ዳስ ጣል ልቤ አንሳው
አይኖች ሁሉ ወደ ቴዲ አፍሮ
የእውቁ አርቲስት የፍቅር፣ የአንድነት፣ የኢትዮጲያዊነት እና የፍርሃዊ እኩልነት ስድስተኛ አልበም – የጨለማው ጌታ የሆነውን ስድስተኛውን መንፈስ አስቆጥቶ እያወራጨ ነው‼️
ዳስ ጣል ልቤ(አንሳው) የኢትዮጲያን ስምንት የመከራ ዘመንን በስምንት ደቂቃ ከሽኖ ያቀረበበት ድንቅ ስራ ‼️
አርቲስቱ የፋሺስቱ ኢላማ ሆናል፣ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብና መላው የኢትዮጲያ ሕዝብ አይኖች ሁሉ ወደ አርቲስቱ ያተኩሩ‼️‼️‼️
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
……………ዳስ ጣል ልቤ ፣ ዳስጣል
ከዚህ በላይ ሀዘን ከዚህ በላይ መርዶ ከወዴት ይመጣል።
ፍቅርን ብየ እንጂ ተግቼ ለሰላም እኔስ መታገሴ
መች ከሀገር ይበልጣል እኔስ አንድ ነፍሴ።
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን
ምጥ አታስተምር ልጅ እናቷን!
ወይድ አታስቆጥረኝ ማንነቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ደም አጥንቴን!
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን‼️
ባንዲራየን‼️
አንሳው‼️
ባንዲራየን አንሳው‼️‼️‼️
📌 በአምስት ቀን ብቻ ከ 75.000.000 አድማጭ ጆሮን መማረክ የቻለ በታሪክ በኢትዮጲያ ብቻ ሳይሆን በድፍን አፍሪካ ብቸኛ እና የመጀመሪያ የሆነው #ኢቶሪካአልባም
ትናንት ከሃያ አመት በፊት በጃ- ያስተሰርያል ዘመንና ትውልድ ተሻጋሪ ድንቅ የጥበብ ስራው ጥበብ፣ ፍቅር፣ እውነት፣ ፍትህ፣ ኢትዮጲያዊነት እና ፍትሃዊ እኩልነትን አፍኖ የነበረው የወቅቱ ህወሃት መራሹን ኢሕአዴግ ቃጭል አጥልቃ የደነበረች በቅሎ ድንጉጥና ደንባራ ያደረገውን ያህል ዛሬም ከስምንት አመት በኃላ ይዞት በመጣው ኢቶሪካ አልባ የመላውን ኢትዮጲያዊ አንጀት አርስ ሆኖ በተወዳጅነት እየተደመጠ የመሆኑን ያህል በባሌም ሆነም ሆነ በቦሌ ብለው በስልጣን ማማ ላይ ፊጥ ያሉ የዘመናችን ገዢዎች ግን የወደዱለት ሳይሆን እጅግ የተናደዱበትና በድንጋጤ ድንብርብራቸው የወጣበት ድንቅ አልበም ሆኖ ተከስታል።
አስራ ስምንት ነጠላ ዘፈኖችን ያቀፈው ኢቶሪካ አልበም ከይዘቱ እስከ አቀራረቡ እጅግ ታሪካዊና ልዩ አልበም ሆኖ ተመዝግባል። አይደለም በኢትዮጲያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ይቅርና በአፍሪካ የሙዚቃ ኢንደስተሪ ታሪክ ውስጥ በአንድ ግዜ 18 ነጠላ ዜማዎችን
📌የግጥሙ ደራሲ
📌የዜማ ደራሴ
📌በድምጽ አቅራቢ አንድ በሆነ አርቲስት ተቀናብሮ ለሕዝብ በመቅረብ እና በአምስት ቀን ቆይታ ብቻ ከ 75.000.000 በላይ የአድማጭን ጆሮ መማረክ የቻለ በታሪክ ብቸኛው አርቲስት ኢትዮጲያዊው የሙዚቃ ንጉስ እውቁ አርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ብቻ እና ብቻ ነው።
