>

ጋዜጠኛ ውብሸት ምግብ ከበላ 24 ሰዓት አልፎታል

Wibishet Taye

በላይ ማናየ

ጋዜጠኛ ‪#‎ውብሸት_ታዬ‬ የ14 አመት እስር ተፈርዶበት በዝዋይ ማረሚያ ቤት ይገኛል። ውብሸት ትናንት ግንቦት 20/2008 ዓ.ም የታሰረበት ክፍል ሲፈተሽ ጽሁፍ ተገኝቶብሃል በሚል በቅጣት ጨለማ ቤት እንዳስገቡት ባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃኔ ተስፋየ ገልጻልኛለች። ውብሸት ዛሬም ጨለማ ክፍል እንደታሰረ ነው። ይህን በመቃወም ውብሸት የርሃብ አድማ ማድረጉንና የሄደለትን ምግብ መመለሱን ለማወቅ ችያለሁ። ዛሬ ውብሸትን ለማየት የሄዱ ሰዎች “ማየት አትችሉም” ተብለው ተመልሰዋል። ጋዜጠኛ ውብሸት ምግብ ከበላ 24 ሰዓት አልፎታል።

Filed in: Amharic