>

“ባለፉት ስድስት ዓመታት አንድም ሰው ‘torch’ አላደረግንም - የሞቀ  ጭብጨባ፡፡”

“ባለፉት ስድስት ዓመታት አንድም ሰው ‘torch’ አላደረግንም – የሞቀ  ጭብጨባ፡፡”

 

ነፃነት ዘገዬ

 

ይህ ማይም ሰውዬ በስንቱ አሳቅቆ ሊፈጀን እንደሆነ ቀጣዮቹን ምሣሌዎች እንመልከት፡፡

Torch – ትርጉሙ flashlight/ባትሪ ወይም በገጠር አካባቢ ከጣሊያንኛ ተወስዶ ‹ላምባዲና›  የምንለው ነው እንጂ እርሱ ማለት የፈለገው ከእግሊዝኛ ወደአማርኛ ሲመለስ “ማሰቃየት” የሚለው አይደለም፡፡ ይህን የእንግሊዝኛ ቃል በዐረፍተ ነገር ብናየው – He broke his torch when he fell down. Please give me that torch; I want to use it when I have to go to the rest room because the bulb doesn’t work there.

Torture – ትርጉሙ እንደስም “ስቃይ”፣ እንደግሥ ደግሞ “ማሰቃየት”ን በሰው ወይ በእንስሳ ላይ መተግበር ማለት ነው – ማሰቃየት አርዕስታዊ ስም ነውና፡፡ ምሣሌ፡- The pathological liar Abiy Ahmed tortured millions of Ethiopians in the past six years, though he blatantly denies it.

ይህ ሰው ውሸቱ ብቻ ሣይሆን ሳያውቅ አውቃለሁ ባይነቱ ከዕብለቱ ባልተናነሰ የሚያቃጥለን ሰዎች ጥቂት አይደለንም፡፡ የግል ትምህርት ቤት የኬጂ ተማሪ የማይሠራቸውን አንድ ሁለት ያህል የእንግሊዝኛ ስህተቶቹን እንይለት፡፡

Both country – to mean both countries; 

By implies – to mean by implication;

ወደ ዋናው ቁም ነገር እንግባ፡፡ ይህ ሰውዬ ከኢድ አሚን ዳዳ በላቀ የድንቁርና ኩራቱ እየተኮፈሰ የሚመራው የብል.ግና ፓርቲ – ፓርቲ መባል እንኳን የለበትም ነበር – ከትናንት ጀምሮ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ ይህ ሰውዬ ከዓለም ህጎች በሙሉ በሚጣረስ መልኩ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ጠቋሚ፣ ራሱ አስመራጭ ሆኖ ራሱን እንደሚያስመርጥ ባለፈው ስብሰባ ታዝበናል፡፡ እኛስ እኛ ነን፡፡ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬው ስለዚህ ዋሾና አፈንጋጭ ዕብድ ፀጥ ረጭ ማለቱ የሚገርም ነው፡፡ አሁንም 2000 የሚጠጋ ከብቶችን ማለትም ድልብ ሠንጋዎችን ሰብስቦ በዐድዋ መታሰቢያ አዳራሽ እየወሸከተ ነው፡፡ በርዕሳችን የተጠቀሰው ፍጹም ውሸት በዚህ ሰውዬ አንደበት የተነገረው እንግዲህ በትናንትናው ዕለት በዚያው ጉባኤ መሆኑ ነው፡፡ የርሱ ውሸት እንዳለ ሆኖ በእያንዳንዱ የውሸት እስትንፋሱ የሚስተጋባው ጭብጨባ ደግሞ ከማበሳጨት አልፎ በነማን እየተገዛን እንደሆነ ሲያስቡት ዕበዱ ዕበዱ ያሰኛል፡፡ እሱስ ሀፍረቱን ባወጣ ሸጦ በልቷል፡፡ ያ ሁሉ ሰው ግን እንዴት አንድ ይሆናል? ነገ መኖሩን እንዴት ረሱ? ለትውልዳቸው ማሰብስ እንዴት አቃታቸው? ይህ ጊዜ እኮ ያልፋል፡፡ ያኔ “ ተመልከት ያን ልጅ! የማን ልጅ እንደሆነ ታውቃለህ? የወሽካታው አቢይ ፓርላማ እንቅልፋምና አጨብጫቢ ልጅ ነው!” መባል በእጅጉ አሣፋሪ ነው፡፡ ዘመድ ካላቸው ይህን የታሪክ ጠባሳ ይንገራቸው፡፡ ከዚህም ብዙ ሳይመሽ፡፡

