>

"..እኛ የፖለቲካ እስረኞች ነን" ስንል በምክንያት ነው 51ዱም ተከሳሾች  አማሮች ናቸው...! (ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ በችሎት ከተናገረው)

“..እኛ የፖለቲካ እስረኞች ነን” ስንል በምክንያት ነው 51ዱም ተከሳሾች  አማሮች ናቸው…!

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ በችሎት ከተናገረው

ጠቅላይ ሚኒስርት ዐቢይ አህመድ የፍትህ ተቋማት ዳኞች ሎቦች ናቸው ብለዉ ተናግረዋል። ነገር ግን

“ዐቃቢ ህግ  አልከሰሳቸውም።

“..እኛ የፖለቲካ እስረኞች ነን” ስንል በምክንያት ነው 51ዱ ተከሳሾች በሙሉ አማሮች ናቸው። የተከሰስነው ሰርቀን አይደለም ወይም ወለጋ ሰዉ ጨፍጭፈን አይደለም  ሸገር ሲቲ ዜጎች አፈናቅለን   አይደለም። ነገም ደጋግመን እንለዋለን ክሳችን ወንጀላችን አማራ ሆነን ነው። ይሄ አይቀየርም ከፈለጋችሁ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሄዳችሁ ብታዩ  በሙሉ አማራ ብቻ ናቸው።

“..እኔ በአንድ ወቅት የመንግስት መገናኛ ብዙኸን ውስጥ ጋዜጠኛ ነበርኩ እንዴት እንደሚሰራ አውቃለሁ የፓርቲ ትዕዛዝ እንደወረደ አይቀርብም። በእኔና በረ/ፕሮፌሰር  ሲሳይ አውግቸው የፀጥታ ደህንነት ግብረሃይል መግለጫ በማለት ሽብርተኛ ብሎ በእኛ ላይ ሁለት ጊዜ ዘገባ ሰርቷል።

በዚህ ችሎት ባሉ ተከሳሾች ሁሉም ላይ በተደጋጋሚ የሽብርተኝነት ዘገባ ተሰርቷል። ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ወረቀትና እስኪብርቶ እንጅ የጦር መሳሪያ ይዤ ፎቶ አልተነሳሁም ከየት አምጥቶት ነው ግብረሃይሉ ፎቶሾፕ ያቀናበረው? ስለዚህ ፍ/ቤቱ  ፋና ዋልታ እና OBN የመንግስት መገናኛ ብዙኸን በሰሩት ዘገባ መጥተዉ እንዲያስረዱ ጥብቅ ትህዛዝ ይሰጥልን። በተሰራው ዘገባ የሞራል ድቀት አድርሰውብናል ቤተሰቦቻችን በእጅጉ ተጎድተዋል። በፍርድ ቤት ሂደት ያለን ሰዎች ነፃ ሆነን የመታየት ህገመንግስታዊ መብታችን ተጥሷል።

የአማራ ተወላጅ በመሆናችን የፖለቲካ እስረኛ ነን የምንለው በተጨባጭ ማሳያ ነው። የሚዲያዉ ኃላፊዎች መጥተው ለምን እንደዘገቡት ያስረዱ ይህ ካልሆነ ጠንከር ያለ እርምጃ እኛም እንወስዳለን።

ጠቅላይ ሚኒስርት ዐቢይ አህመድ የፍትህ ተቋማት ዳኞች ሎቦች ናቸው ብለዉ ተናግረዋል። ነገር ግን

ዐቃቢ ህግ አልከሰሳቸውም።

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው

ሀምሌ 3/2015 ዓ,ም የተናገረው ተመዝግቧል።

የችሎት ዘገባ 

ስንታየሁ ቸኮል ባልደራስ

Filed in: Amharic