አሳዛኝ ቀን አርቲስት ሰለሞን ዓለሙ አረፈ….!!!!
(ይትባረክ ዋለልኝ)
ፀሀፊ ተውኔት ፤ ደራሲና ተዋናይ ነው ፡፡ በበርካታ ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውና አመት በላይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ተላልፎ የነበረው የሸምጋይ ተከታታ የሬዲዮ ድራማ ደራሲ ማለትም ( በአብዬ ዘርጋው ስም በሚታወቀው ስራው )
ደራሲና ተዋናይ ነው ሰለሞን ዓለሙ :: ሰለሞን ከዚህ ስራው በተጨማሪ የሙሉ ጊዜ ተውኔቶችን ፅፏል::ከዳንኪራው ጀርባ ፤ ፍራሽ ሜዳ ፤ የሁለት አለም ሰዎች ፤ ግርዶሽ ፤ ገመዱ ፤ ሰው ለሰው ፤ ድብልቅልቅ ፤ በድሉ ግራኙ ፤ አዙሪት ፤ ፅናት ፤ ወዘተ ከፀሀፊ ተውኔት ከደራሲ ፤ እና ተዋናይ ሰለሞን ዓለሙ ቀደምት ድርሰቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ፡፡
ኢትዮ ሪፈረንስ
በሰለሞን ዓለሙ ህልፈተ ህይወት የተሰማን ሃዘን ጥልቅ ነው። ለሰለሞን ዓለሙ ፈጣሪ መንግስተ ሰማያትን እንዲያወርስልንና ለቤተሰቡም መጽናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።