>

በሸዋሮቢት ተማሪዎችና መምህራን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለተጨፈጨፉት ዝቅ አድርገው አወለበለቡ!! (ሰሜን አሜሪካ ባልደራ)

በሸዋሮቢት ተማሪዎችና መምህራን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለተጨፈጨፉት ዝቅ አድርገው አወለበለቡ!!

ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

* …. በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ከበባው እንደቀጠለ ነው – ትላንት ማታ ሲተኮስ አድሯል!!

/

በሸዋሮቢት ተማሪዎችና መምህራን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለተጨፈጨፉት ዝቅ አድርገው አወለበለቡ። የከተማዋ ኗዋሪዎችም በወለጋ በአማሮች ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት በተቃውሞ ሰልፍ አውግዘዋል።

በኦሮሚያ በንፁሃን አማሮች ላይ በየጊዜው ጭፍጨፋ እየተፈፀመ እስካሁን ድረስ እንድም ጊዜ ፍትህ ባለመሰጠቱ እጅግ እንዳሳዘናቸውመ‍እ በተቃውሞ ሰልፍ ገልፀዋል።

“…ስርዓቱ በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን ለህዝብ ያስረክብ፣በአማሮች ላይ የሚፈፀም የዘር ማጥፋት በአስቸኳይ ይቁም፣የንፁሃን ወገኖቻችንን ጭፍጨፋ ማየት በቅቷናል.፣ ዘመነ ካሴን ማሳደዱ ይቁም….”የሚሉ የተቃውሞ መፈክሮችን አስምተዋል።

በተያያዘ ዜና፣ ትናንት ምሽት 4 ሰዓት በደብረ ብርሃን ዮኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ተከፍቶ የነበረው ተኩስ አሁን መቆሙን ተማሪዎች ጠቅሰዋል።

ትናንት ምሽት የመንግስት ታጣቂዎች በዮኒቨርስቲው ተኩስ ከፍተው ያመሹት የተማሪዎችን ዋና እና ምክትል ተወካዮች አፍኖ ለመውሰድ እንደነበረ ተገምቷል።ለጊዜው እንዳልተሳካላቸው ታውቋል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic