>

ትቸው! ረስቸው! [አስፋ ጫቦDallas Texas USA]

“መድረክ ንጉሳዊ ነው እንዴ ?”በሚል አንድ የኔን ስም ጠቅሶ ግርማ ሰይፉ የጻፈው እነሆ:-
Ato Assefa Chaboአቶ አስፋ ጫቦ በቅርቡ ባሳተመው መፅኃፍ ውስጥ የሸዋ ንግስና ከተመለሰ የእኛም መመለስ አለበት የሚል ስላቅ አቅርቦ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር በየነም ቤተሰቦቻቸው በአካባቢው እንዲህ ዓይነት የንግሰና ጥያቄ ከመጠ ከሚጠይቁት ወገን ናቸው ስለሚባል፤ ይህ እስኪመጣ ድረስ መድረክን የንግስና መለማመጃ ያደረጉት መስለኝ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ብዙ ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸውን የአመራር ቦታ ቢቻል ፖለቲካውን ጭምር መተው ለምን ተቸገሩ?
መጀመሪያ ከት-ከት ብዬ ሳቅኩ::ሁለተኛም አንድ ፤”እዚያ መድረስ ክልክል ነው!” ብዬ የሾህ አጠር ያጠርኩበት መንደር አደረሰኝ።ስለዶክተር በየነ ጴጥሮስ ያለው ነው።ፈርቼ ፤አለሳልሼ ፤በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የቆመለትን አላማ፤እኔም ጠንሳሽ መሥራች የሆንኩትን ድርጅት፣የደቡብ ኢትዮጵያሕዝቦች ሕብረት አገር እያየ መቃብር ሲያወርደው ዝም አልኩ። ዝም እንኳን አላልኩም። አገር ሳያውቀው ፀሐይ ሳይሞቀው በ email ብዙ አልኩት። መንፈሱ “አትቅበረን! አትከፋፍለን!አመራጩ መንገድ ይህ ነው!” የሚል ነበር። አሁን በግርማ ምክንያት ለበየነ ጴጥሮስ የላኩለትን መልእክት ሳነበው ገረመኝ። ዛሬየገረመኝ ከ2003 በፊት ጀምሮ የላኩት መልእክት በጣም ብዙ፤ረዣዥምም ነበሩ።ይህ ባይመጣ ኖሮ ለሕይወቴ ታሪክ ያልኩት ነበር።
በየነን ያውኩት በነሐሴ 1983 አፍሪካ አደራሽ “የስላምና ድሞክርሲ ስብስባ” ሳቢያ ሒልተን ሆቴል የስነበትን ስሞን ነበር። ደቡብ ኢትዮጵያወጣቶች ሕዲያን ጨምሮ የፖለቲካ ዝንባሌ የነበራቸው ባብዛኛው እንተዋወቃለን። በየነ ከዚያ ውስጥ አልነበረምና ሳየው ገረመኝና “አንተ ደግሞ ከየት መጣህ?” ያልኩት በውስጤ ነበር። በዚያ ስብሰባ ሳቢያ የደቡብ ህቦች ህብረት ፈጠርን። የ11 ብሔረሰብ ተውካዮች ተፈራረምንበት። የተፈራርምነው በሒልተን ሆቴል አርማ(Letterrhead)ር ባለበት ወረቀት ነበር። አንድ ቅጅ ለሆቴሉ ማነጀር ሰጠሁ። እኔ የለኝምና አስቀምጦት ከሆነ ታሪካዊም ይመስላል። እኔ ሊቀ መነበር ተስፋዬ ሐቢሶ ዋና ጸሐፊ ሆነን ተመረጥን። በየነ ጵጥሮስ በነጋታው ስራውን ጀመረ።
በነጋታው በጥብቅ ፈልግሐለሁ ብሎ ቡና ጋብዞኝ ተስፋዬ ሐቢሶ ላይ ክሱን ይደርድር ጀመረና አቋረጥኩት። በሐዲያና ከምባቶች መካከል ያለውን የአካባቢ አለመግባባት በመጠኑም አውቅ ስልነበረ፤ከሁሉም በላይ ተስፋዬ ሐቢሶን የተሻለ የማውቀውም ስለነበረ ክሱን አልተቅበልኩትም። የሆነ ሆኖ ነገሩን ከተስፋዬ ጋር ሳነሳው “በየነ ዋና ጸሀፊ ለመሆን ስለሚፈልግ ይውስደው!” አለኝና አቃለለኝ።ዋና ጸሐፊም ሆነ።
በሕዳር ወር 1984 ወደ አውሮጳና አሜሪካ ለመጓዝ ሲግጅት ላይ እያለሁ ፒያሳ ቲ- ሩም ምሳ ሊጋብዛኝ እንደሚፍልግ ነገረኝና ተገናኘን። “የምትሔድ ከሆነ ስራውን በተሻለ ለማጠናከር የሊቀመንበርነቱን ስራ በውክልና ስጠኝ” አለኝ።ወረቀት የዞ ነበርና እዚያው ፈርሜ “ እስከምመለስ ድረስ በየነ ጴጥሮስ ሊቀ መንበር ክሆኖ እንዲስራ” ብዬ ጻፍኩለት።ለዚህ ጉዳይ ምሳ መጋበዝ ድረስ መሔዱ ያኔም አሁንም ይገርመኛል። ምሳ የሚያስጋብዝ ትውውቅ የለንምና ነው።