ከጃዋር እስከ ሕዝቅኤልና ፀጋየ አራርሣ፣ ከሌንጮ ባቲ እስከ ምርኮኛ አሥር አለቃ ጁላ፣ ከመለስ ዜናዊ እስከ ጌታቸው ረዳ፣ ከአሥራት ገብሩ እስከ ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ከአልማዝ መኮ እስከ አልማዝ ሠይፉ፣ ከሌንጮ ለታ እስከ ሽመልስ አብዲሣ፣ ከታዬ ደንደኣ እስከ ታየ ቦጋለ፣ ከመረራ ጉዲና እስከ በቀለ ገሪባ፣ ከኃይሌ ፊዳ እስከ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ፣ ከአቢይ አህመድ እስከ ለማ መገርሣ፣ ከኩማ ደመቅሣ እስከ አበበ ቶላ ፈይሣ፣ ከሲሣይ ጋጋኖ ማለትም አጌና እስከ ኃይሉ ጎንፋ፣ ጄኔራል ዋቄ እስከ አባቡ ደባልቄ፣ ከደበላ ዲንሣ እስከ ጫልቱ መገርሣ፣  … ምን አለፋህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በጉልበቱ ገብቶ የሚፈተፍትም ሆነም በወልጋዳ የምርጫ ሂደት ሥልጣን የሚይዝ ሁሉ አፍ መፍቻ ቋንቋውን ጓዳው አስቀምጦ በአማርኛ እየተናገረና መጽሐፍ ጽፎበት እንጀራውን እያበሰለ የሚኖር የአማርኛ ተቀላቢ አሁን ምን ታያቸውና ነው አማርኛን የማጥፋት የማይሆን ዘመቻ በዐዋጅ ያጸደቁት? አማርኛ በዋሽንግተን ዲሲ አንዱ የብሔራዊ ቋንቋ መሆኑን፣ በቻይናና በራሽያ በትምህርት በቤቶች ሳይቀር እየተሰጠ መሆኑን፣ በኮርያውያን አንደበት እየተንበለበለ መነገሩን፣ በብዙ ፈረንጆች አንደበት የአፍ መፍቻ ያህል እንደብርቅ መነገሩን፣  በጀርመን የማኅበራዊ ሣይንስ የጥናትና ምርምር ማካሄጃ ቋንቋ መሆኑን፣ በአፍሪካ እጅግ ብዙ ሀገራት ተፈላጊ መሆኑን፣ ወዘተ. እኚህ ደናቁርት ባለጊዜዎች አላወቁ ከሆነ ይነገራቸው፡፡ አንዳንዴ ባለቤቱ የሚያቀለውን አሞሌ ባለዕዳ የሚቀበልበት መልካምና የተለዬ ወይም ያልተጠበቀ አጋጣሚ መኖሩንም አማርኛን በማጤን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ያባረረቻቸውን አማሮች ዓለማችን ተቀብላ በብዙ በረከቶች እንዳጎናጸፈቻቸው ሁሉ ሕወሓት በከፊል ኦሮሙማ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋው የዘመተበትን የአማርኛ ቋንቋ ደግሞ ይህቺው ዓለም አላሣፈረችውም – በፀጋ ተቀብላዋለች፡፡ ወደፊትም ገና የዓለም አንዱ ቋንቋ ይሆናል፡፡ ይህን ስል ግን ከቋንቋ ዕድገት ህግና ሥርዓት ተነስቼ እንጂ ቋንቋውን ወይም ተናጋሪዎቹን ስለምወድ አይደለም – ደግሞም ለምንስ እጠላቸዋለሁና? በመልመድና በመማር ካልሆነ እንደቋሚና ተንቀሣቃሽ ንብረት ከእናት አባት የማይወረሰው ቋንቋ በመሠረቱ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ ዱላ መማዘዣ ሊሆን አይገባም፡፡ በቋንቋ የሚጣሉ እልም ያሉ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ ነገ ጥለሃት በምትሄዳት ዓለም ውስጥ የኔ የምትለው አንድም ነገር የለም – ሌላው ቀርቶ የኪስህ ቦርሣም ያንተ አይደለም፡፡ ስንቱ ነው በቢሊዮኖች አከማችቶ አይቶት ብቻ የተሰናበተ? በእውነት ቂልነት ነው፡፡ የአንድን ቋንቋ ተናጋሪዎች ልትጠላ ትችላለህ፡፡ ቋንቋውን መጥላት ግን ዕብደት ነው፡፡ አፄ ዮሐንስ በአማርኛ የገዙት፣ መንግሥቱ ኃይለማርያም በአማርኛ የገዛው፣ አፄ ኃይለ ሥላሤ በአማርኛ የገዙትአፄ ምኒልክ በአማርኛ የገዙት አማርኛን ስለወደዱት ሣይሆን ለአገዛዝ ስላመቻቸው ነው፡፡ እንግሊዝኛን በቦሌም በባሌም ልንማር የተገደድነው እንግሊዝን ወይም እንግሊዝኛን በአፍ መፍቻነት የሚናገሩትን ሕዝቦች ወደንና አፍቅረን ሳይሆን እንግሊዝኛን መናገር የሚሰጠውን ዓለም አቀፍ ጠቀሜታ አስበን ነው፡፡ ከዚህ አኳያ አማርኛ ባይኖር ኖሮ ይሄኔ ኦሮሙማ ጉድ ሆኖ ነበር፡፡ አንድ እውነተኛ ቀልድ ትዝ አለኝ – የኔ ነገር፡፡ “ጨዋ” አንባቢ ይህን አንቀጽ ይዝለለው፡፡

