>
6:40 pm - Sunday July 3, 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ የውርደት ቀን! (በዚህ ቀን ከ25 ዓመት በፊት)

ተፈሪ ደምሴ

1.) በጎጥ በጎሳ የተደራጁ ተንኮለኛ መሰሪ ባንዳዎች፣ ዘረኞች፣ ጠባቦች፣ ሌቦች፣ ዘራፊዎች ወንበዴዎች፣ ፀረ አንድነት ቡድኖች የኢትዮጵያን ህጋዊ መንግስት አፈረሱ!
2.) በዚህ ቀን ኢትዮጵያ ለ 3000 ዘመን የታሏቅነቷ ነፀብራቅ የነበሩትን የምፅዋ፣ አዱሊስ፣ አሰብ ወደቦችዋን በማጣት በአንድ ቀን በር አልባ ሆነች!

3.) በዚህ ቀን ህዝቦች ኢትዮጵያዊነታቸውን ተቀምተው እንደ ሸንጎ ቀበሌ በጎጥ እና በዘር በሀይማኖት ተለያይተው ታጥረው አሳፋሪ የባርነት ቀንበርን ተሸከሙ!
4) በዚህ ቀን 300ሺህ ህዝባዊ አብዮታዊ ሰራዊታችን በምዕራባውያን በአረብ ሀገራት እገዛ በፀረ አንድነት ቡድኖች ቀንደኛ የሀገራችን ጠላቶች እንዲሁም በገዛ ህዝቡ ተመቶ ሜዳ ወድቆ ቀረ!
5) በዚህ ቀን ከሀዲ ባንዳዎች ከጠላት ጋር በመሰለፍ የገዛ ሀገራቸውን ወጉ!
6) በዚህ ቀን ባንዳዎች ኤርትራን አስገነጠሉ ሰፊውን የታላቋን የኢትዮጵያ ህዝብ ወደብ አልባ አደረጉ!
7) በዚህ ቀን ሰፊው ህዝባችን ላይ፦ ስደት፣ ውርደት፣ እስር፣ ግፍ፣ ፣ዘረኝነት፣ መከራ፣ ጠባብነት፣ ሞት፣ ርሀብ፣ እርግማን፣ ድህነት ነገሰ!
8) በዚህ ቀን ህዝባችን በየቦታው ተሰዶ የነጭና የአረብ የማንም ቅራቅንቦ መጫወቻ ሆኖ የአለም መሳቂያ ሆነ!
9) በዚህ ቀን የአንድ ብሄር የበላይነት ብቻ ነግሶ መላ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ ዝርፊያ አፈና ግድያ ዘር ማጥፋት ፈፀመ!
10) በዚህ ቀን በጎጥ በተደራጁ ወንበዴዎች ምክንያት 130ሺ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ባድማ መሬት ላይ እንደ ቅጠል ረገፉ!
11) ጎጠኞች ለዘመናት በአባቶቻችን ደም ተከብሮ የቆየውን ባህር በራችንን ለተራ ወንበዴ መስጠታቸው ሳያንስ የኢትዮጵያን ድንግል መሬት ለአረብ፣ለነጭ፣ በአጠቃላይ ለማንም ሸጠው ሀብታችንን አዘርፍው እንደገና ሌላ ውርደት አከናነቡን!
~ በዚህ ቀን ጎጠኞች፣ ወንበዴዎች፣ ገንጣዮች፣ ሽፍቶች በታላቋ ሀገር የ3000 ዘመናት ታሪክ ባደባባይ ተሳለቁ፣ ሰንደቋን ተራ ጨርቅ ነው ብለው አንጓጠጡ፣ ታላላቅ ነገስታቶችዋን ታሪክ አንቋሸሹ!
~ በዚህ ቀን ኢትዮጵያ በጠንካራ የሀገር ፍቅር ወኔ የተደራጀውን ታሪካዊ ጦርዋን አጣች፣ ባህር ሀይሏም ፈረሰ በጎጥ በተደራጁም እና የዘረኝነት ልክፍት ባለባቸው አላማቸውም ሀገራቸውን መጠበቅ ሳይሆን የሽፍታ አለቃቸውን እና የዘረኝነት ህልማቸውን ለመጠበቅ በሆነ ወራዶች እና የሀገር ፍቅር በሌላቸው ቡድኖች ተተካ

~ በዚህ ቀን የማርና ወተት ምንጭ በነበረችው ታላቋ ኢትዮጵያ ጎጠኞች የዝርፍያ፣ የአፈና፣ የግድያ፣ የሰቆቃ፣ እና የእርዛት እቅዳቸውን ወጠኑ..
ይሄ ቀን የውርደት ነው ምንል ጎጠኝነትን፣ ዘረኝነትን፣ ማፊያነትን፣የስልጣን መባለግን ምንቃወም ሀገራችንን ምንወድ በኢትዮጽያ ታላቅነት ምናምን እነዚያ ለሀገር ፍቅር ደማቸውን ከተቀደሰው የሙሳ (የሙሴ) ባህር የቀላቀሉትን ጀግኖች ምናደንቅ  በዚህ ክፉ ቀን ጥቁር ባንዲራ በማድረግ አንገቷ ለተቆረጠው፣ አብዛኛው ልጆችዋ ከርታታ ለሆኑባት፣ ዜጎችዋ በአስከፊ ጎጠኝነት ለተጎዱባት፣ ጥሪቷ በናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ለተዘረፉባት ለእናታችን አጋርነታችንን እንግለፅ! ክብር_የሀገራችንን_አንድነት_ለማስጠበቅ_ሀገር_ላለማስገንጠልና_ወደብአልባ_እንዳትሆን ከገንጣዮች ከባንዳዎች ከዘረኞች ከፀረአንድነት ቡድኖች ጋር ሲታገሉ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው በአራቱም መዘዝን ወድቀው ለቀሩ ለኢትዮጵያ መለዮ_ለባሽ_ወታደሮች_ለህዝባዊ_አብዮታዊ_ሰራዊታችን  ጀግኖች ሰማዕታት የኢትዮጵያ ልጆች ይሁን!!!

Filed in: Amharic