>

አርበኛ ዘመነ ካሴን በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለማስገደል መታቀዱ ተደረሰበት...! (ሳተናው ሚድያ)

አርበኛ ዘመነ ካሴን በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለማስገደል መታቀዱ ተደረሰበት…!

ሳተናው ሚድያ


አገዛዙ አርበኛውን በሀይል አስገድዶ ፍርድ ቤት ለማቅረብ በተደጋጋሚ ቢሞክርም አልሳካለት ማለቱን በመረዳቱ በሴራ ሌላ አደገኛ ኦፕሬሽን  ለመስራት እንዳቀደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህም አርበኛ ዘመነ ካሴን እንደ ጠላት የሚመለከቱ ሀይሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርገዋል፡፡ በስብሰባው ላይ ሁለት ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን የመጀመሪያው ከዚህ በፊት እንደሞከሩት አርበኛውን በሀይል አስገድደው ከማረሚያ ቤት ማስወጣት እና ፍርድ ቤት ማቅረብ የማይቻል እንደሆነ የገመገሙ ሲሆን ሁለተኛው እና ሊያደርጉት ያቀዱት አደገኛው አካሄድ ደግሞ ሦስት ሰዎችን ሽጉጥ አስይዘው እና ታራሚ አስመስለው በማስገባት አርበኛ ዘመነ ካሴን እንዲገድሉ ማድረግ ነው፡፡

በዚህም በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በድብቅ መሳሪያ ይዘው እንዲገቡ በሚመለመሉ ሰዎች አማካኝነት ድራማዊ የሆነ ግርግር በማስነሳት የትግል ምልክት የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሴን ለመግደል እንደወሰኑ ሳተናው ለማወቅ ችሏል፡፡

የአማራ ህዝብ ከዚህ በፊት ለህዝባቸው የሚታገሉ ጀግኖችን በራሱ በብአዴን አገዛዝ በማጣት እና አታጋይ ጀግና ባለመኖሩ ህዝባችን በየቦታው በግፍ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ይገኛል፡፡ ለአብነትም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን፣ አርበኛ አስቻለው ደሴን፣ ሳሙኤል አወቀን፣ ፋኖ መዝገቡን እና በርካታ ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን ጀግኖች አጥተናል፡፡

አሁንም ለራሳቸው ህዝብ መድረስ ያልቻሉና ስቃዩ የማይሰማቸው ሀይሎች ሌላኛውን የትግል አርማ አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማሳጣት ሌትተቀን እየደከሙ ይገኛሉ፡፡

ሁሉም የአማራ ህዝብ ካለፈው ተምሮ አሁን በህይወት ያሉ እና ለህዝባችን እየታገሉ የሚገኙ ጀግኖችን በንስር አይን ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡

የአማራ የትግል አብሪ ኮከብ የነበረው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በትግል ህይወቱ ከተናገረው ትልቅ ንግግር አንዱ ‹የአማራ ጠላቱ ሆዳሙ አማራ ነው› እንዳለው ሁሉ አሁንም በአማራ ስም ስልጣን ይዘውና ወንበር ላይ ተቀምጠው ለአማራ የሚታገሉትን እንቁ ልጆች በመግደል አማራን ያለ ታጋይ ለማስቀረት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም የአርበኛ ዘመነ ካሴ ወዳጆች እና የትግሉ ደጋፊዎች ይህንን አደገኛ አካሄድ ቀድሞ በመረዳት ትልቅ ርብርብ በማድረግ አርበኛውን ከጉዳት መጠበቅ ይገባል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የአማራ ፋኖ ከመግለጫ ጋጋታ ወጥቶ ወደ ተግባር እርምጃ በመግባት አርበኛውን ከተደገሰለት የሞት ድግስ በመታደግ ታሪካዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ሳተናው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

የአማራ ህዝብ ከበባውን ሰብሮ ድሉን ይቀዳኛል!!

አርበኛ ዘመነ ካሴ የማንደራደርበት ቀይ መስመራችን ነው !!

Filed in: Amharic