>
4:39 am - Friday July 1, 2022

በጎንደር ላይ ያነጣጠረው የህዋታዊያኑ ሴራና ጥቃት....[በወንድወሰን ተክሉ]

በጎንደር ላይ ያነጣጠረው የህዋታዊያኑ ሴራና ጥቃት የኢትዮጵያን ህልውናን አፍርሶ የ”ታላቂቱ “ትግራይ ቅዠት መተግበሪያ እምብርት ነው።
` ****
ዓይኖቹ ወደ ጎንደር ይዩ
እግሮች ሁሉ ወደ ጎንደር ያምሩ
እጆች ሁሉ ወደ ጎንደር ይዘርጉ
ልቦች ሁሉ ስለ ጎንደር ያስቡ!!

እኔ ብቻ ሳልሆን ለምን ብዙዎቻችን ከላይ የተደረደሩትን አራት ጥሪዎችን ስለ ጎንደር እንደምናቀርብ የገባውና የተረዳ በርካታ ቢሆንም አሁንም ያላወቀ፣ጉዳቱን እና አደገኝነቱን በጥልቀት ያልተረዳ ወገን ምንድነው ጎንደር ጎንደር እምትሉት?
በኦሮሚያ ከሞያሌ ባብሌ በእየለቱ የሚፈሰው የንጽሃን ኦሮሞ ደም -ከንቱ ነው ውይስ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለ አይደለምን? በሚል ጥያቄ ስለ ጎንደር አጋናችሃል ስሜትን በውስጡ ሊያጎልብት ይችል ይሆናል ብዪ እገምታለሁ።

አዎን -እውነት ነው በምስራቃዊው የኦሮሚያ ግዛት ነዋሪ ወገኖቻችን እንደ የሰሜኑ ኢትዮጵያ አማራ ወገኖቹ በመሬቱ ምክንያት በመንግስታዊ ተቃም ሰልጥኖ፣ታጥቆና ተደራጅቶ ያለው የሱማሌ ክልሉ መንግስታዊ ክንፍ ሃይል ምንም ያልታጠቁትን የኦሮሞ አርሶ አደሮች ከመጋቢት ወር ጀምሮ ከ50በላይ በሆኑ መንደሮች ላይ ይገባኛል ጥያቄ አንስቶ በጉልበት ለመውሰድ ወረራና ግድያን እየፈጸመ እንዳለ እያየን ነው-እየገለጽንም ነው- ህዝባዊ ትብብርና ድጋፍንም እየጠየቅን ነው።

ይህ አርእስት የጎንደር አርእስት በመሆኑ በጎንደር፣በአማራና ብሎም በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልክታን ለማሳየት እንጂ በኦሮሚያ ምድርም ሆነ በጋምቤላም ሆነ በሌሎች ስፍራዎች ምንም እንዳልተፈጠረ በማየት እንዳልሆነ የቅድሚያ ግንዛቤን መጋራት ይኖርብናል።

**ጎንደርን ለምን እናተኩርባት?

የቅማንትን መለያ የለበሰው የሪፈረንደም ድራማ ተጫዋቹ እራሱ ቀማሪና አዘጋጅ የሆነው የህወሃት ሃይል ሲሆን ዓላማውም ተደጋግሞ የተገለጸውንና በወረቀት ላይ ብቻ የነበረውን ዓላሙን መተግበሪያ ጅምሩ በማድረግ ነው።

ለመሆኑ አማራውን ከሱዳን ጋር እንዳይዋሰን ለምን ተፈለገ?

ለመሆኑ ለምንድነው ኢትዮጵያ በአንድ ፓርቲና መንግስት ስር ሆና ከክልል ክልል የሚለያይ ካርታ፣ህገ መንግስትና ስርዓተ ትምህርት ሊኖራት የተገደደችው?

**ለምሳሌ -በትግራይና በቤኒሻንጉል ያሉ ባለስልጣናት፣ትምህርት ቤቶችና ህዝብ ሁለቱ ክልሎች እንደሚዋሰኑ በህገ መንግስታቸው ላይና የክልላቸው ካርታ ላይ አውጥተውናበትምህርት ቤት ደረጃም የሚያስተምሩ ሆነው ሳለ የአማራው ግዛትና የተቀረው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ከዚህ ጋር የተቃረነ ካርታ ይዞ ያለው?

