ታሪክ፣ ትውልድና ሀገር ይወቀው!!
እኛ የብልጽግናን ሰራዊት ስንፋለም ከጀርባችን በሕወሓት ተላላኪ “ፋኖ” ነን ባዮች ተወግተናል፤
የጦሩ ፊታውራሪ ተሰውቷል!! አዎ ታሪክ፣ ትውልድና ሀገር ይወቀው!!!
በአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ውስጥፈር ቀዳጅ የሆነውን ግዙፉን ክፍለ ጦር ይመራ የነበረው፣ የገብርየ ክፍለጦር ዋና አዛዥ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተቀዳሚ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ በሕወሓት ተላላኪ “ፋኖ” ነን ባዮች በሽምግልና ስም ከበባ በመፈጸም፣ ልብ በሚሰብር ክህደት ከጀርባ ተመቶ ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም. ተሰውቷል፡፡
በአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ውስጥ እጅግ ልብ የሚሰብር መራር ሐዘን ተፈጥሯል! ይህን እውነታ ታሪክ፣ትውልድና ሀገር እንዲያውቀው ዕዛችን በዚህ መግለጫ ዕውነታውን ይፋ አድርጓል!!
የጋሸናው ምሽግ ሰባሪ፣ የብልጽግና ሰራዊት አንበርካኪ፣ የአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶችን አሰጨናቂው ጀግና ታሪክ ይቅር በማይለው መልኩ ክህደት ተፈጽሞበታል፡፡
በብልጽግና የጦር ጀኔራሎች ቀይ ዞን ተብሎ የተከለለውን የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ሞዴል የሆነውን ሰፊ የውጊያ ቀጠና በጀግንነት ይመራ የነበረው ታላቁ የጦር ፊታውራሪ በከሃዲን ተወግቷል! ተወግቶምተሰውቷል፡፡
ይህ ክህደት በአማራ ትግል ውስጥ ትልቅ ጠባሳ እንደሆነ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ያምናል!!የጦሩ ፊታውራሪ ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ በሽምግልና ስም ከጀርባው የተወጋው ከሰሞኑ በሱዳን ከሚገኘው የሕወሓት ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ቡድን መሪ ከሆነው ጀኔራል ሙዘይ መኮንን ጋር ሁለት የፋኖመሪነን ባዮች ጋር ተገናኝተው ሴራ አሲረው፣ ተልዕኮ ተቀብለው መጡ ከሃዲያን ነው፡፡
እነዚህ ከሃዲያን በሽምግልና ስም ከዋና የጦር ማዘዣ ጣቢያ 150 ኪሎ ሜትር ተስቦ እንዲወጣ የተደረገውን መሪያችንን በላይ ጋይንት፣ ወለላ ባህር አጎና ከተማ ላይ ውጊያ ተከፍቶበት ከአርባ በላይ የሕወሓት ተላላኪ ፋኖ ነን ባይ ታጣቂዎችን በመደምሰስ፣ ከጀርባው ተመቶ ተሰውቷል፡፡
ይህን አቻ የማይገኝለት ክህደት፡- ታሪክ፣ ትውልድና ሀገር እንዲያውቅልን እንፈልጋለን!! የተካደው ጀግናው ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ አልያም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝና መላ ሰራዊቱ ብቻ አይደለም፡፡ የተካደው የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል ነው፡፡ የተካደው የሰማዕታት የትግል አደራም ነው፡፡ የተካደው የአማራ መጭው ትውልድ ጭምር ነው!!
በመሆኑም:-
1. መላው የዕዛችን ሰራዊት አባል፣ የድርጅታችን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ዕዞች፣ በየደረጃው ያላችሁ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አዛዦች፣ ከጠቅላይ መምሪያው እየወረዱ ያሉ ወታደራዊ ትዕዛዞችንእንድትቀበሉ ጓዳዊ ወንድማዊ የትግል መመሪያው ተላልፏል፤
2. በቀጥታም ይሑን በተዘዋዋሪ በዚህ የክህደት ተግባር የተሳተፉ አካላት ላይ ከሕዝባችን ጋር በመሆንአስፈላጊውን ወታደራዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፤
3. መላው ሕዝባችን የአማራን የኀልውና ትግል ለመጥለፍ የሚንቀሳቀሱ፣ ከብልጽግናና ከአማራ ታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ የተቀበሉ ከሃዲያንን ለይቶ በማወቅ ትግሉን ከጠላፊዎች እንዲጠብቅጥሪያችንን እናቀርባለን፤
4. በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የሐቀኛ የአማራ ፋኖ ትግል ደጋፊዎች የትግሉን ተኩላዎች ለይተው በመገንዘብ ወደፊት በሚወሰዱ ማንኛውም እርምጃዎች ላይ ግንዛቤ ኑሯቸው አስፈላጊውን ድጋፍእንዲያደርጉ ጥሪ እናደርጋለን፤
5. በአማራ የኀልውና ትግል ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ የባዕዳንና የጠላት ተላላኪዎች፣ የትግሉነጋዴዎች፣ የሥልጣን ጥመኞች፣ የብልጽግና ስልታዊ አጋሮችን፣ በተመለከተ ለመላው የአማራሕዝብና የትግላችን ደጋፊ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ያለውን ውስጣዊና ውጫዊ አሰላለፍ በቅርቡበማስረጃ ላይ የተመሰረተ ዝርዝር መግለጫ ይፋ እናደርጋለን!!
የሰማዕታት ደም በብርቱ ሠራዊታችን ተጋድሎ፤
- በሕዝባችን ደጀንነት በእጥፍ ይመለሳል!
- ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!!
- የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