>

በመተከል ከጉምዝ ታጣቂዎች ጋር በተደረገ ተኩስ ሁለት የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ተሰው

በመተከል ከጉምዝ ታጣቂዎች ጋር በተደረገ ተኩስ ሁለት የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ተሰው
 አንድ ሌላ የአማራ ታጣቂም ተሰውቷል
ጌጥዬ ያለው
በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ፤ ማንቡክ፤ ጉልባክ ቀበሌ ከኦነግ-ሸኔ እና ሕወሓት ጋር ጥምረት እንደፈጠረ ከሚነገርለት የጉምዝ አማጺ ቡድን ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ሁለት የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ተሰውተዋል። ያልተገባ መስዋዕትነት እንዲከፍልና አደረጃጀቱ እንዲፈስ እየተደረገ እንደሆነ ከሚነገርለት ልዩ ሃይል፤ አስራሦስቱ መቁሰላቸውንም ከስፍራው የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። ከአሸባሪዎቹ አጋር የጉምዝ አማጺ በኩል ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ታጣቂዎች ተገድለዋል። በሀገር መከላከያ ሰራዊት ባለቤትነት ብቻ እንደሚያዝ የሚታወቀውን ሞርታር የአማራ ልዩ ሃይል ከጉምዝ ታጣቂ ማርኳል።
በተያያዘ ዜና ባለፈ ባለፈው ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ከማል ጋሹ የተባለ ሌላ አማራ ታጣቂ በጉምዝ አማፅያን ጋር ሲፋለም በማንቡክ ከተማ አቅራቢያ ተሰውቷል። ወጣቱ በአካባቢው በርካቶችን በማሰልጠን ይታወቃል።
ከማል ጋሹ
Filed in: Amharic