የህወሀት እቅድና የዘመነ ኩባንያ ፍፃሜ!

እንደምን ሰነበታችሁ ሰሞኑን ትንሽ ጠፍቼ ነበር ።በሁለት ምክንያቶች ነው ።አንደኛው ለተከታታይ ጊዜ ባቀረብኳቸው ወደ 40 የሚጠጉ ማስታወሻዎች ምን ያህል የአማራ ፋኖና ደጋፊዎች ተጠቅመውበታል የሚል ዳሰሳ ለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የሱባኤ ጊዜ በመሆኑ ነው ።ዛሬም በብዙ መሰናክሎች መሃከል ብሆንም ከአማራ ህልውና ትግል የሚበልጥ ምንም ነገር ስለማይኖር አስቸኳይ መረጃዎችን ለእናንተ ለማጋራት ተከስቻለሁና ውሃ በብርጭቆ ፋት እያላችሁ ተከተሉኝ ?

ተመሰረትኩ ብሎ ከነገረን 90 ቀናትን ያስቆጠረውን በህወሃት መልካም ፈቃድ ስያሜውን ጭምር የተቸረው አፋብን የሚባለው የዘመነ ኩባንያ የአለቆቹን ፈቃድ ለማስፈፀም የአማራ ፋኖን አስተባብሮ ወደፊት ለመራመድ እግሩ ስለታሰረ ሳይቋቋም ወደ መጨንገፍ እያመራ ነው ።ይህ ስብስብ ከመመሥረቱ በፊትም ከተመሰረተ በኋላም አሳማኝ ምክንያቶችን እያነሳን ለአማራም ለራሱ ለዘመነ ካሴና አጋፋሪዎቹ ጭምር ለመምከር ሞክረናል ።ምንም እንኳን በአማራ ትግል መሐል ሆነው የህወሃት አገልጋዮች መሆናቸውን ብናውቅም በሂደት ራሳቸውን ፈትሸው ለህዝብ የሚበጅ ተግባር ይፈፅማሉ ተብለው ቢጠበቁም ከአማራ ህዝብ ፍጅት ይልቅ ደብረፂዮን ሲያስነጥሰው ቅንጥስ ያድርገን የሚሉት የዘመነ ቡድን አባላት በዚህ ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት ከጠቀስን የራሱን የስልጣን ጥማት ማርካትና በዘመናት መካከል የተገኘውን ሃቀኛ የአማራ ትግል መሪ በጅምላ ፈርጆ ከአመራር ቦታ ማራቅ እንዲሁም በብዙ ጀግኖች ወንድሞቻችን ደሞ የተመሰረተውን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን (አፋህድን) በማፍረስ ትግሉን ወደ ኋላ በማጓተት አማራውን የወያኔና አብይ አህመድ ተገዥ ለማድረግ መንገድ ማደላደል ሥራዎች ብቻ ናቸው ።እንዲህ ሳይወለድ ለሚጨነግፍ ንቅናቄና ከራስ ህዝብ ውስጥ እንኳን አብሮ ለመኖር ለማያስችል የጫካ ስልጣን በመስገብገብ የ70 ሚሊዮን አማራን የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል እንደ ኤሳው በምስር ወጥ ለመሸጥ መጋጋጥ ይህን የጨረቃ ንቅናቄ በማፍረስና ዘመነን ከአመራርነት በማባረር የሚቆም ሳይሆን ገና የታሪክ የህሊናና የፍትህ ተጠያቂነትም ያስከትላል ።ከህወሓት ቀጥተኛ ትዕዛዝ እየተቀበለ በአማራ ልጆች ደም ባህር ዳር ላይ ለመንገስ ያቆበቆበው ዘመነ ካሴ ሰሞኑን በተከናወነው ረዘም ያለ ስአት የፈጀ የንቅናቄው ስብሰባ ላይ የሚከተሉት ጉዳዬች እንዲፈፀሙ በአጀንዳነት አቅርቧል ።

1ኛ.በሁሉም ቦታ በዚህ የህልውና ትግል በተሰው አመራሮችና አርበኞች ስም የሚጠሩ የፋኖ አደረጃጀቶች በሙሉ መጠሪያቸው ወደ ቁጥር እንዲቀየ ር

