* የህዝቡ ስሜት በየፈርጁ ይገለጻል ፣ ዛሬም ጀግና ሙሽራ አየን !
* ከሪዮ እሰከ ዲሲ፣ ከአማራ እሰከ እስከ ኦሮሚያ የህዝብ ሀቅ !
* እጁን ቆልፎ ” አቅመ ቢሶች ነን ፣ ታስረናል !” ሲል ” አሸሻሪ ነህ ” አትበሉት
* ስማን ” ሰከን በል” ዘማች ፣ አዝማች ወታደሩ ፣ ሰከን ! ! !
” ሰከን በል ” የሚለውን የአርቲስት ይሁኔ በላይን ወኔ ቀስቃሽ ወቅታዊ ዘፈን በሠርጓ ቀን እንዲዘፈን የመረጠችው ሀገር ወዳድ አስገራሚና አስደናቂ ሙሽራ ቪዲዮ የደረሰኝ ከትንናት በስቲያ ነው ፣ መረጃውን ያደረሱኝ ደግሞ እዚህ ሳውዲ የሚገኙ ቤተሰቦቿ ናቸው ። ስመለከተው በስሜት የሸነቆጠኝን የሙሽሪት ልዩ የሀገር ፍቅር መግለጫ የሆነውን የሙሽሪት የሠርግ ቀኗ ምርጫ ” ሰከን በል ” ጣዕመ ዜማ ልዩ መልዕክት የሰማሁት በመሪሩ ሀዘን ሳምንት መካከል ቢሆንም ዜማው ከፈንጠዝያና ዳንኪራ የወጣ መልዕክት አለውና ከሙሽሪት ወኔ ጋር ” ሰከን በል ” ሰከን በል እያልን ስለሚያገባን እናዎጋለን … !
የሙሽሪት ሜሮንን ቪዲዮ እንዳሰራጨው ጠየቄ በሙሽሪት ቤተሰቦች በኩል ሙሉ ፈቃድ ሰጥተውኝም ነበር ። ቢሸፍቱ አልቅሳ ቀኑ ጥቁር የሀዘን ቀን ስለነበር ከማሰራጨት ወኔውን አጣሁት … መረጃው ሲደርሰኝ ሠርጉ በሃገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እንደተከወነ የገለጸችልኝ እህቷን የሙሽሪትን ሙሉ ስሟን ማን ይባላል ስል ጠየቅኳት ፣ መለሰችልኝ ” በስሟ ትገረማለህ ሜሮን መሀመድ ያሲን ትባላለች ፣ ለእኔ የእናቴ ልጅ ናት በአባቷ አፋር ናት ፣ እሷ ግን ክርስቲያን ናት ፣ መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራት ገድማት ቤተክርስቲያን የለም ፣ እንደሚመስለኝ ብቸኛዋ የአፋር ክርስቲያን እሷ ናት ! ” አለችኝ ! ተደመምኩ ፣ አፋሮች ሲነሱ አባት አሊ ሚራህ ትዝ ይሉኛል ፣ ” የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቋታል !” ሲሉም በቦታው ነበርኩ ! አሳይታ … የአፋሯ ሙሽራ ስለ ኢትዮጵያ የሆነችውን ብትሆን እሷ የጀግኖች ዘር መሆኗ ነው አክኩና አሁንም በሰማሁት ታሪክ ተደመምኩ !
ብቸኛዋ የአፋር ክርስትያን ልትሆን የምትችለው ሙሽሪት ሜሮን ዛሬ የወገኗ ነገር አንገብግቧት ” ሰከን በል ” እያለች በሠርጓ አዳራሽ በስሜት ስትውረገረግ ፣ እጆችዋን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ ከነሚዜዎቿ በማንሳትና በማቆላለፍ ከህዝቡ ጋር መሆኗን በልዩው የሠርጓ ቀን በወኔ ተሞልታ ስታሳይ አለቀስኩ … በሚታየው ጥልቅ ስሜቷ ውስጤን ነካችውና ሆዴ እንደ መባባት አለ …
” ሰከን በል ” የሀገር ወዳዱ የታዋቂው ዘፋኝ የይሁኔ በላይ የአዲስ አመት ልዩ ማስታወሻ ቢሆንም ሰከን ባላለው ወታደር ህዝብ እየተጨፈጨፈ ላዘነ ለተቆጨና እንደኔ ቆሽቱ ላረረው ጥሩ ሰሜት መግለጫ ሆኖም ሰንብቷል … ዛሬ በሙሽሪት እጅ በአዳራሹ ገብቷል … ሙሽሪትን ደጋግማ ” ሰከን በል ” ስትል ስማኋት ፣ ከአርቲስት ይሁኔ ድምጽ እኩል ስታዜመው ” ሰከን በል ” ስትል ሰማኋት ፣ ሰከን ማለት ደግሞ ግድ ይላል ! ወታደሩ ሰከን በል ፣ ገዳይ አስገዳይ ጨምላቃው ፖለቲከኛም ሰከን በል ፣ የሚሞተው ወንድምህ ነው ፣ የሚሞተው እህት ናት ፣ እናም ሰከን ማለት ይበጅሃል ፣ ሰከን በል ! ስትል እስክታውን በቁጭት ስታስነካው የፈንጠዝያና ዳንኪራ ስሜት ላለመሆኑ ያሳብቅባታል !