አባትና እናት ገላቸውን ለመታጠብ ወደፍል ውኃ ይሄዳሉ – ወንድ ሕጻን ልጃቸውን ይዘው፡፡ በዚያን ዘመን ወንድና ሴት በአንድ ላይ ወደአንድ መታጠቢያ ገንዳ አይገቡም ነበርና እናት ለብቻዋ አባትም ለብቻው ሊገቡ ሲሉ ልጁ ወደእናቱ ያዳላና ወደዚህ ልግባ ይላል – ወደእናቱ፡፡ አስተናጋጆች ደግሞ “ሴት ልጅ ወደእናቷ፣ ወንድ ልጅ ደግሞ ወደ አባቱ ነው የሚሄድ” ብለው ይከለክሉታል፡፡ ልጁ እየከፋው አባቱ ጋ ገባ፡፡ ቆመው መታጠብ እንደጀመሩ ልጅዬው ሣሙናው ያዳልጠውና ወድቆ ሊፈጠፈጥ ሲል የአባቱን አንድ ነገር ይዞ ለጥቂት ይተርፋል፡፡ አባቱም “ይሄኔ እናትህ ጋር ገብተህ ቢሆን ኖሮ ጥርስህን ለቅመህ ነበር፡፡” አለው ይባላል፡፡ ነገር ያለማዋዣ አይጣፍጥምና ባለጌ አትበሉኝ፡፡

እናሳ! “በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ” ብላችሁ ተቀኛችሁ? 

ለማንቻውም የዕብዱ አቢይ ፀሐይም እየጨለመች ናት፡፡ ባትጨልምበት ኖሮ የሚናገረው ሁሉ ይህን ያህል ቅጣምባሩ ባልጠፋበት ነበር፡፡ የጨለመበት ሰው ደግሞ ልክ ባሕር ላይ እየሰመጠ ያለ ሰው ይመስላል፡፡ እየሰመጠ ያለ ሰው የሚያድነው እየመሰለው ዐረፋውንም ገለባውንም ይጨብጣል፡፡ እንጂ በየእሥር ቤቱ ካለበቂ ምግብ፣ ካለመብራትና ውኃ፣ ካለአየር በድብደባና ኢሰብኣዊ ድርጊቶች መከራና ሲቃ እየወረደበት ታጉሮ የሚገኘው ዜጋ ከአንድ ሰው አንሶ ነው እስከዚህ የሚበጠረቀው? የሚገርመው አጨብጫቢዎቹም እኮ እውነቱን ያውቃሉ – ለማጨብጨብ ስለሚገደዱ እንጂ፡፡ አማራን እንደሰው ሳይቆጥር እንደተናገረ እንውሰድለትና እነክርስቲያን ታደለንም እነዮሐንስ ቧ ያለውንም እንተዋቸውና መጣሁበት የሚለውን የኦሮሞ ብሔርም ብናይ ኢሰብኣዊነቱ ሊቀንስ ይችላል እንጂ ስቃዩና ሞቱ፣ ስደቱና እንግልቱ በዚያም ሠፈር አለ፡፡ እርሱና ቡድኑ እንደሰው ከሚቆጥሩት የኦሮሞ ነገድ ስንቱ ነው የታሰረው፣ የተሰቃየው፣ በሌሊትም ወጥቶ በከተማ መሀል የተገደለው? “አንድም ሰው አላሰቃየሁም” ብሎ በሰው መከራና ስቃይ ማፌዝ ምን ይሉት ቀልድ ነው?  ውይ … አሁንስ ምርር አለኝ፡፡

Filed in: Amharic