ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ የሐዘን መግለጫ!
ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም
በዚህ ወቅት የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ጠላት ላይመለስ ግብዓተ መሬቱን እየፈፀምን በምንገኝበት ወቅት የጠላት የመጨረሻው ግብዓተ መሬት መፈፀም ያልተመቻቸው የጠላት አጀንዳ የሸከሙ ፖለቲካ አራማጆች ጠላት በደገሰበት ሁሉ የጭፈራ ኪነት ያቋቋሙ ዳንኪረኞች ከጠላት ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ ፈፅመው ወንድማችን አርበኛ ከፍያለው ደሴን በሽምግልና ሰበብ ከጀርባው ተወግቷል። ክሕደት ተፈፅሞበት ሰማዕት ሆኗል ።
እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው አባባል የአህያ ቢሆንም ለዛሬዉ እንድናስታውሳችሁ ተገደድን።
ዕለተ አርብ ሚያዝያ 3 ቀን 21017 ዓም በጥንታዊቷ የስልጣኔ መስራች የአፄ ፋሲል ሀገር ፣ አፄ ቴዎድሮስ ሱሪውን የለበሰባት የ፣ የባለክሩ እና ታማኝ ጦረኛ የገብርየ ትውልድ ቀዬ፣የሊቆች መፍለቂያ፣ የአድባራቱ መድመቂያ ፣የጦር ጠበብቶች ሰፈር በሆነችው ሀገረ ጎንደር የአባቱ የክርስቶስ ልጅ የሆነው ፣የሰው ልጆች በመስቀል ነፃ በወጣንበት ዕለት፣ በአብይ ፆም ወቅት ፣በኢድአልፈጥር ሰሞን፣በጁምዓው ቀን ለእውነት የወጣው ከፍያለው ደሴ በእውነተኛው ቀን የጠላትን ተልዕኮ በተሸከሙ ከሐዲዎች ትልቅ በአርበኛችን ላይ የክሕደት ታሪክ ተፃፈ።
የጦር ጠበብቱ መሪ የገብርየ ትንፋሽ፣የአፄ ቴዎድሮስ ውቅር የሆነው ሜጀር ጀነራል ከፍያለው ዛሬ በጥቁር ፋሽስቶች ተከድቷል። ነገር ግን ወንድማችን ሜጄር ጀነራል ከፍያለው ደሴ በጣም ወደ ከሚወዳቸው እና አደራ ወደ ተረከባቸው አባቶቹ ወደሆኑት አፄ ቴዎድሮስ እና ገብርየ ግዳጁን ተወጥቶ ተቀላቀለ እንጂ አልሞተም።
በመጨረሻም መላው የአማራ ህዝብ ሆይ አፄ ቴዎድሮስን ገድሎ እና አስገድሎ ሀገር የመራ ባንዳ እንደሌለ ሁሉ ከፍያለው ደሴን ገድሎ የአማራን ትግል መጎተት እንደማይቻል እያሳወቅን ሚስማር ሲመቱት እንደሚጠብቅ ሁሉ የአማራ ትግልም ይበልጥ አንድ ምዕራፍ በከፍያው መሰዋዕትነት እንደተጠበቀ ይቀጥላል። “ጅብ ከሚበላክ በልተኸው ተቀደስ” እንዲሉ ህወሀት እና ሳልሳዊ ብአዴንን ለማስወገድ በምናደርገው ዘመቻ መላው የአማራ ህዝብ እና ደጋፊዎቻችን እውቅና እንዲኖራችሁ ከወዲሁ እናሳውቃለን።
ጀግናን በልቶ ጀግና መፍጠር አይቻልም።
ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!
ሸዋ፤ አማራ፤ ኢትዮጵያ