የኢትዮጲያዊያኑ 2018 ዓ ም በገባ በ8ኛው ወር – በ8ኛው ቀን በ8ኛው ሰዓት ላይ ከስምንት ዓመት በኃላ የተለቀቀው የቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ አልባም ከኢትቶጲያና ከአፍሪካም ወጥቶ በአለም የሙዚቃ ቻርት (Billboard) ላይ በዳስ ጣል ልቤ የአንደኛነትን ደረጃ የያዘ ተደማጭ ሙዚቃ ከመሆኑም በላይ በቲክቶክ፣ ፌስ ቡክ፣ ቲዊተር (X) Main stream Media እና በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በፈረንጁ፣ በአረቡ፣ በጥቁር አፍሪካዊው፣በኤርትራዊው፣ በሱማሊያዊው፣ በኬኒያዊው፣ በሱዳናዊው እና በድፍን ኢትዮጲያዊው ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆን የቻለ አለበም ነው የሆነው።ዝበኢትዮጲያ የቀድሞ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና የኢትዮጲያን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት አምባሳደት ቲቦር ናዤ ስለአርቲስቱ ኢቶሪካ አልበም ሲናገሩ አርቲስት ቴዲ አፍሮን “ስሙት” ~በማለት ጥሪ ካስተላለፉ በኃላ “…ሙዚቀኞች ከጋዜጠኞችና ከባለሙያዎች ይልቅ እውነትን ለመናገር ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው…” ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
አምባሳደሩ አያይዘውም “…ወደዱትም ጠሉትም፣ ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንደ ችግር የሚመለከታቸውን ጉዳዮች በዘፈን ለመግለጽ ያሳየው ዝግጁነትና ድፍረት አድናቆት ይገባዋል፣ እና ስሙት!” በማለት አልበሙን አድማጭ ያደምጠው ዘንድ ጋብዘዋል።
የአምባሳደር ቲቦር ናዤ አስተያየት አርቲስት ቴዲ አፍሮ ለሕዝብ ጆሮ ያበቃው ሙዚቃ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መልዕክት ወደ ሀገራዊና አለማቀፋዊ የውይይት መድረኮች መድረሱን የሚያሳይ ሲሆን BBC,DW Al-Jazeera እና መሰል ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቃማት ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።
18 ሙዚቃዎችን ያቀፈው ኢቶሪካ አልበም ውስጥ ዳስ ጣል ልቤ /አንሳ) የሚለው ባለ ስምንት ደቂቃ ሙዚቃ የአቢይ መራሹን የብልጽግናን ስምንት የመከራን ዘመን በውብ ስንኞቹና ውብ የጥበባዊ የዜማ ስራ ለሕዝብ ጆሮ ያበቃው ስራ በመሆኑ ከ18ቱ ውስጥ ከፍተኛ አድማጭ በማግኘት አንደኛ ሆናል። እስካሁን ዳስ ጣል ልቤን( አንሳው) ከ 13.000.000 በላይ አድማጭ ጆሮን መማረክ የቻለ ሲሆን ይዘቱም ጎጠኝነት ነግሶ የኢትዪጲያዊነት መገፋት፣ አያት ቅድመ አያቶቻችን ድምና አጥንት ገብረው፣ ምትክ የለሽ ብርቅዬ ህይወታቸውን ሰውተው ያወረሱንና ያቆዩልንን ኢትዮጲያን፣ ኢትዮጲያዊነት እና አረንጋዴ ፣ቢጫ ፣ቀይ ክቡር ሰንደቅ አላማችን በዚህ ስምንት አመት የደረሰባቸውን አሰቃቂ መገፋትን አርቲስቱ ፍንትው አድርጎ የገለጸበት ነው።
ዳስ ጣል ልቤ – አዲስ አበባ እና አዲስ አበቤያዊ የደረሰባቸውን ስርአት ተኮር በደልን በውብ ስንኞች እና በድንቅ ዜማ እያዋዛ የገለጸበት የሀገረ ኢትዮጲያ ህልውና ላይ የተጋረጠውን የመፍረስ አደጋን በማሳየት ትውልዱን ሀገርህን ታድን ዘንድ ተነስ፣ አንሳው፣ ባንዲራህን ሰንደቅህን፣ አርማህን አንሳ እያለ ታላቅ ጥሪ ያቀረበበት ድንቅ የጥበብ ስራ ሆኖ ነው ያየሁት ።
በዳስ ጣል ልቤ አርቲስቱ ስለ ኢትዮጲያ ፣ ስለገጠማት አደጋ ገልጾ ጥሪ ሲያስተላልፍ
