>
8:12 pm - Tuesday January 31, 2023

የዶ/ር ታደሰ ብሩ ጉዳይ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው (ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ)

በወንድወሰን ተክሉ

prof-birhanu-nega-esatባለፈው ጥር ወር በለንደን ሂትሮው አየር ማረፊያ በሽብርተኝነት ክስ ተይዘው የነበሩት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ጉዳይ የአግ7 ወይም በእንግሊዝ ያሉ ደጋፊዎቻቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለመብት፣እኩልነት፣ለፍትህና ለነጻነት ለሚያምን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በመሆኑ በዶ/ሩ ላይ የተከፈተውን መሰረተ ቢስ ክስ ተረባርበን ማክሸፍ አለብን ሲሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
የአግ7 ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከ2009 ጀምሮ በስደተኝነት ደረጃ በእንግሊዝ የሚኖሩ ምሁር ሲሆኑ በሰብዓዊ መብት ሞጋችነታቸውና በሀገር ወዳድነታቸው የሚታወቁ ሆነው ሳለ በእንግሊዝ መንግስት በ2000 ዓ.ም በጸደቀው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ አንቀጽ58 ስር ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ክስ ባለፈው ሀምሌ5ቀን 2017 ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ መለቀቃቸው ይታወቃል።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በለንደን ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ባስተላለፉት መልእክት “የኢትዮጵያ ህዝብ ዋነኛ ጠላት በሀገር ቤት ያለው ህወሃትና ግብረ አብሮቹ ብቻ የሚመስላቸው ሰዎች እኛ ቀደም ብለን ስንገልጸው ከነበረው የጠላት ዓይነት ሁኔታን የዶ/ር ታደሰ ብሩ ከርሳሞ ጥሩ ምስክር ነው” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ላለፉት ሃያስድስት ዓመታት የህወሃትን ስርዓት በዲፕሎማሲ፣በሎጀሰቲክስ፣በወታደራዊ ቁሳቁስና በፋይናንስ ተሽክሞ ያለው የእንግሊዝ መንግስት ዛሬ በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ በከፈተው መሰረተ ቢስ ክስ አንዳች ነገር እንዲያደርግ መፍቀድ የለብንም ” ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከአሸባሪዎች ድረ-ገጽ ላይ መረጃ በመሰብሰብ የተከሰሱ ሲሆን የክሱን ይዘት የተከታተለው ዘ-ዴይሊ ሜይል በዘገባው “በዶ/ሩ ላይ የተጠቀሰው የመክሰሻ አንቀጽ እንደነ አይ ሲ ሲ መሳይ አሸባሪ ድርጅቶችና አባላት የሚከሰሱበት ቢሆንም ስኮትላድ ያርድ ግን ዶ/ሩን ለአሸባሪነት የሚያበቃ መረጃዎችን በማሰባሰብ ክስ እንደሚከሳቸው ” ዘግቦ የነበረ ሲሆን አጠቃላዩ የክስ ይዘት ከአግ7 ጋር ያልተያያዘ እንደሆነም ማወቅ ተችላል።
“እኛ የምናካሄደው ትግል በሀገር ቤት ይሁን እንጂ አጠቃላይ የትግሉ አድማስ ውቂያኖስ ተሻግሮም የህወሃት የነፍስ አባት ከሆኑት ምእራባዊያን ጭምር ነው” ያሉት የአግ7 ሊ/ር ፕ/ር ብርሃኑ “ከዚህ በፊት ህወሃት አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ከወሰዱ በሃላ ዛሬ ደግሞ ዶ/ር ታደሰ ብሩን በአሸባሪነት ስም በእጅ አዙር በእንግሊዝ ህግ አስፈጻሚ ህዝብ እንዲያዝም ሆነ እጃቸው እንዲያስገቡት በፍጹም መፍቀድ የለብንም” ሲሉ በለንደን ላሉ ኢትዮጵያዊያን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የእንግሊዝ መንግስት ከምእራባዊያን ሀገራት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የህወሃት መራሹን መንግስት በመደገፍ፣በማደራጀትና ብሎም ድጋፍ በማስተባበር የታወቀ ቢሆንምና ከስርዓቱ ጋር እጅና ጋንት የሆነ ቢሆንም በእንግሊዝ ግብር ከፋይ ህዝብ ቁጥጥር ስር ያለ ነጻና ገለልተኛ የፍትህ ተቃም ስላለ የዶ/ር ታደሰ ብሩን ዓይነት ጉዳዮች በአግባቡ ተማግተን ማሸነፍ ይቻላል ባይ ናቸው ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ።
`የእንግሊዝ ዜግነት ያለውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከህወሃት መራሹ ስርዓት እስር ቤት በማስፈታት ረገድ የእንግሊዝ መንግስት ለአንድ ዜጋው ማድረግ ያለበትን ጥረት እንዳላደረገ የሚተቹ እንግሊዛዊያን ፖለቲከኞችና የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች በርካታ ናቸው።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ በአግ7 ከፍተኛ የአመራር አባልነታቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በህወሃት መራሹ መንግስት ጥርስ የተነከሰባቸውና ብሎም በ2014 በሰላይ የኢ-ኔት አፕ[ፕሮግራም]ኮምፒተራቸው ላይ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን በግዛቱ የተፈጸመውን አህጉር ተቃራጭ ወንጀል የእንግሊዝ መንግስት ድርጊቱን በፈጸመው [Gamma International]የእንግሊዝና ጀርመን ፕሮግራም አምራች ድርጅት ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ እንዳልፈቀደ ተገልጻል።
“ትግሉ በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ነው” ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ጠበቃ በመባል የሚታወቁ አንዳንድ ምእርባዊ ሀገራት ተመልሰው የኢትዮጵያዊያኑን ለመብት፣ለእኩለነት፣ለፍትህና ለዲሞክራሲን ትግል በተጻራሪነት ሲታገሉ እንደሚገኙ በማስገንዘብ የትግሉን ውስብስብነትን ለማሰየት ሞክረዋል።
በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ በለንደን ፖሊስ የተከፈተው የአሸባሪነት ክስ የህወሃት የእጅ አዙር ክስ መሆኑን ያሰመሩበት ፕ/ር ብርሃኑ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያ ከዶ/ር ሃላ ሆኖ መደገፍን አስፈላጊነት በአጽንኦት በመግለጽ መልእክታቸውን ደምድመዋል።

Filed in: Amharic