ምስራቅ ተረፈ
ጠርተኸን መጥተን በጣልከው ድንኳን ፡
“ኢትዮጵያ “ስትል ሰምተንህ ረካን ፡
ከጨገግንበት በደስታ ፈካን ።
የጥሪ ካርድህ ዘርን አይጠቅስም፡
ፅፈህበታል “ኢትዮጵያዊ “ስም ።
አንድ ሁኑ ብለህ ጦማሩን ስትልክ ፡
ከተን ተገኘን እንደ ሚኒሊክ !!
ዐዕላፍ ወዳጅህ ከደጅህ ሲደርስ ሳይገፋፋ ፡
በትርምሱ በግርግሩ ሳይጠፋፋ፡
የግንባሩ ጌጥ ሳይቀረደድ ፡
እየሸመነ የፍቅር ገመድ፡
እንደለበሰ የወሉን ሸማ
ሰንደቁን ሰቅሎ በልቡ ማማ
ሲያረግድ አመሸ በራስ ከተማ
ስሟን ስንጠራት ረቦ መንፈሷ
መሀከላችን ተገኝታ ነበር “ኢትዮጵያ “ራሷ!
የታል አትበሉ መናኸሪያችን?
የታል አትበሉ አደባባዩ?
እየታዘዙ አየር ሰማዩ !!!



