“……የኢትዮጵያ አርበኞች የጥንት አርበኞች እነ አናብስቱ
ሲረገጥ ባንዲራው ገና አሁን ሞቱ።
ካለበታው ሲሆን ወርቅ አይደለም ዝምታ ለበግም አልበጃት
አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት……” በማለት ዝምታ ለማንም እንደማይበጅ በመግለጽ አንሳ፣ ተነሳ እያለ ትውልዱን ሞግታል።
ከዳስ ጣል ልቤ ጎን ለጎን እንደ የአዞ እንባ፣ መሬማ፣ ጀምበር፣ የጺዮን ሙሺራ እና መሰል የሆኑ እጅግ በሳል ሀገራዊነት፣ ኢትዮጲያዊነት፣ ፍትህ፣ ሀገራዊ ፍቅር በተዋቡ ድንቅ ስንኞችና ዜማ ያቀረበባቸው ድንቅ ስራዎችንም በኢቶሪካ አልበሙ አካቶ ያቀረበ ሲሆን በዚህ ድንቅ የሙዚቃ ስራ አሸናፊ ሆኖ የወጣው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ሳይሆን የማትሸነፋዋ ሀገረ ኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያዊነት አሸናፊ ሆነው ተከስተዋል ብሎ ነው ይህ ጸሀፊ የሚያምነው።
አርቲስት ቴዲ አፍሮ በኢትዮጲያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ኢትዮጲያንና ኢትዮጲያዊነትን በማቀንቀን በዚህ ትውልድ አቻ ያለው አርቲስት አይደለም። ለሁለት ድፍን አስርተ አመታት ያህል አንዳችም አይነት የአቃም እና የስሜት መዋዠቅ ሳያሳይ ከግርማዊነቶ እስከ የዛሬው ዳስ ጣል ልቤ ስድስት አልበሞች ውስጥ በተዋበ ግጥምና ዜማ እየተሞሽሩ ለአድማጭ ጆሮ የደረሱት ኢትዮጲያ፣ ኢትዮጲያዊነት፣ ኢትዮጲያዊ አንድነት፣ ፍትሃዊ እኩልነት፣ የሰንደቅ አላማን ክቡርነትን ከፍቅር፣ ከውበት፣ ከታሪክ፣ ከእምነት፣ ከማህበራዊ ህይወት እና ብሎም ከአፍሪካዊነት ጋር እያሰባጠረ በማቅረብ በሙዚቃ የክብር ማማ ላይ ከፍ ብሎ በስራው መቀመጥ የቻለ ድንቅ አርቲስት ነው።
📌 አይኖቹ ሁሉ ወደ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ይመልከቱ‼️‼️‼️
ጃ- ያስተሰርያል- ዳግመኛ በዳስ ጣል ልቤ እንዳይደገም መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ እና መላው የኢትዮጲያ ሕዝብ አይኖቹን በአርቲስቱ ላይ ያድርግ፣ እግሮቹንም ወደ አርቲስቱ ቤት ያንቀሳቅስ እንቁአችንንን እኛ ካልጠበቅን ማንም አይጠብቅልንም ‼️‼️‼️
ኢቶሪካ አልበም በወጣ በአምስተኛው ቀን ከ75 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ጆሮ ማግኘት የመቻሉ ሀቅ የሚደሰት የመኖርይን ያህል እጅግ ጥቂትም ቢሆን የሚከፋ እና እጅግም የተከፋ የለም ማለት አይደለም አይደለም።
አቢይ መራሹ የብልጽግና ስርዓት እጅግ ከተከፉት ጥቂቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛ ሆኖ ብቅ ብላል። ይህ እጅግ አናሳ ቡድን ግን ስልጣን ላይ ተፈናጦ ያለው የብልጽግናው ገዢ አመራር ቡድን በአርቲስቱ ዳስ ጣል ልቤ ( ባንዲራውን አንሳው) ድንቅ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃ ከብዙሃን በተቃራነ መልኩ እጅግ ደንግጦ በንዴት ጦፋል።
