>
8:03 pm - Tuesday January 31, 2023

እንደ ሰው ማሰብ ከተቸገሩ፤ እንደ አህያ ለመኖር የሚረዳ ቀላል ምክር

ወይም:-

የሕወሃቶችን ልብ መብላት ዘዴዎች ሀ፣ሁ?

donkey-heavyloadበእውነት የህወሃቶችን ልብ በልቶ ውስጣቸው ለመጎዝጎዝ እንደ መቻል እጅግ የቀለለ ነገር ያለ አይመስለኝም።

1) ልክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ መቀሌ ላይ እንዳለው በየአጋጣሚው ደርግን ለመጣል በተካሄደው ትግል ህወሃት የከፈለው መስዋዕትነት ወደር የለሽ ነው እያሉ ማስተጋባት

2) ትግርኛ ዘፈን ሊዘፈን ከበሮ ድም ሲል፣ ክራር ሲከረከር፣ ማሲንቆ ማፉአጨት ሲጀምር እጅን እያወዛወዙ ለጭፈራ መውጣትና የሆነን ትግሬ ለጭፈራ እየጎተቱ መጋበዝ

3) ትግርኛ የምትችል ከሆነ ከእነሱ ጋር ስትገናኝ በትግርኛ ብቻ ማውራት፣ የማትችል ከሆነም ለመቻል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆንህን በተግባር ማሳየት

4) በሃላፊነትም ሆነ በስራ ልምድና በትምህርት ደረጃ ግልጽ የሆነ ብልጫ ያለህ ቢሆንም የህወሃት ታጋይ ሁሉ ብቁ ነው በሚል ስሜት ከእሱ እውቀትና ልምድ ለመማር ፍቃደኛ መሆንህን በተግባር ማረጋገጥ

5) የሆነ ሁኔታ ሲኖር ፈጥኖ በመድረስ የደስታውም ሆነ የሃዘኑ ተካፋይ ለመሆን አለመቀደም

6) የስራ ባልደረባህን ጀሮ በመጥባት ሪፖርት የማድረግ ዝግጁነትን በተግባር ማሳየት ወዘተ ከመሳሰሉ ተልእኮዎች አንዱን ወይም የተወሰኑትን ወይም ሁሉንም በብቃት መወጣት መቻል ነው።

ከእነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ቢያንስ በአንዱ በሚፈልጉት መንገድ መንቀሳቀስ የቻለ እንደ ታማኝ ሃይል ተቆጥሮ ሁሉም አይነት የእድገት በር ይከፈትለታል፡፡ ከመይ ዝበለ ቅኑዕ ሰባይ መሲሉካ (እንዴት አይነት ቅን ሰው መሰለህ)፣ ታማኝ፣ ታታሪ፣ አመለ ሸጋ፣ ለለዉጥ የተጋ ሰዉ መሰለህ እየተባለ ይወራለታል፡፡

ዘመኑ ኪራይ ሰብሳቢዎች የነገሱበት ነውና ይህንን የሚቀበል ህሊና ያላቸዉ ብልጦች ሁለት እርምጃ ቀድመዉ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ገና ለገና የትግርኛ ከበሮ ድም ሲል እጃቸዉን እያወዛወዙ መድረኩን ይሞሉታል፡፡ የተቀመጠ ተዋቂ ትግሬ ካለም የተቀመጠበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ከእኔ ጋር ጨፍር እያሉ በግብዣ ስም ያጣድፉታል፡፡

በዚህ ረገድ የሚታየውን ሩጫ አሁን ካሉት የኢህዴን ታጋይ ከነበሩ ሁለት ሌ/ጀነራሎች አንደኛው የሚቀለኝ ትግርኛ መናገር ነው ሲል ለአንድ የደቡብ ተወላጅ የተናገረውን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።

ይኸው ትግርኛን የማይሞከረው የደቡብ ተወላጅ ብ/ጀነራል ቢሮ ተጠርቶ የተጠራበት ምክንያት በትግርኛ ይነገረዋል። በመሃል ምን እያልከኝ እንዳለ እኮ አይገባኝም ይለዋል። “ትግርኛ አትችልም እንዴ!? ብሎ በመደነቅ ስሜት ጠይቆት ከላይ የተገለጸውን ምክንያት እንደነገረው ራሱ ብ/ጀነራሉ ነበር ያጫወተኝ።

ወደ ስድስት የሚሆኑ ሜ/ጀነራሎች ያሉ ሲሆን አንዱ ብቻ በትግርኛ መግባባት ሲቸገር የተቀሩት ግን የስራ ቁዋንቁዋቸው ትግርኛ ነው። ብዙ ቁዋንቁዋ መቻል የሚበረታታ የስራ እድልንም የሚያሰፋ መሆኑ እውነት ቢሆንም የሚቻልበት ምክንያት ከርስ ለመሙላት ተብሎ መሆኑ ነው ክፋቱ።

ይህ ሁኔታ ተገልብጦ ኦሮሞች የበላይ ቢሆኑና ጫናቸውም ልክ እንዳሁኑ ቢበረታ እነዚህ ሰዎች ተገልብጠው ኦሮምኛ አስጠኑን እንደማይሉ እርግጠኛ መሆን እንዴት ይቻላል!?

ይህን ሁሉ ያናገረኝ የኢህዴን ነባር ታጋይ የነበረውና አሁን ላይ የብአዴን ስራ አስፈጻሚ አባል የሆነው ከበደ ካሳ (ጣሳ) እና ሃይለማርያም ደሳለኝ መቀሌ ላይ ለትግርኛ ጭፈራ የቀደማቸው ሰው አለመኖሩ ግርምት ፈጥሮብኝ ነው። ሃይሌማ ሽልማትም ጎርፎለታል።

አቤት የሰዉ እሳቤ ያሰኛል! በእዉነት ህወሃቶች ሰዉን ለመጥላትም ሆነ ለመዉደድ መሰረታዊ ከሆነ ጉዳይ አይነሱም፡፡ ሃዘን ላይ ማን ደረሰ? ለቅሶዉ ልባዊ ነበር ወይ? ተሃድሶ ላይ ትግርኛ ዘፈን ሲዘፈን ማን ጨፈረ? አጨፋፈሩ እንዴት ነበር? ከነማን ጋር ሆኖ ጨፈረ? ትግርኛ ቋንቋን ለመቻል ጥረት ያደርጋል ወይ? ትግሬዎች ሲያናግሩት በትግርኛ ያናግራል ወይ? ከመጣበት ድርጅት መሪዎች ጋር ግንኙነት ያደርጋል ወይ? ተገናኝቶስ ያገኘዉን ወሬ አምጥቶ ይነግረናል ወይ? የተነገረዉን ሁሉ እንደወረደ ይቀበላል ወይ? የሰላምታ አሰጣጡ ሞቅ ያለ ነወይ? ወዘተ የሚሉት ዋነኞቹ የታማኝነት መለኪያዎች መሆናቸው እጅግ ያሳዝናል።

ምንጭ:- ከፌስ ቡክ

Filed in: Amharic