይችልም፡፡ ሁሉም የሥራ ዘርፍ፣ ሁሉም የሥልጣን ቦታ፣ ሁሉም የጥቅም ሸጥና ሰርጥ… የኦሮሞና በኦሮሞ የተያዘ ነው፡፡ ወያኔ-ትግሬዎችን የሚያስመሰግን ዘመን መጣና አረፈው፡፡ የሚመጣ ግን አይመስለኝም ነበረ፡፡ ግሩም ነው፤ ዕድሜ ሰጥቶት መጨረሻውን ያዬ፡፡ አይቀርም – የቆዬ ያያል፤ የኦነግ/ኦህዲድ/ብአዴን መጨረሻ ከወያኔ መጨረሻም ይብሳል፡፡ ግልጽ እኮ ነው!! በቃኝ፡፡

Filed in: Amharic