መሳሪያ ታጥቆ ስልጣን ላይ ፊጥ ያለው አናሳው ገዢ ቡድን ተደናግጦ ሲደናበር የሚወስደው እርምጃ በዚህ ስምንት የመከራ ዘመን እንዳየነው ያስደነበሩትን ንጹሃንን ማሰር፣ ማሳደድ፣ ማፈን፣ በየእስር ቤቱ ማጎር፣ ማፈናቀል፣ በተናጥልና በጅምል መግደልና መጨፍጨፍን ስራዬ ብሎ መፈጸም ሆናል።
ኢቶሪካ አልበም ተለቆ ዳስ ጣል ሌቤ በተደመጠ ማግስት የዚህ ስርአት ቁንጮ አቢይ አህመድ ምኒስትሮቹንና ካድሬዎቹን ሰብስቦ “…. ብልጽግና በዘፈን ጫጫታና ግርግርታ ፈጽሞ አይደናቀፍም …” በማለት ደም ስሩ ተገታትሮ አይኖቹን እያጉረጠረጠ ተናገረ። አያይዞም “… ብልጽግናን በዘፈንና በጫጫታ አደናቅፋለሁ የሚል ካለ ባለን ልምድ በመጠቀም እንቅፋታችንን እንደ ጉቶ ነቅለን በመጣል ወደፊት እንቀጥላለን እንጂ የሚያደናቅፈን ፈጽሞ አይኖርም..” በማለት ዛተ። ለጥቆም ሙዚቃው በወጣ በሁለተኛና ሶስተኛ ቀን ለካድሬዎቹ ባስተላለፈው ቀጭን ትእዛዝ በአርቲስቱና በአልበሙ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፍቱ አደረገ። ኢቶሪካን አልበም የሚያደምጡትንም በአሸባሪነት ክስ እያፈሰ ከ156 በላይ አዲስ አቤቤያዊን እያፈነና እያፈሰ በየፖሊስ ጣቢያው ማጎር ጀመረ።
አልበሙ በወጣ በአራተኛው ቀን የዚህ ስርአት ቁንጮ የሆነው አቢይ አህመድ ብቅ አለን “….እኛ ንስሮች ነን፣ ሌሎች የሚጮህ ቁራዎች ናቸው . ናቸው ….” በማለት የስብእና ገደላውን ዘመቻ ይበልጥ ያሳልጥ ቀጠል። ይህንን የስብእና ገደላውን ዘመቻ በተናገረ ማግስት ኢቶሪካ አልበም በወጣ በአምስተኛው ቀን ዛሬ በእለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 11 ቀን 2026 ላይ የአርቲስት ቴዲ አፍሮ ቃለ አቀባይ እና ምክትል ማናጀር ማህሌት ሰለሞንን እና የአርቲስቱ ለብዙ አመታት የቅርብ ወዳጅ የሆነውን አቶ ዮሱፍን ከየቤታቸው በፌዴራል ፖሊስ እየደበደበ እንዲታሰሩ አደረገ።
ለእነዚህ ሁለት ኢትዮጲያዊያን በፌዴራል ፖሊስ እየተደበደቡ ለመታሰር ያጠፉት ጥፋት የአምስት ልጆች እናት የሆነቺው ወ/ሮ ማህሌት ሰለሞን የአውቁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ቃለ አቀባይ እና ምክትል ማናጀር መሆን ሲሆን ለአቶ ዮሱፍ ደግሞ እጅግ ለረዥም ግዜ የአርቲስቱ የቅርብ Close Friend ጋደኛ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው እንደ ጥፋት ተቆጥሮ በፌዴራል ፖሊስ እየተደበደቡ እንዲታሰሩ ያደረጋቸው።
ይህንን ድርጊት ይበልጥ ስንፈታው ኢቶሪካን ለምን አዳመጣችሁ ተብለው የታፈሱት ከ156 በላይ ወጣቶችም ሆነ የእነ ማህሌት እና ዮሱፍ እየተደበደቡ መታሰር – የቴዲ አፍሮ እየተደበደበ መታሰር ሆኖ ነው የምናየው። ምክንያቱም አርቲስቱ ኢቶሪካን አልባም ባያወጣ እነዚህ ሰዎች ሰለባ አይሆኑም ነበር። ይህንን የአቢይን ዘመቻን ትርጉም አንድ ደረጃ ከፍ አድርገን ስንመለከተው የዘመቻው ዋና ኢላማ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ሆኖ ቢታየንም የዘመቻው ኢላማ ግን ኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነት፣ አዲስ አበባ እና አዲስ አበቤያዊነት፣ ፍትህ እና ፍርሃዊ እኩልነት ላይ የተዘመተ የጸረ ኢትዮጲያ ቡድን ዘመቻ ሆኖ ነው ቁልጭ ብሎ የሚታየን።
