>

በጋዜጠኛ አበራ ወጊ ህልፈት አዝነናል - መልካም ስሙ ግን ከመቃብር በላይ ይኖራል! [በስደት የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር]

RIP- Journalist Abera Wegiበሳዲያጎ ከተማ ነዋሪ የነበረው እና ለረዥም ግዜ በነጻ ፕሬስ ጋዜጠኝነት ያገለገለው፤ጋዜጠኛ አበራ ወጊ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የሰማነው፤ በጥልቅየሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነን ነው። ጋዜጠኛ አበራ ወጊ ዛሬ በእስር ከሚገኘው ከጋዜጠኛ እስክንድርነጋ ጋር አብሮ ሰርቷል። በተለይም ማዕበል በተሰኘው ጋዜጣ ላይ ዋና አዘጋጅ በመሆን ለብዙአመታት አገልግሏል።
 
አቶ አበራ ወጊ የማዕበል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት፤ በበሳል ብዕሩ ወቅታዊየኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ጽፏል። በተለይም በዚሁ የማዕበል ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ፤ኢትዮጵያዊነት የቃል ኪዳን ማተማችን ነውየሚለውን መሪ ቃል ያመነጨው፤ አቶ አበራ ወጊነበር።ከዚሁ የጋዜጠኝነት ስራው ጋር በተያያዘ፤ የታሰረበት እና ለብዙ ስቃይ የተዳረገበት የክስመዝገብ፤ አነጋጋሪ እና አስገራሚ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ በህግ ስም የተስራውን ግፍ ስለሚያሳይ፤በዚህ አጋጣሚ ለመጥቀስ እንወዳለን።  
ወቅቱ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ውስጡን እየተካሄደ የነበረበት ግዜ ነው።እናም ጋዜጠኛ አበራ በድንበር አካባቢ ይደረግ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ በዜና መልክ አቀረበ።ዜናውን ተከትሎበወቅቱ የትግራይ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት፤በትግራይና ኤርትራድንበር፤ እንኳንስ ጦርነት ተነስቶ ክባድ የተኩስ ድምፅ ሊሰማ ቀርቶ፤ የባረቀም ጥይት የለም።ሲሉ፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ደግሞ፤በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ድንበር፤ እንኳንስ ጥይትጅራፍም አልጮኸም።በማለት ፓርላማውን ፈገግ አደረጉት። ተከታዮቻቸውም የጦርነት ሰበርዜና አቅራቢውን፤ ጋዜጠኛ አበራ ወጊንህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጣላት፤ የሃሰት ዜና አቀረብክብለው አሰሩት።
 
ጋዜጠኛ አበራ ወጊ፤ በዚህ ዜና ምክንያት እስር ቤት እያለ፤ ውስጥ ውስጡን ሲደረግየነበረው ጦርነት ተጋግሎ ሊደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ። እንደ ኢትዮጵያ ዘመንአቆጣጠር ግንቦት 4 ቀን፤ 1990 .. በፓርላማ ደረጃ ጦርነቱ ታወጀ። ምንም እንኳን ጦርነቱገሃድ ቢወጣም ለአቶ አበራ ወጊ ግን ምህረት አልተደረገለትም፤ ወይምለካስ ያቀረብከው ዜናእውነት ነበር።ተብሎ ይቅርታ አልተጠየቀም። ጦርነቱ ተፋፍሞ እያለ የጠቅላይ ሚንስትሩመግለጫ እንደ መረጃ ቀርቦም ጭምር፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ 2 ችሎት ዳኛ ሃጎስ ወልዱ፤ በአቶ አበራ ላይ የአንድ አመት ተኩል እስራት ፈረደበት።
 
አቶ አበራ ወጊ ከላይ በተጠቀሰውየኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነትለአንድ አመት ከስድስትወር ከታሰረ በኋላ ሲፈታ፤በሌላ ክስ ይፈለጋልብለው፤ ከእስር ቤቱ ውጪ የማዕከላዊ ምርመራፖሊሶች እየጠበቁት ነበር። ነዚህ ፖሊሶች በማምለጡ ምክንያት፤ ደህንነቶች ጭምር ጋዜጠኛአበራ ወጊን ማደን የጀመሩበት አጋጣሚ ተፈጠረ። በዚህ መሃል ነው የሚወዳት አገሩን፤ ኢትዮጵያንለቅቆ ለመሰደድ የበቃው።
 
ጋዜጠኛ አበራ በሳንዲያጎ ከተማ ነዋሪ በነበረበት ወቅት፤ በሃዘን እና በደስታ ከሌሎችኢትዮጵያውያን አልተለየም። ከኢትዮጵያ ወጥተው በስደት  ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችን ለመርዳትይደረግ በነበረው እንቅስቃሴ፤ ግንባር ቀደም ተባባሪ፤ ለተቸገሩ ደራሽ እና አጽናኝ ወንድማችንነበር። ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ አንድነት ለቆሙ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ልባዊድጋፍ በመስጠት ይታወቃል።
 
በመጨረሻም በህይወት በነበረበት ወቅት በቁጭት ከሚናገራቸው ነገሮች እስር ቤትውስጥ እያለ አስፈላጊ ህክምና ባለማግኘቱ ለተባባሰ የስኳር ህመም መዳረጉን ሁሌም በቁጭትከሚያነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። በኋላ ላይ ህመሙ እየባሰበት ሲመጣ፤ ወደ ሆስፒታልከወሰዱት በኋላ፤ ያልተገባ በሽታ በመርፌ እንደተሰጠው፤ ይህንንም ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በህክምና  ማወቁን በቁጭት ይገልጽልን ነበር።

በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች

Filed in: Amharic