>

"ሞትህ ዛሬ መሆኑን ብታውቀው መፈጠርህን ትጠላ ነበር።" (ንጉሱ ካሌብ)

ኢትዮጵያ በህወሓት እና ግብረ አበሮቹ ትናንሽ አዕምሮ በመፈራረስ ላይ ያለች ብቸኛዋ አፍሪካዊ አገር ሆናለች። እነዚህ ዘረኞች አገራችንን በጎሳ ከፋፍለው ድንበር ያሉትን ሰርተው፣ የፈለክበት ተንቀሳቅሰህ እንዳትሰራ መታወቂያህ ላይ የጎሳ ስም ለጥፈውልህ በሕይወት አለሁ ካልክ ተሳስተሃል። ወያኔዎች ዙርያህን ምን እየሰሩ እንዳሉ አልታየህም እንጂ መቃብርህን በግሬደር እየቆፈሩልህ፣ ለሞትህ ቀን እየደገሱልህ ነው። ከእነርሱ የጥፋት እሩጫ ይልቅ ያንተ መደንዘዝና ለሞት ቀን ተዘጋጅተህ መቀመጥህ ያስደነግጣል። ከእነርሱ የበቀል ዝግጅትና ፋሽስታዊ እብሪት ይልቅ ያንተ በእራስህና በልጆችህ ላይ እየተደገሰ ያለውን የጎሰኞች ድግስ ከቁሌቱ ትንሽ ለአፍንጫህ እንዴት እንዳልሸተተህ በቁም ያስበረግጋል።
አበው ሲተርቱ ”ውሃ ሲወስድ አሳስቆ” ነው እንዲሉ አባይ ወልዱና ገዱ አንዳርጋቸው አደረግን ያሉት አደገኛ ውል አማራን ለማጥፈት የታለመ የናዚዎች ድራማ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።
በትግራይና ዐማራ ሕዝብ መካከል ልዩነት የተፈጠረው በ1967 ዓ•ም ህወኃት ባወጣው ማኔፈስቶ የዐማራ ሕዝብን ”ጠላት” ነው በሚል ቃል በቃል ያስቀመጠ ህወሓት ኢትዮጵያን በጎሳ ሸንሽኖ የድንበር ውሎች ተደረጉ እያለ ቆይቶ የሚፈነዳ ቦንብ ሲያስቀምጥልህ ተቀምጠህ ለምትመለከት አንተ ትውልድ የመከራ ዘመንህን እያረዘምከው መሆኑን ማወቅ አለብህ።
በዐማራና ትግራይ መካከል ውል ተፈረመ በተባለ በሰዓታት ውስጥ ሁለቱም ክልሎች የመገናኛ ብዙሃን በእየራሳቸው የሚጣረስ ዜና ይዘው ከመውጣታቸው በላይ ሁለቱም ተመሳሳይ ቦታዎች ወደ እኔ ተጠቃለሉ የሚል ዘገባ ይዘው ወጥተዋል። ይህ በእራሱ እንደ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት እና አንድነት ተምሳሌ ለሆነች ሀገር የመጨረሻ የውርደት ደረጃ ነው። ለነገሩ ሀገሪቱ ሳትሆን የውርደት ሸማው በእዚህ ዘመን ላለን ትውልዶች ነው። በገዛ ሀገራችን ድንበር ሲከለል ድንበር አንፈልግም አንለያይም ብለን የጎሰኞችን ድንበር ማፍረስ ያልቻልን ደካሞች! በገዛ ሀገራችን ያልወከልናቸው ጉግ ማንጉጎች ድንበር ተካለልን፣ ተፈራረምን ብለው በሰበር ዜና ሲያሳዩን እናንተ ማን ናችሁ? በስሜ በድንበር ከወንድሜ የዐማራ ሕዝብ ከወንድሜ የትግራይ ሕዝብ ከወንድሜ የኦሮሞና ሱማሌ ሕዝብ እንድታካልሉኝ ስልጣን ቀድሞነገር መቼ ሰጠሁኝ? ብለን የማንጠይቅ ከንቱዎች ነን። እኛ ነን የሞት ሞት የሞትን። እኛ ነን በቁም የተዋረድን። እኛ ነን ምን እያደረጉ እንደሆነ እና ነገ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጅ በልጆቻችን አንገት ላይ እያሰሩ እንደሆነ ያልገባን።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓትና ግብረ አበሮቹን የክልል ማካለልና ኃላፊነት የጎደለው እጅግ የተለጠጠ የጎሳ ፖለቲካ እንክትክቱን ካላወጣና እራሱ በራሱ ተመካክሮ አኗኗሩን ካልወሰነ በኦሮምያና ሱማሌ በጉጄ እና ቦረና ቤንሻንጉል እና ዐማራ እና ሌሎችም ቦታችዎች በማራገብ ብዛት በተቆሰቆሱ የጎሳ ጠቦች ሕዝብ እንዳለቀ ነገ ይሄው ግጭት ወደ ከተሞች ተዛምቶ ኢትዮጵያ ልትወጣው ወደ ማትችለው ማቅ ህወሓት እና አጋሮቹ እንደሚከቷት መረዳት አለብን። እኛ ያልወከልናቸው በስማችን ድንበር ሲከልሉ ቆሞ ማየት ከወንጀሉ ጋር ከመተባበር እኩል ነው። ማን ወከላችሁ? እኛ መቼ ተጣላን? ጥሉም የድንበር ክልሉም ያለው እናንተው አእምሮ ውስጥ ነው አታፋጁን! በአንድ ሀገር ውስጥ ድንበር የለም! ይህ ሃገርን የመክዳት እና የመከፋፈል ከባድ ወንጀል ነው! ብለን ልንቃወም ይገባል።የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት እንደሚኖር የሚያውቀው እራሱ ነው። በመሬት ድንበርተኝነት ገበሬው በሚገጥመው ክርክር ሁሉ እንዴት እንደሚፈታ የእራሱ ብሂል እና ዘይቤ አለው።እነኝህ ጥበቦች ናቸው ለሺህ ዓመታት የኖረች ሀገር ፈጥረው ለአፍሪካ በጭንቅ እና የጨለማ የቅኝ ግዛት ዘመን እረዳት እንድትሆን የረዳት። አሁን ወቅቱ ህወሓት የድንበር ውል አደረኩ እያለ በስማችን ሲነግድ በቴሌቭዥን መስኮት እየተመለከትን ከንፈር የምንመጥበት ሳይሆን አንተ ያሰመርከው የጎሰኞችን ድንበር አንቀበልም። በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ የድንበር አጥር ሊኖር አይገባም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብቱ ሊጠበቅ ይገባል ብለን በፅናት የምንነሳበት ወቅት ነው። ከዚህ በተለየ ግን በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ የድንበር ውል አደረግን ሲሉህ ተቀምጠህ ለምትመለከት ትውልድ – “ሞትህ ዛሬ መሆኑን ብታውቀው መፈጠርህን ትጠላ ነበር።” በመሆኑም የወያኔን ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ የዘመናት ድራማ በቃ ብለን በኢትዮጵያዊ አንድነት እንነሳ።

Filed in: Amharic