>

የሕሊና ደም (የቀድሞው የኢትኦጵ ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም ኣርኣያ)

ልኡል ኤርትራ ተወልዶ ያደገ፣ የሻዕቢያ አባልና በኋላም የሕወሐት ታጋይ የነበረ ነው። ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በቤተ-መንግስት የአቶ መለስ ዜናዊ ጠባቂ ተደርገው ከተመደቡት አንዱ ነው። ከዚያም የፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ልዩ አጃቢ ሆነ። ከአምስት አመት በፊት ልኡልን ጨምሮ ሶስት ጠባቂዎች ፕ/ት ግርማን አጅበው አሜሪካ መጡ፤ ሶስቱም እዚህ ጥገኝነት ጠይቀው ቀሩ። ሁለቱ አሜሪካ፣ አንዱ አውሮፓ ይኖራሉ።

ልኡል ሲናገር፥ « መለስ ዜናዊ እጅግ ተጠራጣሪ ሰው ነው። ማንንም አያምንም። በአገሪቱ የተፈፀሙ የተናጠልና የጅምላ ግድያዎች ዙሪያ እያንዳንዷ ትእዛዝና ውሳኔ ከመለስ ውጭ የተከናወነች አይደለችም። በሺህ የሚቆጠሩ (እንዳልከው) 2.500 የሕወሐት ታጋይ መኮንኖች በሆለታ ያለቁትና በአንድ ጉድጓድ አፈር እንዲለብሱ የተደረገው በመለስ ውሳኔ ነው። ትእዛዙን ያስፈፀመው ደግሞ ስዬ ነው። (በነገራችን ላይ በ1994ዓ.ም በኢትኦጵ ጋዜጣ ስለ እስር ቤቱ እልቂት በፎቶ የተደገፈ ተከታታይ ዘገባ ይፋ ተደርጐዋል)…ሃየሎም የተገደለው በመለስና ሻዕቢያ በተቀነባበረ ሴራ ነው። በክንፈ ገ/መድህን ግድያ ሁላችንም ተጠያቂ ነን!..ሁላችንም እጃችን አለበት!!» …በሃዘን ስሜት አንገቱን አቀርቅሮ እየወዘወዘ.. ሲቀጥል፥« አሰፋ ማሩ የተባለ ሰው እንዲገደል ትእዛዝ የተላለፈው ከመለስ ነበር። የፈንጂና ቦንቦ ጥቃቶች የሚፈፀሙት በትእዛዝ ነው። እነ ወ/ስላሴ፣ ኢሳያስና ሃይሌ የተባሉ ፍንዳታውን በማቀነባበር ዋነኛ ተዋናዮች ናቸው። ትእዛዙን ከመለስ፣ ስብሃትና ሳሞራ ይቀበላሉ። አየር ሃይል ውስጥ አሁን ድረስ በሚኖሩ የፈንጂ አጥማጅ ባለሙያዎች ድርጊቱ ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል።…በአገሪቱ ስፍር ቁጥር የሌለው የጭካኔ ድርጊት ተፈጽሞዋል። ለእነ መለስ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ሲባል ነው ያ ሁሉ እልቂት ይፈፀም የነበረው።…ሁላችንም ሕሊናችን ይደማል!! እነዚህ ሰዎች ለማንም ኢትዮጵያዊ የሚሆኑ አይደሉም። ሌላው ቀርቶ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ናቸው!..»..በብስጭት ስሜት ተውጦ።…(የልኡል መረጃዎች ሰፊ ናቸው፤ በሌላ ጊዜ እመለስባቸዋለሁ)
ፎቶ- የቀድሞው ታጋይ ልዑል በኣርኣያ ተስፋማሪያም

Filed in: Amharic