የዚህ ስርዓት ቁንጮ የሆነው አቢይ አህመድ “…… የብልጽግናን ጉዞ በዘፈንና በጫጫታ ለማደናቀፍ የሚያስብ ካለ እንደ ጉቶ እየነቀልን እንቀጥላለን …..” ብሎ ሲዝምት ለስልጣኔ ብዬ እንደነ ሀጫሉ ሁንዴሳ፣ ኢንጀር ስመኘው በቀለ፣ ጄ/ል ሰአረ መኮንን፣ ጄ/ል አሳምነው ጽሄ፣ ዶ/ር አምባቸው፣ መሰል ታዋቂ ሰዎችን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ ተወላጆችን እንደገደልኩና እንደጨፈጨፍኩ አርቲስት ቴዲ አፍሮንም ከመግደል ወደ ሃላ አልልም እያለ በግልጽ እየነገረን መሆኑን መረዳትና ማመን ይገባል።
እኔ ከተወለድኩበት የኦሮሞ ብሄር የተወለደውን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ቀርጥፎ የበላ አረመኔ አገዛዝ ዛሬ ገድያታለሁ ብሎ ያሰበውን ኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን በቅጽፈት አንሰራርቶ አሸናፊነቱን ያሳየን አርቲስት ቴዲ አፍሮን ይሳሳለታል ብሎ ማሰብ እጅግ ቂልነትና ሞኝነት ነው የሚሆነው። ይህ ስለሆነም ነው ከሃያ አመት በፊት ህወሃት መራሹ የኢሕአዴግ ስርዓት በ ጃ- ያስተሰርያል ዘፈን ምክንያት በአርቲስቱ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ዛሬ ከሀያ አመት በሃላ የህወሃት ወራሽ በሆነው የኦህዴድ መራሹ የብልጽግና ስርዓት በአርቲስቱ ላይ ዳግመኛ እንዳይፈጸም እንደ ሕዝብ ልንነሳ እና አርቲስቱን ልንጠብ ይገባል ከማለት የቻልኩት።
ያበደ ውሻ ማንንም ይነክሳል። እራሱን መከላከል የማይችልንና ያገኘውን ሁሉ ያበደ ውሻ ይነክሳል። ብልጽግና እንካን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ እንደሚባለው በፊትም በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልል በተነሳበት የቅቡልነት እጦት ችግር ላይ መሀል አዲስ አበባ ላይ ዳስ ጣል ልቤን በዚህ የጨበራ ምርጫ ድራማ ዋዜማ ላይ መስማት ያገኘውን እና የሚችለውን ሁሉ ተናካች ፍጹም ያበደ ውሻ እንዲሆን አድርጎታል። የዚህ ስርአት የጉልበት አቅም ሕዝብ፣ ሕግ ፣ ጥበብ እና ማስተዋል ሳይሆን መሳሪያ፣ ኃይል፣ጉልበት እና መሀይማዊ የስልጣን መመሪያ እንደመሆኑ መጠን የኃይልና የጉልበትን አቅም ከሰፊው ሕዝብ ጉልበትና አቅም አንጻር ስንመዝነው ባዶ የሆነ ያህል በማይመጣን ደረጃ ላይ ያለ ሆኖ ነው የምናየው።
ስለሆነም የቱንም ያህል እስከ አፍንጫው የታጣቀ አፋኝ ስርአት ሕዝብን አሸንፎ የማያውቅ እንደመሆኑ መጠን መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ እና ብሎም መላው የኢትዮጲያ ሕዝብ በጋራ በመነሳት የአርቲስቱን ደህንነትና ህልውናን መጠበቅ መቻል ብቻ ሳይሆን ይህንን ፋሺስታዊን ስርዓት ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ማስወገድ የሚችል መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ላስተላለፍ እወዳለሁ።አበቃሁ‼️‼️‼️
አይኖቹ ሁሉ ወደ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ቤት ይመልከቱ‼️‼️
እግሮች ሁሉ ወደ አርቲስቱ ቤቱ ያምሩ‼️
ልቦች ሁሉ ስለአርቲስት ቴዲ አፍሮ ያስቡ‼️
ለፋሺስቱ አምባገነን ፈጽሞ የአፈና እድል አንስጠው ‼️‼️



