2ኛ.በጠቅላይ ግዛት ስም የተሰየሙ በተለይም የነገስታትና መኳንንት መፍለቂያ ሆኖ በሚታወቀው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት መጠሪያ ላይ ህወሃት ደስተኛ ስላልሆነች የጠቅላይ ግዛቱ መጠሪያ በሙሉ እንዲሰረዝ የሚል

3ኛ.በየጠቅላይ ግዛቱ ያሉ የፋኖ ታጋዬችና የጦር መሪዎች በራሱ በዘመነ ካሴ በሰጠው ስምሪት መሰረት አካባቢያቸውን ለቀው ወደሚመደቡበት እንዲሄዱ

4ኛ.በፊት ለፊት ለመናገር ፈራ ተባ እያለም ቢሆን በየአካባቢው ባሉ ክፍለ ጦሮች መካከል የህወሃት ሰላዬች ስምሪት ወስደው የሚንቀሳቀሱ እንዲሆን (የዚህ ምደባ ዋና አላማው አንታዘዝም የሚሉትን ማስወገድ ነው) የሚሉትን ዋና ዋና አጀንዳዎች ለሥራ አስፈፃሚዎች ቀርቦ ሰፊ ክርክር ከተካሄደ በኋላ ስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ በእንጥልጥል ተበትኗል።የአብዛኞቹ ሥራ አስፈፃሚ አባላት አቋም ያልተመቸው ዘመነ ካሴ በስብሰባው ማብቂያ ላይ “በዚህ ካልተስማማን አፋብን ይፈርሳል “በማለት ለማስፈራራት ሞክሯል ።የዚህ አጀንዳ አፈፃፀም በሂደት የምናየው ቢሆንም በአጀንዳነት የቀረቡትን ሃሳቦች ስንፈትሽ የሚከተሉትን ቁም ነገሮች እናገኛለን ።

ሀ.ዘመነ የህወሃትን የወረራና የመገንጠል ጥያቄዎች ለማስፈፀም በእነ ሻለቃ ዳዊት አመቻችነት የተመደበ የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን አደባባይ ላይ ይዞት መከሰቱን

ለ.ህወሃት በአማራ ህዝብ በተለይም በሸዋ ህዝብ ላይ የያዘቸው የዘመናት ጠላትነት ገና ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥልና ከአብይ አህመድ ጋር በመናበብ ሸዋን ሊያጠፉ የተዘጋጁ መሆኑን
ሐ.የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የሚለውን ስያሜ ስቦ በማምጣት እንደ ሻለቃ መከታው ማሞ ያሉትን የሸዋ አርበኞች ከሰራዊቱ የመነጠል ሴራ መታቀዱን

መ.ዘመነ ካሴ የህወሃትን ተልዕኮ እንደ ጨረሰ ቢፈልግ በአብይ አህመድ ካልሆነም ቀደም ብሎ በውጪው አለም ወደገዛቸው ንብረቶቹ ሄዶ በሃብት እየተንደላቀቀ እንደሚኖር ቃል የተገባለት መሆኑን

ሠ.እውነተኛ የአማራ ፋኖዎች በአፋጣኝ አፋብን የሚባል ፀረ አማራ ሰብስብን በጊዜ በትኖ የራሱን መሪዎች ካልመደበ የአማራ ህዝብ ያለ ውክልና የኢትዮጵያ የሽግግር ስርዓት ሊከናወን እየተቃረበ መሆኑን

ረ.ህወሃትና የኦነግ ሃይሎች አማራውን መሪ አልባ ትግል ነው ብለው ራሳቸውን የፊት መሪ አድርገው ወደ ቤተመንግሥት በመግባት የመገንጠል ፍላጎታቸውን በሁለቱ ፀረ ኢትዬጲያ ሃይሎች ስምምነት ብቻ እንዲፈፀም ሰፊ የውጪ ዲፕሎማሲ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን

ሰ.የአማራ ትግል በዚህ ሁኔታ የሚጓተትና ዘመነ የተሰጠውን ሥራ ካልሰራ ህወሃትና ብልፅግና ፋኖን በጋራ ለመውጋትና ወልቃይትንም ራያንም ይዞ ወያኔ ከተገነጠለ የኦሮሞ ሃይሎች በስምምነት በስልጣን ላይ ለመቆየት እየተሰራ መሆኑን መረዳት ይገባል እላለሁ ።

ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ
ከአዳባይ
መጋቢት 16/2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.