ስንታየሁ ቸኮል በ100.000ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ ተወስኗል…!
የሺሀረግ በቀለ
*…. ከአገር እንዳይወጣ ኢሜግረሽን ሁለት ጉርድ ፎቶ እንዲያስገባ ፍርድ ቤቱ አዟል..!
የስርዓቱ አስጨናቂ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በመቶ ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ወስኗል። ከአለፈው ቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ከነበረበት እስር ቤት ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዶ የቆየው ስንታየሁ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቧል። በአባ ሳሙኤል እስር ቤት እንደሚገኝም ተረጋግጧል።
የባልደራስ የድረጅት ጉዳይ እና ስራ አስፈፃሚ አይበገሬዉ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ በአራዳ ምድብ ችሎት የቀረበ ሲሆን የግፍ እስረኛዉ 100ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ የስርዓቱ አገልጋይ የሆነዉ ፍርድ ቤት ወስኗል እንዲሁም የህሊና እስረኛዉ ከአገር እንዳይወጣ ኢሜግረሽን ሁለት ጉርድ ፎቶ እንዲያስገባ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። መጨረሻዎን ማየት ነዉ እንግዲህ ቀጣይ ድራማ ይኖር ይሆን???