>
5:13 pm - Monday April 19, 9790

አሜሪካ በቀዩ ምንጣፍ ላይ እንደገና እንድትከበር ትፈልጋለችን?[ ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም] 

 ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Obama Receptionየዶናልድ ትሩምፕ (ያሜሪካ ፕሬዚደንት ዕቹለመሆን ተወዳዳሪያነጋገር ዘይቤ እንዲህ የሚልነው፡አሜሪካ ንደገና ለመከበር ትፈልጋለች፣ምክንያቱም ቀሪው የዓለም ክፍል አሜሪካንንማክበሩን ትቷልና ፡፡

ስለዶናልድ እኔ ጉዳዬ አይደለም፡

ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ሲጎበኝ የመጀመሪያየሆነው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማባለፈው ወር ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት በቀይምንጣፉ ላይ የተደረገለትን ክብር የጎደለውአቀባበል አስመልክቶ ዶናልድ ትሩምፔትየተናገረው የአነጋገር ዘይቤ በአምሮዬ ውስጥአቃጨለ፡፡

የክብር መገለጫ የሆነው የቀይ ምንጣፍ ተውኔት እና እርባናቢስነት ከነገሮች እይታ አንጻር ትልቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖምግን ለአንድ ሉዓላዊ ለሆነ ሀገር ቁጥር አንድ የመንግስት ኃላፊ የሀገሩን/ሯን ክብር የሚገልጽ ጉዳይ ስለሆነ ነገሩ እንዲህበቀላሉ የሚታይ እና የሚታለፍ አይደለም፡፡

ቀደም ሲል እንዳልኩት ሁሉ እኔ ከፍተኛ ለሆነ የአቀባበል ዝግጅት በዓል እና ለአጋጣሚዎች ቸበርቻቻ ለሆነ የአቀባብልስነስርዓት ብዙም ትኩረት አልሰጥም፡፡ ሆኖም ግን እኔ የማስተምርበት ዩኒቨርሲቲ የምረቃ በዓል በሚያዘጋጅበት ጊዜየዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ባለስልጣን እጅግ በጣም የተዋበ እና ያጌጠ የፕሮፌሰር የመጎናጸፊያ ልብስ በመልበስ እንዲሁምበጭንቅላት ላይ የሚደፋውን የዩኒቨርሲቲውን መለዮ እያደረጉ ክብረ በዓላትን ሲያከናውኑ ተሳትፈአለሁ፡፡  

መደበኛ የሆኑ የክበር ዝግጅቶች መደረ ጠቀሜታ ይገባኛል፣ ሆኖም ግን ሲደረጉ እጅግ በጣም ባማረ እና በተዋበ የዝግጅትሁኔታ መሆን አለባቸው፡፡

.. ባለፈው ሀምሌ ወር ሁለተኛው አጋማሽ ላይ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራውወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያደረገው የአቀባብል ስነስርዓት እጅግ በጣም የወረደ እናየዩናይትድ ስቴትን የፕሬዚዳንቱን ቢሮ እና መላውን የአሜሪካንን ህዝብ የዘለፈ እና ያዋረደ አሳፋሪ ድርጊት እንደነበርእምነት አለኝ፡፡

ለዓለም ህዝብ ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ተጠሪ እና በጣም ጠቃሚ እና ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ የዩናይትድ ስቴትአሜሪካ ህዝብ ተወካይ ነው፡፡ ስለሆነም መንግስቱን ወክሎ ጉብኝት በሚያደርግበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ክብር ሊደረግለትይገባል፡፡ 

ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊመጥን የማይችል እንዲያውም ብልህነት የጎደለውእና የመድረክ ላይ አስቂኝ አቀባበል የተውኔት ጨዋታ አካሂዷል!

ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ለአባማ እንደዚያ ያለ ክብርን ያጎደፈ አቀባበል ለምን እንዳደረገ ሲታሰብ ህሊናንየሚበጠብጥ ጉዳይ ነው፡፡

ኦባማ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ እየሰበሰበ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ከፍተኛውን የገንዘብ እርዳታየሚሰጥ ሰው ነው፡፡

ኦባማ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ እያፈሰ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) በማጀል በሙስና የነቀዘውን እና የበከተውን እንዲሁም በወንጀል የተዘፈቁ ድርጆቶቹን በገንዘብ ይደግፋል፡፡

ኦባማ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በሰው ልጆች ላይ እየፈጸማቸው ያሉትን ኢሰብዓዊ ወንጀሎች አይቶእንዳላዬ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ፣ መናገር እየቻለ መናገር እንደማይችል ዱዳ በመሆን ዝም ብሎ የተቀመጠ መሪ ነው፡፡

ኦባማ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እውቅና ለመስጠት እና ሕጋዊነትን ለማላበስ ሲል እስከ ጥርሱ ያገጠጠውሽት እና ቅጥፈትን በማራመድ ላይ ያለ መሪ ነው፡፡ ከዚህም አልፎ ኦባማ የእብሪተኝነት ድፍረትን በተላበሰ መልኩ አሁንባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) መቶ በመቶ በማሸነፍዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ድልን ተቀዳጅቷል በማለት የሸፍጥ የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ የወፍ ምስክሯ ድንቢጥእንዲሉ፡፡

የኦባማ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆነችው ቅብጥብቷ ሱሳን ራይስ ለአባባሉ ከፍተኛ ግነት በመስጠት ፕሬዚዳንቱህወሀትፍጹም በሆነ መልኩ መቶ በመቶ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ድልን ተቀዳጅቷልብለዋል የሚል ጋዜጣዊመግለጫ ሰጥታለች፡፡ ከዚያም በኋላ ራይስ ስሜቷን ልትቆጣጠረው በማትችለው መልኩ በሳቅ ፈንድታለች! ኦባማ ይህንየመሰለ ውለታ እና ወገንተኝነትን ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ያደረገው ምን ትርፍ ለማግኘት ነው? ሌላምንም ነገር ሳይሆን ክብርን የማጣት ውርደት!

በምላሹ አሜሪካ ምን አገኘች? ክብርን የማጣት ውርደት!

በላስ ቬጋስ ከተማ ብዙም እርባና ለሌላቸው ቁማርተኞች ፕሬዚዳንት ኦባማ በአዲስ አበባ ላይ ከተደረገለት የአቀባበልመስተንግዶ የበለጠ ክብር ይሰጣቸዋል፡፡

የቀይ ምንጣፍ አቀባበልማለት የእራሱ የሆነ ልዩ መገለጫ ትርጉም እና ምልክት አለው፡፡ ለዚህም ነው ጠቃሚ የሆኑየመንግስታት እና ሌሎች ይፋ የሆኑ ጉዳዮች ጉብኝቶች በሚደረጉበት ጊዜ ብዙውን ጊዜ ቀይ ምንጣፍ በማንጠፍ የአቀባበልስነስርዓት የማድረግ እና የክብር ዘብ በማቆም አቀባበል የሚደረገው፡፡ ልዩ የሆነ የአለባበስ እና የበዓል ዝግጅት በማድረግለክብር ተብሎ በተነጠፈው ቀይ ምንጣፍ ላይ በችኮላ እና በጥድፊያ ሳይሆን ርጋታን የተላበሰ አረማመድ በማድረግ ዓለምክብር እና ፍቅር ለመስጠት ላሰበችው ህዝብ ሀገር ተወካይ ትሰጣለች፡፡ የሚደረገው ለጉብኝት እንግዳውን ለላከውህዝብ ክብር ሲባል ነው፡፡

ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ ታላቁን እንግዳ የመቀበል ስነስርኣት ባህል እና ትርጉም ከጥንት ታሪክ ጀምሮ የነበረ ነው፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት 458 ዓመተ ዓለም አጋመምነን የተባለው ጦረኛ ከትሮጅን ጦርነት በሚመለስበት ጊዜዝሙተኛና በባሏ ላይ የሚባልግ ሚስቱ ክሊተምነስትራ የክብር አቀባበል ለማስመሰል ቀይ ምንጣፍ አንድዘረጋለጥ አዛነበር፡፡  

ሆኖም ግን አጋመምነን ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ምንጣፍ የሚነጠፈው ለአማልዕክት እንጅ ለእኔ አይደለም በማለትበምንጣፉ ላይ በመራመዱ ሁኔታ ላይ አመነታ፡፡

የእኛዎቹ ዘመነኞቹ መላዕክትፕሬዚዳንቶች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የመንግስታት ተወካዮችማንኛውንም የአቀባበልክብረ በዓል ዝግጅት ለማድረግ ያንን የጥንቱን ባህል በማሰብ በቀይ ምንጣፍ ላይ በመራመድ እነርሱም መላዕክትመሆናቸውን እና እነርሱን ሞት የማይነካቸው ፍጡሮች እንደሆኑ አድርገው በመቁጠር እንድንገነዘብላቸው እና የእኛተግባር እነርሱን ማክበር፣ ወይም ደግሞ ከልባችን እንድናመልካቸው ይፈልጋሉ፡፡

ኦባማ በምድር ላይ ያለ አንድአምላክ” ቢያንስ በግሪክ የግንጋይ አማልዕከት ደረጃ ሊታይ የሚቺል ሰው ነው።ስለዚህም ትክክለኛ የሆነው የቀይ ምንጣፍ የአነጣጠፍ ስነስርዓት ሊከናወንለት እንደሚገባ አምናለሁ፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኦባማን እጅ ለእጅ በመያያዝ ልጆች እየዘመሩበሚሄዱበት የህጻናት ጨዋታ ዓይነት ቀይ ምንጣፍ ነገር ላይ እንዲሸከረከር ሄድ በመደረጉ ክስተት ላይ በጣም ደንግጨነበር፡፡

ኦባማን በባለ አራት ማዕዘን በተሰራ መረማመጃ ላይ እንደ ፐርሻ ምንጣፍ ተመሳሳይ ሆኖ በተዘጋጀው ምንጣፍ ላይ ዋናመረማመጃ በማድረግ ለክብሩ ሲባል እንዲራመድበት አድርገዋል፡፡

ኦባማ ከቆመበት ወደ ግራ አቅጣጫ 8 እርምጃዎችን እንዲራመድ ተደርጓል፡፡ ከዚያም ወደ ቀኝ በመታጠፍ 12እርምጃዎችን ተራምዷል፣ እንደገናም ወደ ቀኝ ሌሎች 15 እርምጃዎችን ተራምዷል፣ በመቀጠልም 11 እርምጃዎችን ወደቀኝ የተራመደ ሲሆን በመጨረሻም 7 እርምጃዎችን ወደ ቀኝ በመራመድ ቀደም ሲል ቆሞበት ወደነበረበት የመጀመሪያቦታው ደረሰ፡፡

በአጠቃላይ የቀይ ምንጣፍ የጥበቃ አጃቢ ዘብ አባላት የአቀባበል ስነስርዓት 59 ሰከንዶችን ወስዷል! የቪዲዮውን ምስልእዚህ ጫን በማድረግ ይመልከቱ፡፡ የቀረው ነገር ቢኖር አሸሸ ገዳሜ እያሉ መጨፈር ብቻ ነው፡፡ በእውነት ሁላችንምወድቀናል፡፡ 

(ሁላቸውም ለመውደቃቸው እና ይህ ጉዳይ እንዴት እውነት እንደሆነ አስረግጦ በድፍረት መናገር ይቻላል!)