የሰከነ ነገር ጠፍቶ …እዚህም እዚያም ግፍ በዝቶ የማንፈልገውን እንድንደግፍ ፣ እንድንመርጥ እየተገፋን ነው …የምንወዳት ሀገራችን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ መጓዝን በውል ለታዘበ ይህ እውነት የማያንገበግበው ወገኔ የለም ፣ እናም ሙሽሩት ሜሮን አንዷ ናት ፣ የሙሽሪት ሜሮን ሰከን በል ምርጫ ከእነ ሙሉ እንቅስቃሴዋ እየተመለከትኩ በሙሉ ሀገራዊ ወኔ በሀዘን ውስጥ ሆኖም በቁጭት እልህ ጥልቅ ስሜት ተዘፍቆምና በሀዘን ስሜት ውስጥ ገብቶ በእልህ ይነሸጣል …
ይሁኔና ሙሽሪት ” ሰከን በል ” እያሉ ባንድ መድረክ የተጫወቱትን ያህል ሰርጾ ሊገባ የቻለው እንቅስቃሴ መሰረቱ በውስጡ ያለው እውነት ለመሆኑ አልጠራጠርም ። በሙሽሪት የደስታ ቀን በሀገር ስሜት ዋጅታ በነፍሷ አልፎ በፊቷና በመላ አካሏ የሚታየው ቁጭት ብሎም የወገናዊነት ፣ የህዝባዊነት ስሜት እውነት ቁልጭ ብሎ በሙሽሩት ላይም ይታያል ! ያ ብዙዎች ዘንድ በጥቂቶች ላይ ያደረው የወገናዊነት ” ያገባኛል “ስሜት እውነት በእርግጥም በሙሽሪት ይገለጻል ! በሀገረ አሜሪከ በዲሲ ከተማ በታላቁ የሙሽሪት የደስታ ቀን የሠርጓ እለት አብሮበትና ከህዘብ አጋር መሆን ስለእውነት እንዲህ ወኔን ቀስቃሽ ሆኖ ጀግንነት በየፈርጁ እንድናይ ምክንያት የሆነችውን ሜሮን ጀግና የእኛ ሙሽራ ብያታለሁ 🙂
ሙሽሪት ሜሮን ” በሰከን በል ” ልዩ ሀገራዊ ጣዕመ ዜማ ያንጸባረ ቀችው ሀገሬ ተጎዳች በሚል ቁጭትን ” መለያየት አይጠቅምም በማለት ነበር …
” ድር እንኳን ቀጭኑ ድር እንኳን ለስላሳው
ሲያምር ሲተባበር ይበልጣል ካንበሳው ” ይል ዘንድ ይሁኔ በሜሮን ሰርግ አብሮነትና የሀገር ፍቅርን በልዩ መሳጭ ስሜት ተሰብኳል !
” ወታደሩ ሰከን በል
አፈሙዙን ሰከን ዐርገዉ
ቃታዉን እንዳተትስበዉ
ቧዶ እጁን ነው እሚጮኸው
ሠላማዊ ወንድምህ ነዉ ” ተበሎም ወታደሩ “ተረጋጋ ፣ ሰከን በል ” ትበሎ ወታደሩ ምክር ሲለገሰው ” ሰከን ማለት ነው ጀግንነት ” ተብሎ በሰርጉ አዳራሽ በህበረት ተስተጋብቷል ፣ ያውም በልዩው የግሏ የደስታ ቀን … ! ጀግናዋ የኢትዮጵያ ሙሽራ !
