>

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ፕሮጀክት ሪፖርት

ehrpየኢትዮጵያ መንግስት ‹የጸረ-ሽብር ግብረ-ኃይል› በሽብር ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል 2008 ዓ.ም ሐምሌ ወር መግቢያ ላይ በጎንደር በነበሩ የወልቃይት አማራ ማንነት ጠያቂ የህዝብ ተወካይ (ኮሚቴ) አባላትን ለማሰር በተደረገ እንቅስቃሴ በሁዋላ በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ህዝባዊ ተቃውሞዎች በተደጋጋሚ መከሰታቸው ይታወሳል፡፡ የህዝባዊ ተቃውሞዎቹም መነሻ ከመስፋፋታቸው በፊት ጎንደር ላይ ብዙ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ትልቅ እና ሰላማዊ ሰልፍም ተካሄዷል፡፡

ከጎንደር በማስከተል በሐምሌ 29/2008 ዓ.ም የተከናወነው የባህር ዳር ሰልፍ ግን በተለየ መልኩ በአሳዝኝ ሁኔታ የተጠናቀቀ ነበር፡፡ ሰልፉ ሲጀምር ሰላማዊ የነበር ቢሆንም ዘግይቶ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ በአንድ ቀን ብቻ ከ50 በላይ የሚገመቱ ንጹሃን መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት አማራ ክልል ከሚገኙት በአጠቃላይ 11 ዞኖች በስድስቱ ዞኖች የጎላ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተደርጎባቸዋል፡፡ እነዚህም ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ባህር ዳር ልዩ ዞን፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ናቸው፡፡ በስድስቱ ዞኖች የሚገኙ አብዛኞቹ የዞንና የወረዳ ከተሞች (አንዳንድ ቦታዎች ላይ ገጠር ቀበሌዎችንም ጨምሮ) መንግስትን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎችንና የቤት ውስጥ አድማዎችን አስተናግደዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና ከተማና የቱሪስት መናሃሪያዋ ጎንደር ላይ የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ ደባርቅ፣ ደብረታቦር፣ መተማ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ወረታ፣ ስማዳ፣ ጋይንት፣ ባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ቲሊሊ፣ ብርሸለቆ፣ ቋሪት፣ ደምበጫ፣ አማኑኤል፣ ደብረ ማርቆስና ሌሎች በርካታ ከተሞችን አዳርሷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አድማሱን እያሰፋ የሄደውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመግታት የኃይል እርምጃ መውሰዱን በተግባር ከማሳየቱም በላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመንግስት ጦር ተቃውሞውን ለመግታት ‹ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስድ› ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ ብርሸለቆ የመሰሉ የጦር ማሰልጠኛዎች ውስጥ ሳይቀር በተለያዩ ቦታዎች ታስረዋል፤ በርካቶች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ባለፉት ወራት በተደረጉት የአማራ ህዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ወቅት ለጊዜው ያሰባሰበው መረጃም ብዙ ዜጎች በመንግስት ኃይሎች እንደተገደሉ ያሳያል፡፡ የሚከተለው ዝርዝር ለጊዜው የተለዩ የሟቾችን ስምና አድራሻ አካትቶ ለማሳያነት የቀረበ ነው፡፡

(*ማስታወሻ፡- መንግስት ህዝባዊ ተቃውሞዎች በበረቱባቸው አካባቢዎች የኢንተርኔትና የስልክ ግንኙነቶችን በሙሉና በከፊል መዝጋቱ በእነዚህ አካባቢዎች ስለተከሰቱ ጉዳዮች መረጃ የማግኘት ስራውን አዳጋች በማድረጉ ይህ ዝርዝር ሁሉንም የመብት ጥሰት የደረሰባቸው ዜጎችን ያሳያል ተብሎ አይጠበቅም፡፡)

