>

የሳይበሩ ጥምር ጦር በድማሚት ተመቷል!

የሳይበሩ ጥምር ጦር በድማሚት ተመቷል!

የብልፅግና ፣ሣልሳይ ብአዴን እና ተከፋይ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት/ ግሪሳ ጥምር ጦር የዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ከአራት ታላላቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች (ኢጋድ፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ተወካዮች) ጋር ባደረገው ውይይት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀዋል። በመሆኑም ሃይላቸውን አሰባስበው፣ ተደራጅተው የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህም የዐማራ ህዝብ ጠላቶቹን የለየበት፣ አስመሳዮች ጭምብላቸውን ሳያስቡት ያወለቁበት መልካም አጋጣሚ ተፈጠሯል።

In short, it looks like the earth started shaking!

እዛ ሰፈር ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል! በመሆኑም ከፍተኛ ሩጫና ውር ውር በሚሉ ግሪሳዎች ማህበራዊ ሚዲያው ተጨናንቋል! እነዚህ ግሪሳዎች በጨለማ ውስጥ እውር ድንብራቸውን ወዳገኙበት አሁን ድረስ በመተኮስ ላይ ይገኛሉ።

አንደኛ

1. የተደረገውን ውይይት ድርድር እንደተደረገ አድርጎ ማደናገር

2. የዐማራ ፋኖ ትግል እንደተሸጠ እና የዐማራ ህዝብ እንደተካደ አድርጎ መሳል

3. አንድም የመንግስት ተወካይ ያልተገኘበትን ውይይት የመንግስት አካል እንደተገኘ አድርጎ መዘገብ

ሳያስበው ጉሮሮውን የታነቀው ስርዓት በዚህ ደረጃ አይኑን በጨው አጥቦ ቢዋሽ፣ አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ቢል አይገርምም። ብልፅግና ለዚህ ተግባር በከፍተኛ በጀት ያስፈረማቸው እንደ ዋዜማ ራድዮ፣ መሰረት ሚዲያ ፣ ሮሃ ሚዲያ፣ ABC ሚዲያ፣ መአዛ መሃመድ፣ “ረ/ፕ” ትንግርቱአብረሃም አንሙት እና ኤልያስ መሰረት ያሉ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች ጉዳዩን በተከፈለ‍ኣቸው ልክ እያስጮሁት ይገኛሉ።

ይህ የነገሩን ክብደት ያሳያል። ኤልያስ መሰረት ከዚህ ቀደም በኤርትራ መንግስት ላይ ባሰራጨው ሃሰተኛ ዜና ከአሶሼትድ ፕሬስ በቅሌት መባረሩ ይታወቃል። የተቀሩት ደግሞ ሃፍረተቢስ የብአዴን ወጣት ሊግ የነበሩ ተረፈ ብአዴን ናቸው።

ለመሆኑ የዐማራ ፋኖ ትግል በአለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እውቅና ማግኘቱ ምን ፋይዳ አለው?

1ኛ. በዐማራ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አለም አቀፍ እውቅና ያገኛሉ

2ኛ. የዐማራ ፋኖ ይዞት የተነሳው (የዐማራ ህዝብ ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ መታደግ) የሚለው cause አለም አቀፍ እውቅናና ተቀባይነት ያገኛል

3ኛ. በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና ተቋማት እንዲከሰሱና በአለማቀፍ ፍርድቤት እንዲዳኙ፣ በስርዓቱ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ፣ በስርዓቱ አገልጋዮች ላይ የጉዞ ማዕቀብ እንዲጣል ሰፊ መደላድል ይፈጥራል።

4ኛ. በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን የምግብ ፣ የመድሃኒት እና ቁሳቁስ ቀጥተኛ አለም አቀፍ ድጋፍ ያስገኛል።

5ኛ. የዐማራ ፋኖ ከድል በኋላ መንግስት የመሆን እድል ቢያጋጥመው በቀላሉ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና እና ድጋፍ ያገኛል።

ስለሆነም ይህን የመሰለ እግርህ እስኪቀጥን ብትዞር ፣ ድምፅህ እሰኪዘጋ በየኤምበሲ እና አለማቀፍ ድርጅቶች ደጃፍ ስትጮህ ብትውል፣ እንደወያኔ ደጋፊዎች መሬት ላይ ብትንከባለል የማታገኘውን ድል ለማንኳሰስ እና ለማጨናገፍ የዐማራ ጠላቶች እንቅልፍ አጥተው ቢራወጡ አይገርምም!

