>
6:31 pm - Monday May 16, 2022

የሰውን ልጅ የክፋት መጠን ያየንበትና እጅጉን የምናውቀውን ነውረኛውን መለስ ዜናዊን በትንሹ

አቻምየለህ ታምሩ

meles_mexicoየሰውን ልጅ የክፋት ልክ ያየንበት መለስ ዜናዊ ከሞተ 5 አመታት ሞላው፡፡ ያለውን አቅምና ጉልበት ሳይቆጥብ ለክፉ ተግባር ያዋለው፤ የዘረኝነት አክሊል ደፍቶ በመንደር ፍቅር ያበደው፤ በእምነትና በቅን ሀሳብ ተገፍቶ ያለፋቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙበት፤ በትምህርት ተወልደው መልካም የሚሰሩና ለወገናቸው የሚያስቡ ሰዎችን በማጥፋት ክብረወሰን የተቀዳጀው የዘረኛነት፣ የክፍናትና የአድሏዊነት ምድራዊ ምልክት የሆነው የትግራዩ ተጠሪ [የኢትዮጵያ መሪ ወይንም ጠቅላይ ሚንስትር ላለማለት ነው] መለስ ዜናዊ ከሞተ አምስት አመታት ሞላው።

ጨካኙ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ውድቀትና መዋረድ ትልቁ የአፍሪካ የጥፋት መሳሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ነበር። እሱና የጥፋት ግብረ አበሮቹ ከትግራይና ከኤርትራ በረሃዎች ጀምረው ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሁሉ በመወገን አገራችንን በጦር ሜዳ የወጉና ቆርሰው ለመስጠት የተስማሙ፤ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በጎጥ ከፋፍለው ለመበታተን ያቋቋሙት የትግራይ ድርጅት አልበቃቸው ብሎ የራሳቸውን የወያኔን ድርጅታዊ ሕግና ደንብ የሚተገብሩ፣ እነሱ አገር በመዶሻ ሲቀጠቅጡ የሚያዳምቁ፣ አገር በመጋዝ ሲቆርጡ ፈራሚዎችና አጨብጫቢዎች የሆኑ፣ የራሳቸው ቋሚ አላማና መመሪያ ሳይኖራቸው ለስልጣን ያበቃናል ብለው የሚያምኑበትን የወያኔን አላማ ቃላቶቹን ብቻ በመለዋወጥ እየገለበጡ የራሳቸው የፖለቲካ ፕሮግራም በማስመሰል በተለጣፊነት ተጠግተው የሥልጣን ፍርፋሪ የሚቀላውጡ እንደ ብአዴን አይነት ነውረኛ የወያኔ ድርጅቶችንና የሕዝብን የጥፋት ዘመን የሚያራዝሙ ቡድኖችና ግለሰቦችን በስራቸው አደራጅተው ሕዝብን እርስ በእርሱ ለማከሳከስ ያላቸውና አቅምና ጉልበት ሁሉ ሳይቆጥቡ ለዘረፋ፤ በቅሚያና ሕዝብን ለማጋጨት በተግባር ያዋሉ የታሪክም የሕዝብም ጠላቶች የሆኑ የፋሽስት ቁንጮዎች ናቸው።

መለስ ዜናዊን ንጹህ ያደረጉት ያሰለፏቸው የትግራይ ወታደሮች በዛሬው እለት በወያኔ ቴሌቭዝን ቀርበው ስለመለስ ዜናዊ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰቦች፣ ልማታዊ መስመሮችና የባንዶች አለቃ ስለነበረው ጌታቸው «ነበረው» ስላሉት «ያገር ፍቅር» ሲደሰኩሩ ነበር። የሰው ልጅ የክፋት መጠን ምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ያየንበትን መለስ ዜናዊን ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ያለው፣ አልሚና አገር ወዳድ ያደረጉት በትግሬነት ያሰለፏቸው የትግራይ ወታደሮችና በእጁ የነበረው የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። በአለም ላይ ዳኛና ሕግ የለም እንጂ ቢኖር ኖሮ በአለም ላይ አሉ ከሚባሉ «የህዝብ ጠላቶች» እና «አሸባሪዎች» ሁሉ አስቀድመው እጃቸው የኋሊት በመጨኛ የፍጥኝ ታስሮ የአለም ወንጀለኞች ችሎት ፊት ለፍርድ የሚቀርቡት ምድሪቷን በክፋት የበኳላት በሰው አምሳኛ የተፈጠሩት ጨካኞቹ አውሬዎች መለስ ዜናዊና በዙሪያው የተኮለኮሉት የወንጀል ግብረ አበሮቹ ነበሩ።

