ዛሬ ቃሊቲ እስር ቤት በግፍ ታስሮ የሚገኘው የአይበሬው ወንድማችን የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አንድዬ ልጅ የናፍቆት እስክንድር የልደት ቀን ነው!! … ለነገሩ ናፍቆትሻም የተወለደው እዚያው ቃሊቲ ውስጥ ነውና ከውልደቱ ጀምሮ ታላቅ ታሪክ ያለው ልጅ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ታላቅ ሰው እንደሚያደርገው ደግሞ እምነቴ ፅኑ ነው! ፀሎቴንም አላቋርጥም!! … ለማንኛውም ናፍቆትሻን መልካም ልደት እንበለው !! ደግሞም የነፃነት ቀን ቀርቧልና በቅርቡ እንደሻማ እየነደደ ለሌላው ብርሃን በመስጠት ላይ ያለው አባቱም ነፃ ወጥቶ፣ መጪው ልደቱን ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በታላቅ ፌሽታና ደስታ እንደምናከብረው ጥርጥር የለኝም!! ናፍቆትሻ በርታልን! ጎብዝልን! እደግልን!
ሞት ለወያኔ! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
መልካም ልደት! ናፍቆት እስክንድር ነጋ
Filed in: Amharic