>
5:31 pm - Friday November 12, 7109

የዐቢይ መንግሥት አፋር በርሃ ውስጥ አፍ*ኖ ከሚያ*ሰቃያቸው 700 የዐማራ ወጣቶች የተላከ የድረሱልን ጥሪ! 

የዐቢይ መንግሥት አፋር በርሃ ውስጥ አፍ*ኖ ከሚያ*ሰቃያቸው 700 የዐማራ ወጣቶች የተላከ የድረሱልን ጥሪ! 

ይድረስ:

፦ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን

፦ለኢትዮጵያ ሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም

፦ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት

፦ለአማራ ክልል ሕዝብ

፦ለአማራ ክልል ፕሬዘዳንት

፦ለአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ

፦ለአማራ ክልል ፍትሕ ጽ/ቤት

፦ለአማራ ክልል ፖሊስ

፦ለአማራ ክልል ልዩ ኃይል

፦ለአማራ ክልል ሚድያ ማዕከል

፦ለአማራ ክልል ምሁራን መማክርት

፦በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለግልና ለመንግሥት ሚድያ ተቋማት እና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ጋዜጠኞች

ጉዳዩ፦ፍትህ ስለመጠየቅና ሰብአዊ መብት ጥሰት እየደረሰብን መሆኑን ስለመግለጽ።

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው እኛ ከዚህ በታች ስማችን የተዘረዘረው ግለሰቦች መንግሥት በአማራ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ብሎ ባወጀበት ወቅት ግንቦት 9/2014 ዓ.ም የግል ሥራችንን ከምንሠራበት ቦታ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በማለት በፖሊስ ከወሰ*ዱን በኋላ፣ ወንጀ*ላችን ምንድንነው ጥፋታ*ችንን ንገሩን ብለን ስንጠይቅ ከመንግሥት የመጣ ትዛዝ ነው በማለት ለ15 ቀናት በደብረማርቆስ እና በጎዛምን ወረዳ በየትኖራ ቀበሌ ባልታወቀ የግል ካምፕ ውስጥ አስረ*ውን ካቆዩን በኋላ ያለፍርድ ለምን በር*ሃብ እና በበሽ*ታ ታሰቃዩ*ናላችሁ ብለን ስንጠይቅ  አርፋችሁ ተቀመጡ እያሉ አንዳንዴም በመደ*ብደብ  ሲያሰ*ቃዩን ከቆዩ በኋላ በቀን 21/09/2014 በሌሊት እጅ*ና እግራ*ችንን በኤሌክትሪክ ገመድ በማ*ሰር መኪና ውስጥ ዓይናችንን አስ*ረው በማስገባት ወሰ*ዱን። የት ልትወስዱን ነው ቢያንስ ቅያሪ ልብስ ለቤተሰቦቻችን ደውለን እንጠይቅ ብንልም አርፋ*ችሁ ተቀመጡ በማለት በሌሊት ሲያጓጉዙን ሰንብተው አፋር ክልል ውስጥ ቡሬ የሚባል ቦታ ልዩ ስሙ ሱላ ካምፕ (ኤርትራ ድንበር ቀይባሕር) አካባቢ እጅግ በርሃማ ቦታ ያለምግብ፣ ያለውኃ እና መድኃኒት በሌለበት በአንድ ካምፕ 700(ሰባት መቶ) ወጣቶች እየተ*ሰቃየን እንገኛለን።

 

ሙቀት እና ርሃብ መቋቋም አቅቷቸው የሞ*ቱ ወንድሞችና ለሌሊት ያመ*ለጡ ልጆችም ይገኛሉ፤ በመሆኑም እናንተ ከላይ የጠቀስናችሁ ተቋማትና ማኅበራት በፍትሕ አምላክ ፍርድ ስጡን ጥፋ*ትም ካለብን ጉዳያችን በሕግ ተጣርቶ ቅጣ*ቱን በተገቢው ቦታ እንቀበላለን። ያለፍርድ እንዴት ለ2 ወራት እንሰቃያለን?

ስማችንን ከዚህ በታች በከፊል አስፍረናል፦

 

፦ምስራቅ ጎጃም

1) ዘመኑ ፀሀይ

2) አንደሻው ንጉሴ

3) መኳንንት ወዱ

4) አወቀ አዳነ

5) አዝመራው አደመ

6) በውቀት ጌታቸው

7) ይታያል ማኔ

8) ውብሸት ደጌ

9) አዛዥ አለቃ

፦ምዕራብ ጎጃም

1) አድማሱ ይታይህ

2) መንግሥቱ ይቤ

3) ዮናስ መለሰ

4) ጌትነት አንዷለም

5) ሀብቴ ሞላ

6) ጥላሁን ገሰሰ

7) መሌ አደመ

8) ጌቴ ፈረጃ (የአብን ሊቀመንበር የነበረ)

፦አዊ ዞን

1) ስሜነህ ጋሼ

2) አንዷለም የሽዋስ

3) ዘመኑ አቤል

4) ደመላሽ ዳኛው

5) ገ/ሚካኤል መለ ሰ

6) አድነው አገኘ

7) አህመድ መሀመድ

፦ደቡብ ጎንደር

1) ይርጉ አስፋው

2) መልካሙ ግዛቸው

3) ቆያቸው ዋጋ

4) ብርሃን ምስጋናው

5) ወ/ሮ እመቤት ፀሀይነው

6) ሞገሴ አባተ

7) ጋሻው ታዘብ

8) እያዩ ሀይሉ

9) 10 ዐለቃ ገብሬ መለ ሰ

10) ወርቅየ ዘገየ

፦ማዕከላዊ ጎንደር

1) ዮናስ ምትኩ

2) ስማቸው አማን

3) አድባሩ እሸቴ

4) ይታገስ ሹመት

5) ባየ ጥጋቡ

6) መሰረት እሸቴ

7) ፋሲል ደጉ

8) 10 ዐለቃ ገ/ትንሣኤ (በ24 ሠዓት ለረፍት ወጥቶ የተያዘ ታንክ ሹፌር)

፦ምዕራብ ጎንደር

1) ማረው አለልኝ

2) እንዳልክ አራጌ

3) ዘለቀ ሞላ

4) መብት ጨቅሎ

5) ሆነ ጌትነት

6) አድኖ ተስፋው

፦ሰሜን ጎንደር

1) ተስፋ ማረው

2) አለሙ በለጠ

፦ሰሜን ሸዋ

1) አማረ ለማ

2) ሚክያስ ወንዲፍራው

3) አበጀ ደጀኔ

4) ወሰኔ አምሴ

5) ከበደ ተክልዬ

6) ተክልዬ ሙሉጌታ

7) ጌታሰው አረጋ

8) ሰይፈ ፀጋዬ

፦ዋግኸምራ ሰቆጣ

1) ኃ/ማርያም አሠፋ

2) መልኬ ሲሳይ

3) ደሳለኝ ምህረት

4) ሰለሞን አዘነው

5) መሰረት ጨርቆስ

6) ብርሃን ደባሽ

7) ፅጌ አስረሴ

8) ፈንታው ወዳጅ

በአጠቃላይ ብዛት700

በሕግ አምላክ ፍትሕ እንዲሰጠን ስንል በተማፅኖ እንጠይቃለን።

አፋር ክልል ሱላ ካምፕ፤

Filed in: Amharic