>

“ዋን ኔሽን አንደር ጋድ” ኬንያ

የኬንያን ምርጫ ቅስቀሳ በቴሌቪዥን እየተከታተልኩ ነው። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ከነዋሪዎች እና ከህጻናት ጋር እየደነሰ እና እየተጫዎተ ‘እኔን ምረጡኝ’ የሚል ቅስቀሳ ያስተላልፋል። ተቃዋሚዎች እና የግል ተወዳዳሪዎች እንዲሁም የፓርላማ አባላት ደግሞ “እኛን ምረጡ” እያሉ  የቅስቀሳ ማስታወቂያቸውን   በቴሌዢዥን እና በራዲዮ እያጧጧፉት ነው። የሲቪል ተቋማት እና ሌሎች ድርጅቶች ደግሞ “ዋን ኔሽን አንደር ጋድ” (ኬንያ በፈጣሪ መዳፍ ላይ ያለች   አንድ ሃገር ናት) ስለዚህ ስትመርጡ ድምጻችሁን “የሞራል ልዕልና ላለው፣የሕዝብን አደራ ለማይረሳ፣ለሰላም የሚተጋን እና ለራሱ ለሚታመን ዕጩ ተወዳዳሪ ድምጻችሁን ስጡ!” እያሉ ይቀሰቅሳሉ። በኬንያ በኦፊሴል የሚታወቁ ከአርባ በላይ ጎሳዎች(ትራይብስ) ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ኦሮሞ እና ሶማሌ ይገኙበታል።

እንግዲህ ልብ በሉ ሁለቱም በኬንያ ጎሳዎች(ትራይብስ) እንጅ ኔሽን(ብሄር) አይደሉም። የሁሉም ጎሳዎች ብሄር ኬንያ ናት። ኔሽን(ብሄር) ማለት አገር ማለት እንጅ ጎሳ ማለት አይደለም። ከኢትዮጵያ በቀር በየትም ዓለም ያለው የብሄር ትርጉም ከኬንያ ጋር ተመሳሳይ ነው። ያም ሆኖ በምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ ይሄን ጎሳ ምረጡ የሚል የኋላቀሮች ቅስቀሳ እና የድንቁርና ፕሮፖጋንዳ እስካሁን አላየሁም። በናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ የየአካባቢው ተወዳዳሪዎች የፓርላማ አባላት እና ሚንስትሮች የምረጡኝ ቅስቀሳ ፖስተሮች እና ባነሮች ከግል እና ከተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር እዚህም እዚያም ተለጥፎ ይታያል። ማስታወቂያውም በተለያዩ ሚዲያዎች ተጧጡፏል።

ኬንያ በአንጻራዊነት በምስራቅ አፍሪካ የሕግ የበላይነት ከሁሉም በተሻለ የሚከበርባት ሃገር ስትሆን የዜጎቿ የነፍስ ወከፍ ገቢም ከምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ነው። and  በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ የሆነው የጆሞ ኬንያታ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ(ኤርፖርት) ሲሆን ከአፍሪካ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ፣ግብጽ፣ሞሮኮ እና ናይጀሪያ ከሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች ቀጥሎ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ትልቅ ኤርፖርት ነው። ወደዚህ ኤርፖርት የሚያመጣው እና ወደ ሞምባሳ የሚወስደውን ዋና ጎዳና የሚያገናኘው የመንገድ ስያሜም “ንጉስ ሃይለስላሴ አቬንዩ” ይባላል።

ከሾሻል ሚዲያ

Filed in: Amharic