Ob 2Pixህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ለአሜሪክ ግብር ከፋይ ህዝብ የሚኪ ማውስየካርቱን ገጸ ባህሪ የያዘውን ተዋናይ ተውኔት የያዘ ዓይነት የቀይ ምንጣፍ በማዘጋጀት ለጉብኝቱ ክብር የሌለው አቀባበልእንዳደረገለት አምናለሁ፡፡ ከዚያ የተሻለ አቀባበል ሊደረግለት ይገባው ነበር፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስበ ለፕሬዚዳንት ኦባማ መንግስታዊ ይፋ ጉብኝት59 ሰከንዶችን የያዘ የቀይ ምንጣፍ የአቀባበል ስነስርዓት ለምን እንዳደረገ የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡

ምናልባትም በዘራፊ ወሮበሎች፣ ሌቦች እና ምስጋና የለሽ ለማኞች መካከል ምን ክብር እና ሞገስ አያስፈለግም ተብሎታስቦ ይሆን?

ወይም ደግሞ ኃይለማርያም እና የእርሱ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) አሻንጉሊት አለቆቹ እንደዚያ ያለውየሚኪ ማውስ የካርቱን ገጸ ባህሪ የያዘውን ተዋናይ ተውኔት የያዘ ዓይነት የቀይ ምንጣፍ የጥበቃ አቀባበል ስነስርዓትለዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ፕሬዚዳንት ይመጥነዋል፣ እናም ይገባዋል በማለት በእርግጠኝነት ያሰቡት የሸፍጥ ስራ ሊሆንይችላልን?

Desalegn Red carpetአሻንጉሊቱ ኃይለማርያም እና የእርሱ  አለቆቹ ከዚህ ቀደም በቂ እና በርካታ የሆኑ እውነተኛ የቀይ ምንጣፍ የእንግዳአቀባበል ስነስርዓት ሂደቶች ምን መምሰል እንዳለባቸው ከሚገባው በላይ እንደሚያውቁ ጥርጣሬ የለኝም፡፡

ኃይለማርያም እና ደመወዝ ከፋይ አለቆቹ የተለየ ክብር የማይሰጠው የአገር ውስጥ ዜጋ እና ብዙ ትምህርት የሌለው የአገርውስጥ ሰው ወይም ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ እንዳለ በአንድ ከተማ ውስጥ እንደሚኖር ተራ ዜጋ ዓይነት ባህሪ በመውሰድእንደዚያ ዓይነት አሳፋሪ እና አስደንጋጭ የሆነ የአቀባበል ስነስርዓት ከማድረግ ይልቅ ከሌሎች ሀገሮች በመመልከትተሞክሮ እና ልምድ መውሰድ አይችሉምን?

ይህንን ስል የተንዛዛ እና ጥልቀት ያለው ትምህርት ማለቴ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህንን ማለት የፈለግሁት ቀላል የሆነትምህርት ጦጣ ሌላውን አይታ እንደምታደርገው ሁሉ ማድረግ ይችሉ ነበር ማለቴ ነው፡፡