**ለምንድነው-የቅማንት ተወላጆች ሆነው በዚህ ጉዳይ ተሳታፊ አንሆንም የሚሉትን ህዋቶችና ብአዴኖች እያደኑ የሚለቅሙት?
`
ታሪኩ ረዥም-ሴራውም ውስብስብና ክፍታቸውም አስከፊ ቢሆንም ጭምቅና ጥቅልል ስናደርገው-
1ኛ-የህወሃታዊያን በጎንደር ላይ የከፈቱት ማንኛውም ዓይነት ሴራ፣ተንኮልና ጥቃት መነሻው መቀሌ የሆነና መድረሻው “ታላቂታ” ትግራይን የመመስረት ገሀዳዊ እውነታ መሆኑ

2ኛ-በጎንደር እየተካሄደ ያለው የህወሃታዊያኑ ጥቃትና ሴራ በጎንደር ተፈጽሞ እዚያው በጎንደር ደረጃ ወይም በአማራ ህልውና ደረጃ ብቻ የሚቆም ሳይሆን የአጠቃላይ ኢትዮጵያን ህልውናን የሚለውጥና ብሎም የሚፈትን በመሆኑ ጉዳዩ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ መሆኑን እናያለን።

ድርጊቱና ጥቃቱ በጎንደር ላይ ብቻ ወይም በአማራው ላይ ብቻ የሚቀር አይደለም። የሁላችን በሆነችው ሀገራችን ህልውና ላይ መቶ በመቶ በአፍራሽ ሚና የሚነካ በመሆኑ ነው –

በተመሳሳይ መረጃ

ከቤነሻንጉል እስከ ጋምቤላ እንድሁም ወለጋን ግማሽ ለግማሽ ሰንጥቀው የትግራይ ምሁራን ህዝቡን እንድያስተምሩ እና የአካባቢው ህዝብ እንደገና እንዲያወቅሩ [social re-engineering] ህወሓት እንቅስቃሴ ጀመረ።

በህወሓት መስራች አባቶቻቸው የተቀረፀውን የታላቋን ትግርይ ምስረታ እውን ለማድርግ አዲስ እንቅስቃሴ መጀመሩን ምንጮች ገለፁ፡፡ የትግራይ ሪፐብሊክ ይሆናል ተብሉ በተቀረፀው ካርታ መሰረት የምዕራብ ኢትዮጵያት የሱዳን አዋሳኝ ህዝቦችን ዳግም የማዋቀር እንዲጀመር የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለትግራይ ምሁራን በሚስጥር በተደረገ ስብሰባ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የትግሪኛ ቋንቋ ጨምሮ ቁርሾ ፈጣሪ የታሪክ ድርሰቶችም የተካተተበት እቅድ ተቀርፆ በመጠናቀቁ በቀጣይ ወደተግባር ይገባል ተብሏል፡፡ የትግረኛን ቋንቋን ለሚማሩ[ለሚከታተሉት] የአካባቢው ተወላጆች[ተማሪዎች] ሁሉን አቀፍ ከፍተኛ ድጋፍ በቅዲሚያ እንደሚሰጣቸውም ተገልጿል። ይህ ተልኮ የተሰጣቸው የትግራይ ምሁራን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በቦታው የትግራይ ተወላጆች መሰረት ባለው መልኩ እንዲሰፍሩና ተቋማዊ ቅርፅ እንዲኖረው አማድረግ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

በአካባቢው ከተወላጆች በስተቀር ሌላ አዳዲስ መጤ ዝሪያ ዝር ማለት የለበትም ተብሏል። አማራ ወይም ኦሮሞ ነኝ የሚል አከርካርውን በመስበር ከስፍራው ማባረን ይጨምራል እቅዱ፡፡ ይህም የአካባቢው ተወላጆች በፊት በማሰለፍ የትግራይ ምሁራን ከጀርባ ሆነው ያስፈፅሙታል ተብሏል፡፡

በታላቋ ትግራይ ማኔፌስቶ እና ካርታ መሰረት ምዕራብ ጎንደር፣ ቤንሻጉል፣ ጋምቤላና ከፊል ወለጋ መካተታቸው ይተወቃል፡፡

Filed in: Amharic