ህዝቤን ተውት እንዲል ደጉ አባት … ባለቅኔው አንጎራጓሪ ” ሰከን በል ” ሲል በሰራው ነጠላ ዜማ አዛዥ ፣ ገዳይ ፣ አስገዳይ አዛዦችም እንዲህም ተብለዋል በይሁኔ ማራኪ ጣዕመ ዜማ
” ሰከን በሉ ህዝቤን ተዉት
ድምጹን ስሙት ፣አትግደሉት
መንግስት በአገሩ በህዝብ ላይ አይተኩስ
ዘር አጥያት ይሁን ንጉስ ከማሪዮሰ ” የተባለው በሙሽሪት ሠርግ ላይ ደምቆ ሲሰማ ማስተዋል ፣ በተበደለ ህዝቧ የተጎዳ የሙሽሪትን ስሜት ማየት ያልቻላችሁ ካላችሁ ስሜታችሁን ፈልጉት … እኔ ይህን የሙሽሪትን ሠርግ “ሰከን በል !” ምርጫና ፣ የመልከ መልካሟን እህት ውስጥና ውጫዊ ስሜት ተረድቸው ረክቸበታለሁ !
ሰሚ ቢገኝ ሀገሬው በደስታ በሀዘን ፣ በየተናጠል በህብረት ስሜት ፍላጎቱን ፣ የዲሞክራሲ ጥማት ነጻነቱን እየጠየቀ ነው ፣ ሆዳም ካልሆነው ተትረፍርፎ ከሞላው እስካጣ የነጣው እጁን ወደ ላይ በማንሳት ” አቅመ ቢሶች ነን ፣ ታስረናል !” ብሎ የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ ” አሸሻሪ ነህ ” አትበሉት ! የውስጥ እውነቱ ፣ የተቃውሞ ህብረቱ መገለጫ ምልክት አድርጎታልና እየመረራችሁም ቢሆን ተቀበሉት !
ሙሉ የሙሽሪት ሜሮንን ቪዲዮ እንዳሰራጨው ጠየቄ በሙሽሪት ቤተሰቦች በኩል ሙሉ ፈቃድ ሰጥተውኝም ነበር ። ቢሸፍቱ አልቅሳ ቀኑ ጥቁር የሀዘን ቀን ስለነበር ከማሰራጨት ወኔውን አጣሁት … መረጃው ሲደርሰኝ ሠርጉ በሃገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እንደረከወነ የገለጸችልኝ እህት የሙሽሪትን ስሟን ማን ይባላል ስል ጠየቅኳት ፣ መለሰችልኝ ” በስሟ ትገረማለህ ሜሮን መሀመድ ያሲን ትባላለች ፣ ለእኔ የእናቴ ልጅ ናት በአባቷ አፋር ናት ፣ እሷ ግን ክርስቲያን ናት ፣ መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራት ገድማት ቤተክርስቲያን የለም ፣ እንደሚመስለኝ ብቸኛዋ የአፋር ክርስቲያን እሷ ናት ! ” አለችኝ ! ተደመምኩ ፣ አፋሮች ሲነሱ አባት አሊ ሚራህ ትዝ ይሉኛል ፣ ” የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቋታል !” ሲሉም በቦታው ነበርኩ ! አሳይታ …
ብቸኛዋ የአፋር ክርስትያን ልትሆን የምትችለው ሙሽሪት ሜሮን ዛሬ የወገኗ ነገር አንገብግቧት ” ሰከን በል ” እያለች እጆችዋን ወደ ላይ በማቆላለፍ ከህዝቡ ጋር መሆኗን በልዩው የሠርጓ ቀን በወኔ ተሞልታ አሳይታናለች ፣ እናመሰግናለን !
እናንተም! ሙሽሪትን ስሟት ! ” ሰከን በል ” ትላለች ፣ ሰከን ማለት ደግሞ ግድ ይላል ! ወታደሩ ሰከን በል ፣ ገዳይ አስገዳይ ጨምላቃው ፖለቲከኛም ሰከን በል ፣ የሚሞተው ወንድምህ ነው ፣ የምትሞተቅ እህት ናት ፣ እናም ሰከን ማለት ይበጅሃል ፣ ሰከን በል !
ለጀግናዋ ሙሽራ መልካም ጋብቻ ተመኘሁ !
ሰናይ ቀን !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 24 ቀን 2009 ዓም