እነዚህን ሰዎች ሊያስተምር የሚችል ሰው በአካባቢያቸው የለምን? እባካችሁ እንደዚህ ተማሩ የሚል ሰዉም የላቸው፡

አዳምጡ! የቀይ ምንጣፍ አነጣጠፍ ስነስርዓት ይህንን ይመስላል፡፡ አስተውሉ! ምንጣፉ ቀይ ነው፡፡ ሌላ ምንም ዓይነትቀለም ያልተጨመረበት ነው፡፡ ይህም ማለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ በርካታ ቀለሞች ያልተቀላቀሉበት ቀለምነው፡፡ ልዩ ትኩረት ስጡ! ቀይ ምንጣፍ ማለት በቻይና አገር እየተመረተ የሚሸጠው አርቲፊሻል ባለብዙ ረዣዥም ክርየፐርሻ ምንጣፍ ሌላ ማስመሰያ ምንጣፍ ማለት አይደለም፡፡ ይህንን በሚገባ አረጋግጡ! ይህም ማለት ባለ 50 ሜትር ቀይምንጣፍ እንዴት እንደሚነጠፍ ያመላክታል፡፡ እዚህ ተመልከቱ! ትምህርቱ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል፡፡ 8 ጫማ የመሮጫቡትቶዎችን [ባለረዣዥም ክር ርካሽ የቻይና ቡትቶዎችን] በአንድ ላይ በማያያዝ ወይም ደግሞ በመደረት የዩናይትድስቴትስ አሜሪካንን ፕሬዚዳንት የመቀበል ስነስርዓት ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት ስጡ! ፍጹም በሆነ እናቀና አስተሳሰብን በተላበሰ መልኩ ከሳልቫጅ መደብር ለሚገዙት ዉራጅ ምንጣፍ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንትየአቀባበል ክብር ሲባል 99 ሳንቲም የእንኳን ደህና መጡ ቡትቶ ጨርቅ በማንቸዉም አይነት አትጠቀሙ !!!!!

Obama in Addis Ababa

አረ ጉድ በሉእነዚህ እምነተቢስ ፍጡሮች አንድ ትክክለኛ የሆነ ቀይ ምንጣፍ በማንጠፍ የታላቋን ሀገር መሪ መቀበልካልቻሉ እንዴት በማድረግ እና ምንስ ታምር በመስራት ነው 100 ሚሊዮን ለሚሆን ህዝብ የምጣኔ ሀብት ዕቅድበማውጣት ሀገርን ማሳደግ፣ ማበልጸግ እና ማስተዳደር የሚችሉት!? እዲያው ዕለት በዕለት የጉራ ችርቸራ ባዶፕሮፓጋንዳቸው ለመልቀቅ ካልሆነ በስተቀር፡፡

ከዚህ የበለጠ አስከፊ የሆነው ነገር ደግሞ የማስመሰያውን የፐርሻን ረዣዥም ክር የያዘውን የቡትቶ ምንጣፍ አያይዞ እናአነባብሮ የማንጠፉ ጉዳይ ኦባማን አደናቅፎት በፊቱ በግንባሩ እንዲደፋ ሊያደርገው የሚችል አደገኛ ሁኔታ ነበር፡፡ አምላክበኪነ ጥበቡ ጠበቀው እንጅ፡፡ (የሚስጥር የደህንነት አገልግሎቱ የፕሬዚዳንቱን ደህንነት በመመልከት አዳልጦትከመውደቅ እና ከምንጣፉ ችግሮች መጠበቅ ጋር በተያያዘ መልኩ በአንክሮ መመልከት አልነበረባቸውምን? በርካታ ተራየሆኑ ሰዎች ይህንን አደጋ ተመልክተውታል፡፡)

ለዚህ ጉዳይ ብቸኛው አመክንዮያዊ ማብራሪያ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆች ባራክ ኦባማን ለማሸማቀቅበመፈለጋቸው ምክንያት ነው፡፡ ለባራክ ኦባማ ይህ ለአንተ አይመጥንም ብለው በተዘዋዋሪ ለመንገር ፈልገዋል በሚለውአስተሳሰብ ላይ እምነት አድሮብኛል—…!

በእውነቱ ይህ ድርጊት እኔ ለኦባማ መሪነት ደጋፊ ባልሆንም እንደዚሁም ለእርሱ ያለኝ ክብር የወረደ ቢሆንም እና እርሱየወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ለመከላከል ሲል እውነትን በአፍጢሟ በመድፋት እንደ አቡጀ ሲቀደድ የሰማሁትቢሆንም ይህ ድርጊት ግን እጅግ በጣም እንድበሳጭ አድርጎኛል፡፡

የእኔ ግላዊ አስተሳሰብ ቢሆንም ቅሉ ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆኑ አንጻር መንግስቱንወክሎ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመምጣቱ ሌላውን ነገር ሁሉ ወደ ጎን በመተው አሁንም ቢሆን ከፍተኛ የሆነ ክብርሊሰጠው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ዘራፊ ወሮበሎችን ከጫካው ውስጥ ማስወጣት ትችላለህ፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከወሮበላዘራፊዎች ልታወጣው አትችልም!

