>

የትግል አንድነትና የትብብር ስምምነት!

የትግል አንድነትና የትብብር ስምምነት!

ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር እና ከፍትህ ለኢትዮጵያ የፈለገ ቴዎድሮስ ንቅናቄ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

ሰኔ 19/ 2015 ዓ.ም

እራሱን የኦሮሞ ብልፅግና ብሎ የሚጠራው ቡድንና ተባባሪዎቹ፣ ከትህነግ/ወያኔ በውርስ የተረከቡትን አማራን በጅምላ የመጨፍጨፍ እና ኢትዮጵያን እንደሃገር የመበተን ትልም እውን ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ለጥፋት ዘመቻው ይጠቅመኛል ብለው በነደፉት ስልት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ እስልምና የዕምነት ተቋማት ላይ የጥፋት ዘመቻ ከፍተው የጦር ወንጀል እስከመፈፀም ደርሰዋል።

በዚህ ሂደት፣ በህዝብ ላይ “ይህ ቀረሽ” የማይባል በደል እየተፈጸመ፣ በመንግስታዊ መዋቅር ድጋፍ አማራው በማንነቱ እየታደነ እና በአሰቃቂ ሁኔታ እየተጨፈጨፈ፤ ሙያተኛ የመንግስት ሰራተኛ ከሃላፊነቱ እየተወገደ፤ በንግድ ስራ የሚተዳደረው ነጋዴ ላይ ሊከፍለው የማይችለው ከባድ ግብር እየተጫነ፤ ዜጎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው የንግድ ስራቸውን እንዳይሰሩ እየተደረገ፤ ወላጅ ልጆቹን ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልኮ ያለስጋት ማስተማር እየተሳነው፤ የመላ ኢትዮጰያዊያን ይዞታ በሆነችው አዲስ አበባ ዜጎች በብሄር እየተለዩ ከይዞታቸው እየተፈናቀሉና ያለምንም መጠለያ ሜዳ እየወደቁ ይገኛሉ።

ስለዚህም፣ ሀገራችንን ኢትዮጰያ ከመፈረካከስ፣ የፅንፈኞች ዋነኛ ዒላማ የሆነውን የአማራ ህዝብን ከጅምላ ፍጅት ለመታደግ ስንል፣ በየግላችን ተደራጅተን እየታገልን የምንገኝ እኛ ፍትህ ለኢትዮጵያ የፈለገ ቴዎድሮስ ንቅናቄ እና የአማራ ሕዝባዊ ግንባር፣ ሰፊ ውይይት እና ምክክር ካደረግን ቦኃላ ትግላችንን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ አቅማችንን አስተባረን ተባብረን ለመስራት ተስማምተናል። በቀጣዩ ትግላችን የህዝብ ድጋፍ እንደወትሮው ተጠናክሮ እንዲቸረን በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናስተላልፋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቃት!
ሰኔ 19 2015 ዓ.ም

Filed in: Amharic