Page 2 of 3

ከዚያም እኔ በህዳር 1984 ከኢትዮጵያ ወጣሁ። መመለሻ ድልድዬን መለስ ዜናዊ ቦደሰውና በዚሁ ቀረሁ። በየነ ጴጥሮስድርጅት ማፈራረሱን፤መከፋፈሉን፤ማኩረፉን ተያያዘው። ይህንን ስራውን የሚቃወም የሚመስለውን፤የሚጠረጥረውን ሰው ያኮርፋል።ይህንን ወዳጃችንን ዶክተር ማራራ ጉዲናና መጠየቅ ነው። አንዴ ኢድሐቅ ለሚባል የኢሕአፓ ስዎች ያሰባሰቡት ድርጅት ሊቀ መንበረነት በየነ ጋር ተወዳድሮ መረራ ሲያሸንፍ ጊዜ አኮረፈው።ሌሎች ስማቸውን ለጊዜው መጥራት የማልፈለገው ሁለት የደቡብ ኢትዮጵያ ድርጅቶች መሪዎች የነበሩም ማኩረፉን ነግረውኛል። ከኔም ጋር ያለው ግንኙነት የኩርፊያ ያክል ነው። ለዚያውም እኔ ተጠንቅቀ ሸሽቼ እንጅ ተቀናቅኜም አላውቅም። የምሸሸው “አስፋ እንዲህ አለኝ !”የሚል ምክንያት ላለመስጠት ነበር።
መጀመሪያ የበተነው የኛን ድርጅት ኦሞቲክን ነበር።ኦሞቲክ ከድርጅቶ በስነ ሥርአት ጉድለት ያሰናበታቸውን ሁለት ሰዎች፤ ፊታውራሪ መኮንን ዶሪንና ደምሴ ጻራና የምክር ቤት አባል አስደራጋቸው። የሚገርመውኮ ፊታውራሪ መኮንን ወያኔ ሁኖ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስቴር ሆኖ የተሾመው ከኦሞቲክ ከተገለለ ማግስት ነበር። ሌላው በጥር ወር 1984ወደ 2,000 የሚጠጋ አዲስ አበባ ኗሪ የጋሞ ጎፋ ሰው” መኮንንና ደምሴ ከሐዲዎች ናቸው !”ብሎ ሰለማዊ ሰልፍ አድርጎ ማንነታቸውን በአደባባይ ገልጧልኮ።
አሁን ዘመኑን በረሳሁት በየነና መኮንን አሜሪካ ይመጡና እኔ የነበርኩበት ቤት ያርፋሉ። ምንም ምንም እንዳልሆነ አድርጌ አስተናገድኳቸው። የመጡት ፕሬዚዳንት ካርተር አትላንታ ባዘጋጁት የሆነ የእርቅ ስበስባ ላይ ለመገኘት ነበር። የትኛውን ድርጅት ወክሎ እንደመጣ እንኳን እኔ በየነም የሚያስታውሰው አይመስለኝም። ሊቀ መንበር የሆነውን ድርጅት ብዛት ማስታውስ የሚችል አይመስለኝም። ዘመኑም ራቅ ብሏል። የማስታወሰው አቶ ተሾመ ገብረ ማርያምም አብሮ መጥቶ ነበር። ቦስተን ሁኖ ለበየነ ስልክ ሲደውል አንድ ሁለቴ አነጋግሪያለሁ። ካርተርንም በስልክ ያነጋገርኩት በዚያ አጋጣሚ ነበር። ብቻ ብዙ አብረው የመጡ ስልክ ይደውሉልታልና ያነጋግራል። እስማለሁም!!በተመሳስይ ጉዳይ ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ መልስድ ሲስጥ እስማዋለሁ:: ይገርመኛል!!
አንድ ጥዋት ሎስ አንገጄሊስ (Los Angeles) በእግራችን ሽረሸር ስናደርግ “በየነ አንተ ከደቡብ ኢትዮጵያ አትመስለኝም!” አልኩት። ከት ከት ብሎ ስቆ ፤ሳቁ( ትርጉሜ ጭምር ገብቶትና በ አድናቆትም እንደታገርኩት ቆጥሮ ጭምር ይመስለኛል)” እንዴት? ለምን?” አለኝ። “ሁለመናህ !”አልኩት። “አባቴ ፖሊስ ነበሩ።ያደኩትም ጋሞ ጎፋ ነው” አለኝ። አንድምታው ተንኮሉን የተማርኩት ከፖሊሱ አባቴ ነው ለማለት መስለኝ።የጨንቻ ሰዎች” የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም!” ሲሉም እሰማነበር።እኔ ከደቡብ ኢትዮጵያ አተመስለኝም ስለው የደቡብ ኢትዮጵያ ሰው ይህ አነባባሮ ጠባይ የለውም ለማለት ነበር።
ከብዙበጥቂቱ፣በየነ የጋሞ ልጆችን አበጣበጠ። የጋሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት የሚባል ነበርና መሪዎችን አልፎ፤ተቀናናቃኝ ፈጠሮ፣ በነዚያ ተቀናቃኞች አመካይነነት ማባላቱን ጀመረው።ይህ መባላት የጋሞ መሠረታዊ ባሕርይም ስለ አልሆነ እንዴት እንደተሳካላት አሁንም ይገርማኛል። በዚህ ምክንያት ያደርኩት email አሁን ሳነበው ታሪካዊ ስነድ ይመስለኛል። አጥጋቢም ሆነ የሚረባ መልስ አልሰጠኝም። የዚህ የemail ጥሩ ነገሩ በየነ አልደረሰኝም ሊል አይችልም።ከደረሰ ደረሰ ፤ካልደርሰ ተቀባይ የለውም ብሎ መልሶ ለላኪው ይልክለታል።
ግርማ ስይፉ ስለንጉስና በዝርያ አልጋ መውረሱን ያነሳው ኃይለ ሥላሴን አስታወሰኝ። 1966 ንጉሱ ጃጅተው ነበር :: ያም ሁኖ ስልጣንዋን የሙጥኝ ብለው ያዟት። ከዚያ በኋላ ደርርግ የሆነው የወታደር ስብስብ ሰላምታ ይሰጥና “እግሌንም እገሌንም ወህኒ ማውረድ እንፈለጋለን!” ሲሉ” ወሰዷቸው!” ነበር። አድሮ”

