>

የምዕራብ ወለጋው ጭፍጨፋ ከመከሰቱ በፊት በመንግሥት የተከናወኑ ተግባራት፦ ( አሳዬ ደርቤ)

ምዕራብ ወለጋው ጭፍጨፋ ከመከሰቱ በፊት በመንግሥት የተከናወኑ ተግባራት፦

አሳዬ ደርቤ

* …. መገን ብልጽግና‼️!

➔ የአማራ ድምጽ የሆኑ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ከእስር ቤት ታጎሩ፤

➔ለብአዴን የግርድና ወንበር አስጊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 12 ሺህ ፋኖዎች ታሰሩ፤

➔እንደ ዮሐንስ ቧያለውና አቶ ገዱ ያሉ አፈንጋጭ አመራሮች ተቀነሱ፤

➔ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፖርላማቸውን ሰብስበው ከመንግሥት ቀርቶ ከአክቲቪስት በማይጠበቅ የጥላቻ ንግግር ሕዝብን አነሳሱ፤

➔ከወራት በፊት ኢሰመኮ በጸጥታ ኃይሎች መፈጸሙን ገልፆ እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀበት ቪዲዮ “በኦሮሞዎች ላይ ፋኖዎች የፈጸሙት” ተብሎ ሶሻል ሚዲያ ላይ ተለቀቀ፥

➔ ከዚያም ከአንድ ሺህ በላይ አማራዎችን ያስጨፈጨፈው አካል በኅዘን ሳምንት ፈንታ የችግኝ ተከላ ሳምንት አውጆ እንጦጦ ጫካ ተደበቀ።

እናም እልኻለሁ…

ለተገደሉ ወገኖችህ ፍትሕን፣ በሕይወት ላሉት የመኖር መብትን የምትሻ ከሆነ …ዋነኛ ጥያቄህ “በወገኖቼ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን ይጣራልኝ” የሚል ይሁን!!

ያን ጊዜ ቶሌ ላይ ያስገደለህን አካል ቦሌ ላይ ታገኘዋለህ!

መገን ብልጽግና‼

ባለፈው የቆየ ቪዲዮ ለጥፎ ከ1600 በላይ አማራዎችን ደም አፈሰሰ። የሕዝብም ቁጣ ቀሰቀሰ።

ተቃውሞው ሲበረታበትም፣ የሱዳን ወታደሮችን 6 አስከሬን ለጥፎ የ1600 ንጹሐን እልቂት የፈጠረውን ቁጣ ቀለበሰ። እና ደግሞ ሲገደል የከረመው የአማራ ሕዝብ የሚሞትበትን ጦርነት ለኮሰ።

የብልጽግና ነገር ይገርማል‼️

ስትደግፈው ግጭት ለኩሶ ይጨፈጭፍኻል። የተረኛ እና የብሔርተኛ ማሊያ ለብሶ ያሳድድኻል።

ስትቃወመው ደግሞ አገራዊ ጦርነት ቀስቅሶ ያሰባስብኻል።

በዚያም ጦርነት ላይ እራስህን መከላከል ካልቻልክ ምድርህን አስወርሮ በሱዳን እጅ ወልቃይትን ለህውሓት የማቀበል ሥራ ይፈጽምብኻል ።

ብርቱ ሆነህ ከተገኘህ ደግሞ በጦርነቱ እኩሌታ ላይ ከጠላት ጋር ቁጭ ብሎ ይደራደርብኻል። ወይም ደግሞ እራሱ የለኮሰውን ጦርነት ለብቻህ አሰረክቦህ ይሰወርብኻል።

የሆነው ሆኖ…

ይሄን መድረክ እንደ ናትናኤል መኮነንና ደረጀ ሃብተወልድ ላሉ የጦር መሪዎች አስረክቤ ከመውጣቴ በፊት “የወገኖቻችንን ነፍስ ፈጣሪ ይማር!” እላለሁ። መንግሥት በሚል ሥም ጠላት የተሸከመው ሕዝብም ወኪል አልባ መሆኑን አውቆ አምላክ ይጠብቀው ዘንድ እመኛለሁ።

Filed in: Amharic