የተገደሉ ሰዎች ስም አድራሻ
1. ይሻል ከበደ …………………………………………… ጎንደር
2. ሲሳይ ታከለ …………………………………………… ጎንደር
3. አበበ ገረመው…………………………………………… ባህር ዳር
4. ተፈሪ ባዬ ………………………………………………….ባህር ዳር
5. እድሜዓለም ዘውዱ …………………………………ባህር ዳር
6. አደራጀው ደሳለኝ ……………………………………ባህር ዳር (ዩኒቨርሲቲ)
7. ይበልጣል…………………………………………………ደብረ ታቦር
8. ግዛቸው ከተማ ………………………………………ጎንደር
9. አዳነ አየነው ……………………………………………ጎንደር
10. ማንደፍሮ አስረስ………………………………………ባህር ዳር
11. ቁምላቸው ቃሉ ………………………………………ባህር ዳር
12. አወቀ ጥበቡ ……………………………………………ፍኖተ ሰላም
13. ሲሳይ ከበደ …………………………………………… ጎንደር
14. ሰጠኝ ………………………………………………………ጎንደር (የወልቃይት ተወላጅ)
15. እቴነሽ ሽፈራው ………………………………………ም/ጎጃም፣ ጂጋ
16. እንዳለው መኮነን …………………………………… ጎንድር፣ ጋይንት
17. እሸቴ ………………………………………………………. ባህር ዳር (ቀበሌ 16)
18. ሰለሞን አስቻለ …………………………………………ባህር ዳር
19. ሙሉቀን ተፈራ ……………………………………….ባህር ዳር
20. አደራጀው ኃይሉ ………………………………………ባህር ዳር
21. አስማማው በየነ ………………………………………ባህር ዳር
22. ታዘበው ጫኔ ………………………………………….ባህር ዳር
23. አስራት ካሳሁን ……………………………………….ባህር ዳር
24. የሺዋስ ወርቁ ………………………………………….ባህር ዳር
25. ብርሃን አቡሃይ ……………………………………….ባህር ዳር
26. ሽመልስ ታየ ……………………………………………ባህር ዳር
27. አዛናው ማሙ …………………………………………ባህር ዳር
28. ሲሳይ አማረ ……………………………………………ባህር ዳር
29. ሞላልኝ አታላይ ………………………………………ባህር ዳር
30. መሳፍንት ………………………………………………..ጎንደር፣ እስቴ
31. እንግዳው ዘሩ …………………………………………ባህር ዳር
32. ዝናው ተሰማ ……………………………………………ባህር ዳር
33. ሞገስ ሞላ …………………………………………………ባህር ዳር
34. ሞላልኝ ታደሰ ……………………………………………ባህር ዳር
35. ይታያል ካሴ …………………………………………… ባህር ዳር
36. እሸቴ ብርቁ ………………………………………………ባህር ዳር
37. ሞገስ………………………………………………………….ባህር ዳር
38. ገረመው አበባው ………………………………………ባህር ዳር
39. ማህሌት…….……………………………………………ባህር ዳር
40. ተስፋየ ብርሃኑ ……………………………………………ባህር ዳር
41. ፈንታሁን………………………………………………… ባህር ዳር
42. ሰጠኝ ካሴ ……………………………………………ባህር ዳር
43. ባበይ ግርማ ……………………………………………ባህር ዳር
44. አለበል ዓይናለም ……………………………………………ደብረ ማርቆስ
45. አብዮት ዘሪሁን …………………………………………… ባህር ዳር
46. አበጀ ተዘራ …………………………………………………. ወረታ
47. ደሞዜ ዘለቀ …………………………………………………..ወረታ
48. አለበል ሀይማኖት …………………………………………… ባህር ዳር
49. እስቲበል አስረስ ……………………………………………አዴት
50. ዓይናዲስ ለዓለም ……………………………………………ደብረወርቅ
51. ሽመልስ ወንድሙ ………………………………………………..ቡሬ
52. ታደሰ ዘመኑ ……………………………………………………….አዴት
53. ሀብታሙ ታምራት ……………………………………………ባህር ዳር
54. ይበልጣል እውነቱ ……………………………………………ባ/ዳር፣ ጭስ አባይ
55. ይህነው ሽመልስ ……………………………………………ደብረታቦር
56. በለጠ ካሴ …………………………………………….ደብረታቦር
57. አዳነ እንየው ………………………………………….ጎንደር፣ ቀበሌ 16
58. አለማየሁ ይበልጣል ……………………………………………ዳንግላ
59. ያየህ በላቸው …………………………………………………..ዳንግላ
60. በረከት አለማየሁ ……………………………………………ዳንግላ
61. ተመስገን ………………………………………………………..ዳንግላ
62. ቅዱስ ሀብታሙ …………………………………………… ባህር ዳር
63. ፍስሃ ጥላሁን ……………………………………………ባህር ዳር