እንደዚሁም ሁሉገንዘብ ቢከመር የሰው ልጅ ክብሩን ሊገዛ የማይችል መሆኑ ሀቅ ነው!”

ባራክ ኦባማ የአሜሪካንን መንግስት በመወከል በኢትዮጵያ ላደረገው ይፋ ጉብኝት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላየዘራፊ ቡድን ስብስብ ባደረገው የማስመሰል የአቀባበል አስቂኝ የመድረክ ላይ ትወና እጅግ በጣም አዝኛለሁ!

የቻይና ፐርሻን ርካሽ የቡትቶ ቀይ ምንጣፎችን ለኃይለማርያም ደሳለኝ አንጥፉለት (.. ነሐሴ 212015 ላደረገውየሩዋንዳ ግብኝት) ሆኖም ግን ለኦባማ ጉብኝት ግን የቻይናን የሑዋነግፑን ቀይ ምንጣፍ አንጥፉለት!)

ይህ ነገር እውነት ሊሆን አይችልምን!?

በሁለገብ የፕላስቲክ ክር ምንጣፍ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን ፕሬዚዳንት እንኳን ደህና መጣህ ማለት ጥሩአይሆንምን?!?

(ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና ፕሬዚዳንቱ የተነጠፈው ቡትቶ ምንጣፉ ሳያዳልጠው እና በግንባሩ ሳይደፋ ቀረ፡፡በእርግጥ ፕሬዚዳንቱ የሊመውሲን ተሸከርካሪዋን የኋላ መስታወት አጥብቆ በመያዙ ምክንያት ምንጣፉን በሚረግጥበትጊዜ አዳልጦት ሳይወድቅ ቀርቷል፡፡ ያንን ጉዳይ የደህንነት ሰዎች ይሆኑ ያዘጋጁት?!)

ሆኖም ግን ነገሩ እውነት ነው!

በእርግጠኝነት ትክክለኛው የእንኳን ደህን መጡን ምንጣፍ በገፍ ለመግዛት የሚከተለውን የግንኙነት መስመር በመጠቀምማዘዝ ይቻላል፡

http://www.customized-door-mats.com/sale-329177-red-blue-outside-entrance-polypropyylene-door-mats-with-charming-welcome-printing.html

ዶናልድ ትሩምፕ እንዲህ ብሎ ነበር፣አሜሪካ እንደገና ለመከበር ትፈልጋለች፣ ምክንያቱም ቀሪው የዓለም ክፍልአሜሪካንን ማክበሩን ትቷል፡፡

ዶናልድ ትሩምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢሆን ኖሮ እና ኢትዮጵያን ሲጎበኝ እንደዚህ ያለ ክብርን ዝቅ ያደረገ የሚኪ ማውስአስቂኝ የመድረክ ላይ ትወና ካርቱን ዓይነት የምንጣፍ አነጣጠፍ ስነስርዓት ቢያጋጥመው ኖሮ ምን ያደርግ ነበር?

ለቻይናውያን ከሚነግራቸው ትንሽ ለየት ባለ መልኩ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህበማለት ይነግራቸው ነበር፣አዳምጡ– 25 በመቶ ግብር እንቆርጥባችኋለን!“

እናንተ ህወሀቶች አዳምጡ! እየተሰጣችሁ ያለውን የምትንደላቀቁበትን የመሞላቀቂያ የደህንነት የገንዘብ ቸክ 25 በመቶእንቆርጥባችኋለን፡፡ይል ነበር ትሩምፕ።

አንደዚህ ነበር  ለአሜሪካ ትሩምፕ የምያስመለሰው 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ነሐሴ 25 ቀን 2007 .

Filed in: Amharic