>

ከአማራ ህዝባዊ ሀይል መሪ ፋኖ ዘመነ ካሴ የተላለፈ መልእክት...!!!

ከአማራ ህዝባዊ ሀይል መሪ ፋኖ ዘመነ ካሴ የተላለፈ መልእክት…!!!

*…. ገዳዩና አራጁ ቡድን እነዚህን የተያዙ የፋኖ አባላት፣የልዩ ሀይል አባላት፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመረሸን ጅምላ መቃብሮችን እያዘጋጀ እንደሆነ የአማራ ህዝብ፣የአለም ህዝብ፣የአለም መንግስታት እንዲያውቁ እንፈልጋለን አድርሱልን!!!

➡️ለአማራ ልዩ ሀይል

➡️በመከላከያ ውስጥ ለምትገኙ የአማራ ተወላጆች

➡️ለሁሉም አማራ ህዝባዊ ሀይል(ፋኖ) አባላት

➡️ለሁሉም የአማራ ወጣት

መልእክቱ ይድረስ!

፩ኛ. ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ 7650 (ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ) የፋኖ አባላት ታፍነው ወደ ተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ተወስደዋል።

፪ኛ. “ፋኖን ትደግፋላችሁ!” በማለት ያውም የእኛን ስም በመጥራት ጭምር “የከሌን ትደግፋላችሁ!” በማለት ከ4565 (አራት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ አምስት) በላይ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ታፍነው አብዛኞቹ ደብዛው ጠፍቷል።

፫ኛ. በተጠራው አስቸኳይ የልዩ ኦፔሬሽን   ስብሰባ ላይ ሃሳባቸውን ያለምንም ፍርህት ሲገልፁ የነበሩ የአማራ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከባለፈው ግንቦት 13 ጀምሮ ታፍነው ተወስደዋል። “የከዳ ሰራዊት !” በሚል እየተጫኑ ያሉት ወደ ጅማ፣ ወለጋና ደቡብ ክልል ማረሚያ ቤቶች ነው።

ገዳዩና አራጁ ቡድን እነዚህን የተያዙ የፋኖ አባላት፣የልዩ ሀይል አባላት፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት #ለመረሸን ጅምላ መቃብሮችን እያዘጋጀ እንደሆነ የአማራ ህዝብ፣የአለም ህዝብ፣የአለም መንግስታት እንዲያውቁ እንፈልጋለን።

ትናንት ቅዳሜ ሰኔ 18/2014 በልዩ እስር ውስጥ የሚገኙትን አስራ ሁለት የሚሆኑ የአማራ ልዩ ሀይል አባላትን ሰብሰው ስለ ፋኖ አስቻጋሪነት እንዲመሰክሩና ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት ያቀዱትን እቅድ እነዚህ ልዩ ሃይሎች ሃሳቡን ባለመደገፋቸው “ወደ ወለጋ ወስደን ለሼኔ ነው የምንሰጣችሁ !” ብለው የተሳለቁባቸው መሆኑን ህዝባችን እንዲያውቀው እንፈልጋለን።

➡️እንደሚረሸኑና የጅምላ መቃብሮች እየተዘጋጁላቸው እንደሆነም በግልፅ ይታወቅ!

☝️በእውነተኛ ትግል ላይ የምትገኙ የአማራ ህዝባዊ ኃይል አባላትና የልዩ ሀይል አባለት እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አባለት፣ ታጣቂ የአማራ ወጣቶች ሆይ

❌ህግ ያለ መስሏችሁ እጅ እንዳትሰጡ እመክራለሁ ! ራሳችሁን እንድትከላከሉ ወንድማዊ መልእክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።

#ስለ እኩልነት፣ ሰላም፣ፍትህና ዴሞክራሲ የሚያስብ ሁሉ ይከተለን !

#እናሸንፋለን !

#እንደመማመጥ !

#አንድነታችንን እናስቀጥል !

#አንድ ህዝብ አንድ አማራ !

አንድ ኢትዮጵያ !

#ፍትህን ከገዳዮቻችን መጠበቅ ይበቃል !

#በእኛ መስዋእትነት የአማራን ህዝብ ሰላምና እኩልነት፣ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እናረገግጣለን !

#ከእኛ ጋር ስለሆነችሁ እናመሰግናለን !

Filed in: Amharic