64. ሰለሞን ጥበቡ ……………………………………………ቻግኒ
65. እስቲበል አስረስ …………………………………………… አዴት
66. ዘሪሁን ገደብዬ …………………………………………… ጎንደር
67. ሲሳይ ባብል …………………………………………… ጎንደር
68. ባየሁ ጎንደር …………………………………………… ጎንደር
69. በለጡ መሃመድ …………………………………………… አዘዞ፣ ጎንደር
70. እንጀራ ባዬ ……………………………………………… አዘዞ፣ ጎንደር
71. ወንድም ……………………………………………………. ጎንደር
72. ግርማቸው ከተማ …………………………………………… ላይ አርማጭሆ
73. ሊሻን ከበደ …………………………………………………… አይባ
74. መሌ አይምባ ……………………………………………….. አይባ
75. አዛነው ደሴ …………………………………………… አርማጭሆ
76. አራገው መለስ …………………………………………… አርማጭሆ
77. ሰጠኝ አድማሱ …………………………………………… ደልጊ
78. ታረቀኝ ተሾመ …………………………………………… ደልጊ
79. ሄኖክ አታሎ …………………………………………… ደልጊ
80. ደሴ ደረሰ …………………………………………………ሻውራ
81. ግርማቸው ሞገስ …………………………………………… ሻውራ
82. ወርቁ ጠቁሳ ……………………………………………… ሻውራ
83. ማማዬ አንጋው …………………………………………… ዳንሻ
84. ፈንታ አህመድ …………………………………………… ዳንሻ
85. ክንፌ ቸኮል ……………………………………………. በአከር
86. ሲሳይ ታከለ …………………………………………… አርማጭሆ
87. ማዕረግ ብርሃን …………………………………………… ደብረታቦር
88. መምህር ተስፋየ ብርሃን …………………………………………… ደብረታቦር ቀበሌ 01
89. ይበልጣል ደሴ ………………………………………………………… ደብረታቦር ቀበሌ 01
90. አራጋው መለሰ …………………………………………………………አርማጭሆ
91. አዳነ አያሌው ………………………………………………………… አርማጭሆ
92. አያናው ደሴ …………………………………………… …………አርማጭሆ
93. ትርፌ አጣናው ………………………………………………….አርማጭሆ
94. መምህር ብርሃኑ አየለ …………………………………………… ሰሜን ሸዋ፣ ማጀቴ
95. አብራራው አለማየሁ ………………………………………………………….ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
96. ተመስገን ሲሳይ …………………………………………………………. ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
97. ጋሻው ሲራጅ …………………………………………………………. ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
98. ፈንታ ሞገስ …………………………………………………………. ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
99. ታደለ ያየህ ……………………………………………………………..ም/ጎጃም፣ ቡሬ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት በአማራ ክልል የነበረውን አፈና አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ካለው የመረጃ ማሰባሰብ ተግዳሮትና ከፍተኛ አፈና አንጻር ይህ አጭር ሪፓርት ሁሉን የመብት ጥሰቶች አጠቃሎ እንደያዘ ተደርጎ መቆጠር አይኖርበትም፡፡ ፕሮጄክታችን ግድያንና አፈናን በጽኑ በማውገዝ፣አሁንም
በአማራ ህዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች እርምጃ የወሰዱ የመንግስት ኃይሎች ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ እስካሁን በተከናወኑት የተቃውሞ ድምጾች ሳቢያ ስለደረሰው ጉዳት በገለልተኛ ወገን ምርመራ እንዲደረግ፣ እና የኢትዮጵያ መንግስት የመብት ጥያቄ ያነሱ ዜጎችን ከማፈንና ከግድያ ተቆጥቦ ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ለህግ እንዲገዛ፣ ይጠይቃል፡፡

በተቻለ መጠንም ተጨማሪ ጥናቶችን እና መረጃ ማሰባሰቡን ይቀጥላል፡፡ በአማራ ክልል ተቃውሞን እና ተያያዥ ጉዳዮች መረጃዎች ያላችሁ ለማህበረሰብ ሚዲያ ገጾችቻችን እና በኢሜል መረጃ ብታደርሱን ለተጨማሪ መረጃ ማሰባሰብ ስራችን ግብአት ይሆነናል፡

Filed in: Amharic