Page 3 of 3

ልጆችዎንም የልጅ ልጆችዎንም !”ሲሏቸው ውሰድዋቸው ሆነ። በመጨረሻም ራሳቸውን አንዲት እዚች ግቢ በማትባል መኪና አስገብተው ወስዷቸው።”ከስልጣን ሞት ነው የሚለየን!” የማለት ጥሩ ምሳሌ ይመስሉኛል።
በኢትዮጵያ ፓለቲካ ከ1983 ጀምሮ ስማቸው ያልየለተለየ 3 አሉ። በየነ ጴጥሮስ ፤ኃይሉ ሻውል ፤ይቅርታ ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውልና ዶክተር መረራ ጉዲና ናቸው። ኢንጂኔሩ አሁን በተፈጥሮ ግዴታ ገሸሽ ያለ ይመስላል። ማራራስለትላንት ስለዛሬ ሰለነገም ይጽፋል። ይናገራል! በፓለትካዉ ቦታ፤በቀጥታ ም በተዘዋዋራም ስፍራ (Relevance) ያለው ይመስለኛል።ጎበዝ !ያለበለዚያኢትዮጵኮ የወጣቶችአገርኮ ነች!!
በየነ ጴጥሮስ እላይ በጨረፈታ ለማሳየት ለሞከርኩት ስራው መላውን አለም ደጋግሞ ዞሯልኮ! በዚህ 25 አመት ሙሉ የድርጅቶች መሪነቱ ምን ፈየደ? ምንስ ተናገረ? ምንስ ጻፈ ?የሚል ቢኖር ጉዱ ይፈላ ነበር። የሚል ሰው አለመኖሩ የበጀው መስለኝ። እንዳይኖሩ አድርጎ ይሆን?አሁን ግርማን ላከበት? አንዳንዴ ያኔ ከባንክ ገንዘብ ይዞ ጠፍቶ በኋላ የወያኔ አባል ሁኖ የገንዘብም ምክትል ሚንስቴር እንደሆነው ሰውዬ በየነ ጴጥሮስም የወያኔ አባል ይሆን? እላለሁ የኸው ለ25 አመት ያ ሁሉ ሰው ወህኒ ሲወርድ በየነ አለምን ይዞራል።
ዘኃለፈ ስርየት ይባልና ለንስሀ ሞት አብቃኝ !!ተብሎም ይጸለያል

Filed in: Amharic