>

በሮማ ከተማ 1 ሽህ ኢትዮጵያዊን እና ኤርትራዊያን ስደተኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በኃይል ተባረሩ (ኢሳት)

(ኢሳት ዜና ነሃሴ 18 ቀን 2009 ዓም)

Italy police using water cannon and batons clash with Ethiopian and Ertreanበጣልያን ዋና ከተማ ሮማ ውስጥ ተርሚኒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው ከአንድ ሽህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊን እና ኤርትራዊያን ስደተኞች ላለፉት አራት ዓመታት ይኖሩበት ከነበረው ሕንፃ ላይ በግዴታ ምሽት ላይ በኃይል በወታደሮች ተከበው እንዲባረሩ መደረጉን ጉዳተኞቹ ተናግረዋል።
ነፍሰጡር እናቶች፣ ታዳጊ ሕጻናቶችን ጨምሮ ካለምንም ተለዋጭ መኖሪያ ቤት ጎዳና ላይ እንዲጣሉም ተደርገዋል። ከሃያ በላይ እድሜያቸው ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት የሚሞላቸው ሕጻናት ላለፉት አራት ቀናት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ታዳጊ ሕጻናቱ በአንድ መጋዘን ውስጥ ታግተው እንዳይወጡ ተደርገዋል።
ስደተኞች ሌሎች አገሮች እንዲቀበሉን አሻራችንን አንስታችሁልን ወደ ሌሎች አገሮች እንድንሄድ ይፈቀድልን ሲሉ የጣሊያንን መንግስትን ተማጽነዋል። ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ጎዳና ላይ ምጽዋት ተቀባይ መሆናቸው እንዳሳዘናቸው ጉዳተኞቹ አክለው ገልጸዋል።

Filed in: Amharic