ነገር ግን በጣም የሚደንቀው እና አእምሮው የሚሰራ ሰው ሁሉ በቅንነት መጠየቅ ያለበት አንዳንድ “የዐማራ ህዝብ ታጋይ ነን” የሚሉ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ለምን በዚህ ደረጃ ታመሙ የሚለው ነው?

መቸም ፓለቲካን የመረዳት አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑትን መቀየም አይቻልም። ሌሎች ” ምሁር ነን” ፣ “ጋዜጠኛ ነን” ፣ “ተንታኝ ነን” የሚሉ ግለሰቦች ይህን መረዳት ለምን አቃታቸው?

አርበኛ እስክንድር ነጋ፣ እንዲሁም ፕ/ር ጌታ አስራደ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ዙሪያ ተደጋጋሚ በሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል። እነዚህ ግለሰቦች ለምን ከነዚህ ለዐማራ ህዝብ ሊሞቱ ከወጡት የጉዳዩ ባለቤቶች ይልቅ ሌሎችን ማመን መረጡ?

መልሱ መረዳት አቅቷቸው ሳይሆን ሆን ብለው ነው!

አንደኛውና ዋናው ጉዳይ የሰዎቹን አሁናዊ የፓለቲካ አሰላለፍ ያሳያል። ከዐማራ ህዝብ ትግል በተፃራሪ የቆሙ፣ በስም ዐማራ በግብር ለስርዓቱ የገበሩ ባንዳዎች በመሆናቸው ነው።

እነዚህ ግለሰቦች የኋላ ታሪክ/ track record ቢጠና ከዐማራ ህዝብ ጠላቶች ጋር በአንድም በሌላ ግንኙነት የነበራቸው እና ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን። አንዳንዶቹ ለአገዛዙ በከፍተኛ ገንዘብ የፈረሙ ባንዳዎች ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አንድ ሀሙስ ቀርቶት በጣር ላይ የሚገኘው የስደተኛው ብአዴን legacy አስቀጣዮች ተረፈ ብአዴን ሆነው እናገኛቸዋለን።

ብአዴን “ከክልሉ ውጭ ያለ ዐማራ የምንታገለው እንጂ የምንታገልለት አይደለም !” በሚለው ገራሚ እሳቤው ይታወቃል። የብአዴን ልጆች ዛሬም የዚህ አስተሳሰብ ሰለባዎች ናቸው። ለማሳያ የሣልሣይ ብአዴን አዋላጆች እስክንድር ነጋን፣ ሀብታሙ አያሌውንና ሌሎችንም ከዐማራ ክልል ውጭ የተወለዱ ዐማሮች እንደ ዐማራ ታጋይ ለመቀበል የሚቸገሩት ለዚህ መሆኑ ግልፅ ነው።

አሁን ባለው ሁኔታ የዐማራ ህዝብ ጠላቶች ያጠለቁት ጭምብል ከጊዜ ወደ ጊዜ በገዛ ተግባራቸው እየተገለጠ መጥቷል። በገዛ ዱላቸው ወገብ ወገባቸውን ተብለዋል። ተረባርበው ያሰራጩት የሃሰት መረጃ / Fake News እንደጉም ተኗል! ህዝቡም እየለያቸው፣ በሂደትም አንቀሮ እየተፋቸው ይገኛል። የቀሩትንም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እያጋለጡ ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ ስራ በስፋት ሊሰራ ይገባል።

በመጨረሻም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነገር የተገኘውን ድል እንዴት ከፍ ወደ አለ ስትራቴጄካዊ ጠቀሜታ ማሳደግ ይቻላል? የሚለው ነው!

1. ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዴት እንጠቀምበት?

2. እነዚህ ድርጅቶች ከአገዛዙ ጋር አደራዳሪ ሆነው እንዳይመጡ ምን ጥንቃቄ መደረግ አለበት?

3. ይህ ድል በብልፅግናና ተረፈ ብአዴን እንዳይጠለፍ ምን ይደረግ?

የሚሉት ጉዳዮች ላይ ማትኮር ያስፈልጋል!

ስትደራጅ፣ ድርጅት ሲኖርህ ጉልበት ትፈጥራለህ!

ጉልበት ሲኖርህ ትፈራለህ ፣ትከበራለህ፣ ትደመጣለህ! ይኸው ነው!

አሁንም ከዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ጋር ወደፊት!!!

 

@Dagmawit Getaneh, 

Filed in: Amharic