>

"የታፈንኩት እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አላምንም የታፈነው የአማራ ህዝብም ነው...!!!" ( አቶ ጸጋ አራጌ)

“የታፈንኩት እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አላምንም የታፈነው የአማራ ህዝብም ነው…!!!”

አቶ ጸጋ አራጌ


*…. የአማራ ክልል ምክር ቤት የአፈና ውሎ ቀጥሏል…!!!

የሚያሣዝነኝ ነገር ቢኖር ቢያንስ ቢያንስ መናገርና ሃሣብህን መግለፅ ከምትችልበት ሁኔታ እንዴት የማትችልበት እጣፈንታ ይቀየራል። እኔ በኢህአዴግ ጊዜ በማንኛውም አጋጣሚ ሃሣቤን ከመግለፅ ተገድቤም ታፍኘም አላውቅም ለውጥ ብዬ ለለውጥ ታግዬ መጣ በተባለው የለውጥ ዘመን ግን የህግ ጥሠት አለ ሰነ ስረአት ይከበር ብዬ በመከራከሬ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አዳራሽ በፖሊስ ተይዠ እንድወጣ ትዛዝ ከተሠጠ በኋላ በምክር ቤቱ አባላት በተፈጠረ ጫጫት ፖሊስ ገብቶ ሣያወጣኝ ቢቀርም ነገሩ ግን እንዳልተፈፀመ አድርጌ አልወስደውም።

በመሠረቱ እኔ ሁሉንም ነገር ለመሆን የወሠንኩኝ ሠው መሆኔን ያላውቁ ሠዎች ጉዳዩን የተለያዬ ሠበብ አስባብ እየፈጠሩ ለማደናገር ቢሞክሩም አይሣካላቸውም። እኔ የአማራ ህዝብ ሞት እስከሚቆምና ጥያቄዎቹ እስከሚመለሱ ትግሉ የጠዬቀውን ዋጋ ሁሉ እከፍላለሁ።ይህንን ትግል ያለ ማቋረጥ በማንኛውም ያልተመቸ ሁኔታ ሣደርግ ስራ አጥቸ ጦም አዳሪ እንደምሆን ፣ታስሬ እንደምሠቃይ ፣ቀጥሎም የመጨረሻውን የሞት ፅዋ እንደምቀምስ በመዘጋት አይደለም። መኪናና እጀባ የጎድልብናል ብለው የአማራን ህዝብ በግዞት አስይዘው እንደሚቀልዱት ግን ለመቀለድ አልወሠንኩም። እኔ በምክር ቤቱ ውሎ ሃሣቤን ለመግለፅ እጀን ሣወጣ ብውልም እድል የሠጠኝ አካል የለም ።ሠው በህጋዊ መድረክ ከተከለከለ የሚጠቀመው የትግል መድረክ ያገኘውንና በእጁ ያለውን እድል ይሆናል።

በምክር ቤቱ አባላት የስነ ምግባርና የአሠራር ስረአት ደንብ ቁጥር 12/2003 አንቀፅ 15 ን/አንቀፅ 1,2,3 የምክር ቤቱ ስብሠባ እንዴት በግልፅና በዝግ እንደሚካሄድ በግልፅ አስቀምጧል እኔ የምጠይቀው የአማራ ክልልን ፍትህ ቢሮን ህግ በአደባባይ በማን አለብኝነት ሲሻር በተሻረ ህግ ስብሠባ ሲመራ ለምን ዝም እንደሚል ማብራሪያ እንድሠጥበት የሚመሩበትን ህግ የሻሩ ባለስልጣን ለምን እንደማይጠየቁ አሁንም ስለ ህግ አቤት እላለሁ ።

በመጨረሻም የታፈንኩት እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አላምንም የታፈነው የአማራ ህዝብም ነው።

እኔ የማቀርበው ሃሣብ የዚህን ያህል ሚዛን ተሠጥቶት የሚፈራ መሆኑን እስካሁን ብዙ አልገመትኩም ነበር ከዛሬ ስብሰባ የገባኝ ነገር ተካራክረው እኔን ማሸነፍ አይችሉም ።በወፊትም በሃሣብ አሻናፊ መሆኔን አረጋግጫለሁ ።ዝርዝር የምክር ቤቱን ሂዴት ከቀናት በኋላ እፅፋለሁ።

ሃሣብና እውነት ያሸንፋል !!ጉልበትና አፈና ይሸነፋል።

Filed in: Amharic