የደህንነት ኣባላቱ ወንጀሉን ከሰሩ በኋላ በመጡበት መኪና ተሰውረዋል። የደህንነት ሃይሎቹ በፈጠሩት ግርግር ምክንያት የወያኔ መስተዳደር ኣባላት ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ይህ ሁሉ ችግር ሕዝብን ለመወንጀል የተደረገ መሆኑ የኣከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። እስካሁን በኣከባቢው የሞቱ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር ኣልታወቀም።
ላፍቶ፦ ተጨማሪ መረጃ
በአዲስ አበባ አካባቢ በላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቀርሳ ኮቱማ በሚባለዉ አካባቢ በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተነሳዉ ግጭት 17 ፖሊሶች መሞታቸዉን ነዋሪዎቹ ለቢቢኤን ገለጹ።በፖሊሶችና የቀበሌ አመራሮች በአካባቢዉ ያሉትን ቤቶች ለማፍረስ የመብራት ቆጣሪዎችን ለመንቀል ሲሞክሩ በተነሳዉ ግጭት ነዋሪዎቹ የፖሊሶቹን መሳሪያ በመቀማት፣በዱላና በድንጋይ በተከፈተ ጥቃት ነዉ ፖሊሶቹ የሞቱት።
ግጭቱን ተከትሎ የጦር መሳሪያን የታጠቁ የፌዴራል ፖሊሶች ወደ አካባቢዉ በመግባት ነዋሪዉን እየደበደቡ በጭነት መኪና እያፈሱ ወዳልታወቀ ቦታ እየወሰዱ መሆኑን ቢቢኤን ለማወቅ ችሏል። ህጻናትና እናቶች ያለቤት አባወራ ሜዳ ላይ እንደተጣሉና ለአደጋ እንደተጋለጹ ነዋሪዎቹ ያስረዳሉ።ጿሚዎች ማፍጠሪያ ምግብና ቦታ እንደሌላቸዉ ገልጸዋል። እራሳቸዉን ከፌዴራል ፖሊስ ጥቃት ለማዳን የሚሸሹ የቤት አባወራዎች በየጫካዉ ዉስጥ መቀመጣቸዉን፣ ምንገዶች ሁሉ መዘጋታቸዉን ነዋሪዎቹ ለቢቢኤን ገልጸዋል።ከነዋሪዎቹ ለመረዳት እንደተቻለዉ ቢያንስ አንድ የቀበሌ አመራር ሞቷል።