>

ከሕወሓት ጋር ለመስራት የወሰነውን አፈንጋጭ ቡድን ድምጽ በመሆን የተሰለፉ ጸረ - ኣምሓራዎች

ከሕወሓት ጋር ለመስራት የወሰነውን አፈንጋጭ ቡድን ድምጽ በመሆን የተሰለፉ ጸረ – ኣምሓራዎች

 

መሳይ፣ ግርማ ካሳ እና ዘመድኩን አማሮች አይደሉም። በአማራ ፖለቲካ ውስጥ በከፋፋይነት ሚናቸው ጠላቶቻንን ያስንቃሉ። ከእኛ ወገን ደፍሮ ከትግላችን ውጡ የሚለው ቁጥሩ አነስተኛ ስለሆነ በተደጋጋሚ ቢሸነፉም እንደ መዥገር ተጣብቀው በአማራ ህዝብ ኪሳራና ውድቀት የራሳቸውን የኃይማኖትና የብሔር አጀንዳ ለማሳካት እረፍት አጥተው ይሰራሉ።

ግርማ ካሳ በተዘዋዋሪ ከብልፅግና በሚያገኘው ገንዘብ የሳተላይት TV አቋቁሞ እና ኡጋንዳ የመሸገውን ሳልሳዊ ብአዴን በመጠቀም ፋኖ እርስ በእርስ እንዲዋጋ ለማድረግ በእየለቱ ይጮሃል። ያለማቋረጥ በፌስቡክና በተቆጣጠረው ሚዲያ የሸዋን ጀግኖች ብቻ ነጥሎ ይሳደባል፤ ያጥላላል። ሆኖም አርበኛ መከታው ማሞን እና አርበኛ እስክንድር ነጋን በዚህ ልክ ለምን እንደሚጠላ ግን አልገባንም። ግለሰቡ ሊያሳካ የሚፈልገውን ግብ መርምሮ ማወቅ የእኛ ግዴታ ነው።

መሳይ መኮንን ኢሳትን እና ግንቦት ሰባትን በመጠቀም አማራ በአማራነቱ መደራጀት የለበትም የሚል አቋም ይዞ ለብዙ ዓመት ዘመተ፤ እድሉንም ሞከረ። ግን ማስቆም አልቻለም። በደቡብና በጉራጌ ብቻ ይዘወር የነበረውን ግ7 የአማራ ለማስመሰል ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። አማራ በዚሀ “ኢትዮጵየዊ” ድርጅት ጥላ ስር መሰባሰብ አለበት የሚል ፕሮፓጋንዳ ቢሰራም በመጨረሻ የነቃው አማራ በተለይ ዳያስፖራው ባደረገው መጠነ ሰፊ የ cyber ትግል ፀረ-አማራውን ኢሳት አንኮታኮተው። ጋዜጠኞችም ቋንቋቸው ተደበላልቆ በየአቅጣጫው ተበታተኑ።

ግንቦት ሰባት ምንም አይነት constituent እንዳይኖረ አድርጎ ርቃኑን ያስቀረው አማራ ነበር። በዚህ የተደናገጠውና ተስፋ የቆረጠው ብርሃኑ ነጋ ጓዙን ጠቅልሎ ኦሮሙማ ጉያ ስር እንዲወሸቅ ተገደደ። መሳይ መኮንን ከብርሃኑ ነጋ ጋር አዲስ አበባ ከገባም በኋላ በሰውነቱ ውስጥ የቆሸሸ ፀረ-አማራ ደም ስላለ በድጋሚ አብይን ደግፎ አማራን በመቃወም ዘመቻ ከፈተ። ለሶስተኛ ጊዜ አማራ መሳይ መኮንንን ድባቅ መታው።

መሳይ ከአማራ ጋር መግጠም ከተራራ ጋር መጋጨት መሆኑ ስለገባው 360 ዲግሪ ዞሮና ተመሳስሎ የፋኖ ትግል ደጋፊ በመሆን ተከሰተ። ነገር ግን አሁንም ተኩላ ነው። የአፋህድ ሰዎች እርሱ ሚዲያ ሲቀርቡ እንደ ክህደት እቆጠረዋለሁ። መፈናፈኛ በማጣቱ እንጂ መሳይ አጋጣሚውን ካገኝ አማራን እንደሚታገል ሊሰመርበት ይገባል።

ግንቦት ሰባት በትግላችን ከመቀበሩ በፊት በአማራ ስም እንኳንና የታጠቀ ኃይል የዳያስፖራ ማህበር መመስረት አይፈቀድም ነበር። ነገር ግን ሁሉንም ደቁሰን ልክ አስገባነው። ዛሬ አማራ የአንድን አገር “መከላከያ” የሚደመስስ ኃይል ባለቤት ነው። ክብር ለእርሱ ይሁን።

ሶስቱ Anti Amhara and Non Amharas አሁንም ከአማራ ትክሻ ላይ አልወረዱም። አማራ በአማራነቱ እንዳይደራጅ ያደረጉት መጠነ ሰፊ ዘመቻ በሽንፈት ከተደመደመ በኋላ ሌላ ስትራቴጂ ነድፈዋል። ትኩረታቸውን ትግሉን ወደ ማኮላሸት አድርገዋል። እረኛውን ስትመታ በጎች ይበተናሉ የሚል መርህ አንግበው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እናውቃለን። አትሸውዱንም!! ግብራችሁን እንድ በአንድ መዘርዘር ለእኛ ቀላል ነው።

➖ሶስቱም ጠንካራ የአማራ መሪዎችን ለይተው ያጠቃሉ፣
➖ሶስቱም አማራ ጠንካራ መሪ እንዳይኖረው ጠንክረው ይሰራሉ፣
➖ሶስቱም ፋኖ አንድ እንዳይሆን በተጠና ሁኔታ አንደኛውን ወገን ብቻ በመደገፍ እርስ በእርስ እንዲታኮሱ በአደባባይ ይቀሰቅሳሉ፤ ይፅፋሉ።
➖ሶስቱም ከወያኔ እና ከብአዴን ጋር እንሰራለን ያሉ የፋኖ መሪ ነን ባዮችን ይንከባከባሉ። ትችት አያቀርቡባቸውም
➖ሶስቱም በአማራ ጥቅሞች ላይ የሚደራደር፣ ደካማና መኃይም የፋኖ መሪ ሲያገኙ ነፍሳቸው ሃሴት ታደርጋለች። On and on and on ..

@amaradamot 

Filed in: Amharic