እኛ የምናውቀው መለስ ዜናዊ የገነባው የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ዛሬ በወያኔ ቴሌቭዥን ቀርበው የተናገሩት ነፍሰ በላ የትግራይ ወታደሮች እንዳሉት ዲሞክራሲን ያሰፈነ ስርዓት ሳይሆን የክፋት፣ የዘረኛነትና የአድሏዊነት አክሊል የደፋ፤ በልቶ በማደር የኑሮ ግዴታ ብቻ የተጠመዱ «ቋንቋ» በቀል አስካሪሶችን አካባቢያዊ ወኪል አድርጎ የፋሽስት ወያኔን የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ የዘረጋና ግማሽ ህይወቱ ወደ ሞት ተለውጦ እውር ድንብሩን እየሄደ ወደ ገደል የሚገባ የእጓለ ማውታዎች አገዛዝ ነው።

ራሳቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ብለው የሚጠሩት ጨካኞቹ የትግራይ ወታደሮች «መልዓክ» አድርገው ለተቀኙለት፤ እኛ ግን የሰይጣን ቁራጭና የሰውን ልጅ የክፋት መጠን ያየንበትና እጅጉን የምናውቀውን ነውረኛውን መለስ ዜናዊን በትንሹ እንዲህ ስንል እንገልጸዋለን…

አገር ባንድ እንዳይቆም ለሃያ ሸንሽኖ፣
ሰው እንዳይተነፍስ አፍ አፉን አፍኖ፤
ሲጀግን ሳናየው ጀግና ነኝ እያለ፣
ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ድሀ እየገደለ፤
የመፍትሔ ቁንጮ አሉት የለው አቻ፣
ሲያስገብር ለኖረ በመሳሪያ ብቻ፤
አራጊ ፈጣሪ ስላረገ ራሱን፣
በዙሪያው ሰብስቦ አሰሱን ገሰሱን፣
ታሪክ ላወደመ፣ ዘመድ ስላጣላ፣ድሀ እያስለቀሰ፣
የወፍ ጎጆ ታህል እልፍኝ አልቀለሰ፣
መሀንዲስ ይሉታል አገር ላፈረሰ፤
የሰላም አባት ነው ይሉታል ሳያፍሩ፣
በደም ተጨማልቆ ከጸጉር እስከ ጥፍሩ፤
ሀውልት ቆመለት እየበላ ህይወት እሱ ለደረጀ፣
በግፍ ክበረ ወሰን ስለተቀዳጀ፤
እመበለት ሚስቱም አለች ሀብት የሌለው መናጢ መንጢኖ፣
ካገሪቷ በላይ እሱ ሀብታም ሆኖ፤
አሉት «ምግብ ሳይቀምስ» ሲደክም የኖረ፣
የህጻናትን ደም በልቶ ለደለበ ገፍፎ ለከበረ፤
ባለራይ ይሉታል ለራሱ ተሰርቶ ያላለቀውን ሰው ሲገዛ በኖረ ፈረንጅ ተንተርሶ፣
ሀያ ሁለት አመት ቁልቁል ስለነዳን በሚገርም ፍጥነት ያገር ውል በጥሶ፤
በግፍ ሲረሽነን ከሰው የበለጠ ይመስለው ነበረ የዘላለም ገዢ ኗሪ እንደነገሰ፣
የፈጣሬ ነገር ዛሬ እሱ ከኛ አንሶ ካጠፋቸው እኩል መቃብር ወረደ ክንዱን ተንተራሰ።

Filed in: Amharic