ጠላትህ ቤትህ ሲገባ፣ በርህን ዘግተህ ልክ አስገባ
መስፍን አረጋ
“መውጫ መግቢያውን፣ መሮጫ ማምለጫውን፣ መሸሻ መደበቂያውን በማታውቀው ቀጥና አትዋጋ” (ሰንሹ Sun Tzu)
በወለጋ ጭፍጨፋው ያልረካው፣ አማራን በልቶ ካልጨረሰ የማይጠረቃው የጭራቅ አሕመድ አውሬ ጦር አማራ ቤት ውስጥ ገብቶ መርመስመስ ጀምሯል። በዚህ ድርጊቱ ደግሞ ላማራ ሕዝባዊ ግንባር ከፍተኛ ዕድል ፈጥሮለታል። የጭራቅ አሕምድ ኦነጋዊ ጦር የገባበትን ቤት መውጫ መግቢያ ስለማያውቅ፣ በቀላሉ በማደነጋገር፣ በተገኘው ዲንጋ ሁሉ በመውገር፣ እገባበት ቤት ውስጥ መቅበር ይቻላል። ያማራ ሕዝባዊ ግንባር ማድረግ ያለበትም ይሄንና ይሄንኑ ብቻ ነው። ኦነግ ሙቶ መቅበር ያለበት ሊያጠፋው እመጣበት አማራ ክልል ላይ ነው፡፡
ያማራ ሕዝባዊ ኃይል የሚዋጋው ጓዳ ጎድጓዳውን በሚያውቀው በገዛ ቤቱ ውስጥ ስለሆነ፣ በምዕራባውያን የሚደገፈውን፣ እስካፍንጫው የታጠቀውን የጭራቅ አሕመድ ጦር መግጠም ያለበት ፊት ለፊት ሳይሆን በደፈጣና በደፈጣ ብቻ ነው።
ያማራ ሕዝባዊ ኃይል ወገልጤና እና አማራ ሳይንት ላይ እንዳደረገው፣ ባልታሰበ አዛዥ እየተመራ፣ ካልታሰበበት አቅጣጫ በመመጣት ያልታሰበን ቦታ በድንገት ከተቆጣጠረ በኋላ ማድረግ ያለበትን ሁሉ በፍጥነት አደራርጎ ወዳልታሰበበት አቅጣጫ መሄድ አለበት። በዚህ ድርጊቱ ደግሞ ያማራ ሕዝባዊ ኃይል ባውሎ ንፋስ ወይም በመብረቅ ሊመሰል ይችላል። አውሎ ነፋስ ባልታሰበበት ሰዓት ካልታሰበበት አቅጣጫ በድንገት ነፍሶ፣ የሚጠራርገውን ጠራርጎ ወዳልታሰበበት አቅጣጫ ይነጉዳል። መብረቅ ደግሞ ሲበርቅ እንጅ መቸና በየት በኩል እንደሚበርቅ አይታወቅም። ከበረቀ በኋላ ደግሞ ዓይንን ቢጨፍኑ ዋጋ የለውም። ሲበርቅ ቢጨፍኑ ከመወጋት አይድኑ።
ያማራ ሕዝባዊ ኃይል ያልታሰበን ቦታ በድንገት ሲቆጣጠር፤ የጭራቅ አሕመድ ጦር ቦታውን ለማስለቀቅ በኮንቮይ መግተልተሉ አይቀሬ ነው፡፡ ያማራ ሕዝባዊ ኃይል ማድረግ ያለበት ደግሞ፣ ኮንቮዩ መዟዟሪያ ከሌለው ጠባባ የተራራ መንገድ ላይ እስኪደርስ ጠበቆ፣ የኮንቮዩን የመጀመርያና የመጨርሻ መኪኖች በማጋየት ኮንቮዩ ወደፊትም ወደኋላም መንቀሳቀስ እንዳይችል ዘግቶ፣ ግራ የተጋባውን የኦነግ ሠራዊት ይበልጥ ግራ እያጋባ በመትረየስ መልቀም ነው።
ያማራ ሕዝባዊ ኃይል የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ድል በማድረግ ያማራን የሕልውናውን ትግል በድል ማጠናቅቅ ያለበት አማራ ክልል ላይ ነው፡፡ ወደ አዲሳባ ማምራት ያለበት ድሉን ለማክበርና ጭራቅ አሕመድንና አጋሮቹን ለፍርድ አቅርቦ ዘላለማዊ መቀጣጫ ለማድረግ ብቻ ነው፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com