>
5:18 pm - Thursday June 15, 2969

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚጀምረው ስንት ሰዓት ላይ ነው? (ዳንኤል ክብረት)

ዓርብ ለቅዳሜ ምሽት፣ጳጉሜን አምስት 2002 ዓ/ም ማታ በኢትየጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ እያየሁነበር፡፡ከአሜሪካ የገባሁት በዚያው ቀን ነበርና ዕንቅልፌ ሊስተካከልልኝ ስላልቻ ለበደንብነ በር የተከታተልኩት፡፡እኩለ ሌሊት ሊደርስ ሲል ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ፡፡

የማከብራቸው አርቲስቶች ወደ መድረኩ ተሰባስበው ወጡና በዚያች ታሪካዊት ቀን ታሪካዊውን ስሕተ ትሠሩት፡፡እኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ሊሆን ሽርፍራፊ ሰኮንዶች ሲቀሩ «አዲሱ ዓመት ሊገባ ስለሆነ እንቁጠር» አሉና ወደ ኋላ አሥር፣ዘጠኝ፣ስምንት፣እያሉ እስከ ዜሮ ቆጠሩ፡፡ከዚያም ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ አዲሱ ዓመት ገባ ብለው ዐወጁ፡፡

«ሊቃውንቱ ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል» ይላሉ፡፡በጥንት ጊዜ አውስትራል ያየገባ አውሮፓዊ አይቷት የማያውቅ አዲስ ፍጡር ያይና የሀገሬውን ነዋሪ «ይህቺ እንስሳ ማን ትባላለች?» ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ያም የሀገሩ ነዋሪ «ካንጋሮ» ብሎ መለሰለት፡፡ያም ሰው «ካንጋሮ» የምትባል እንስሳ አገኘሁ ብሎ ለዓለም ተናገረ፡፡በሀገሬው ቋንቋ ግን «ካንጋሮ» ማለት «አላውቅም» ማለት ነበር፡፡አንድ ሞኝ የተከለውን አምሳ ሊቃውንት አይነቅሉትም እንዲሉ ይሄው ስሟ ሆኖ ቀረ፡፡

ይህ የአዲስ ዓመት መግቢያ ሰዓትም በየሚዲያው እና በየአዳራሹ ብቅጥልቅ እያለ ሰነበተና ስሕተት «ሕግ» ሆኖ በአደባባይ ታወጀ፡፡ለመሆኑ ግን የስሕተቱ መነሻው ምንድን ነው?

የመጀመርያው ቁርጥ ያለ ሕግ ካለመኖሩ የተነሣ ይመስለኛል፡፡በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 51/20 ላይ አንድ ወጥ ካላንደርን ማወጅ የፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን ይገልጻል፡፡ሳላውቀው ታውጆ ካልሆነ በቀር እስካሁን የተወካዮች ምክር ቤት ካላንደርን በተመለከተ ያወጣው ሕግ የለም፡፡ስለዚህም እንደ ዘመነ መሳፍንት «ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ጀመር»፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሚመለከታቸውን ባለሞያዎች በሚመለከታቸው ቦታ ያለማሳተፍ ልማዳችን የፈጠረው ሊሆንም ይችላል፡፡አንድ ሰው እድሉን እና መድረኩን ካገኘ፤ታውቃለህ ከተባለ፤አጋጣሚውም ከተፈጠረለት ሁሉንም ይሆናል፡፡ደራሲም፣አዘጋጅም፣ዳይሬክተርም፣ተዋናይም፣ይሆናል፡ዘፋኝም፣ኮምፖዘርም፣ደራሲም፣የድምፅ ባለሞያም ይሆናል፡፡ይኼ ልማዳችን የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተም በሞያው የደከሙ፣ከልክ በላይ የሠለጠኑ፤ነገሩን ከነምክንያቱ ሊያስረዱ የሚችሉ ሊቃውንት እያሉ ሞያውን የማያውቁት እና ለሞያውም ትኩረት የማይሰጡ አካላት ገቡበትና ሁሉም የየራሱን መንገድ ፈጠረ፡፡

እንደገናም ደግሞ ፈረንጅ ያደረገው ሁሉ ትክክል ነው የሚለው ክፉ ልማዳችንም ለዚህ ሳያጋልጠን አልቀረም፡፡ፈረንጆቹ አዲሱን ዘመናቸውን የሚቀይሩት በእኩለ ሌሊትነው፡፡ያም እንኳ ቢሆን ትክክል ሆኖ አይደለም፡፡የዘመን መለወጫ በሽርፍራፊ ሴኮንዶቹ የተነሣበ የጊዜው ይለዋወጣልና፡፡ነገር ግን በልማድ ሕግ /customary law/ መሠረት በእኩለ ሌሊት ሰዓታቸውን በመጀመራቸው ከሰዓታቸው ጋር እንዲገጥም አድርገው ተጠቀሙበትና በዚያው ጸና፡፡ታድያ እኛም ለመሠልጠን እንደ እነርሱ በእኩለ ሌሊትአዲሱን ዓመት መቀበል አለብን ተብሎ ሳይታሰብ አልቀረም፡፡

ፈረንጆቹ በእኩለ ሌሊት አዲስ ዓመታቸውን ቢቀበሉ እውነታቸውን ነው፡፡ምክንያቱም የእነርሱ የቀን አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት አንድ ሰዓት አልፎ ይጀምርና በእኩለ ሌሊትያልቃል፡፡አዲሱ ዓመታቸውም 00 ብሎ የሚጀምረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ኮፒ በሚጠቅም መንገድ ከተደረገ አንዳንድ ጊዜ መልካም ነው፡፡ነገር ግን ኮፒ ሲደረግ ለገልባጩ እንዲያመቸው አድርጎ ካልሆነ ከመኮረጅ የባሰ ስሕተት ይሠራል፡፡

ትምህርት ቤት እያለን የሚቀለድ አንድቀልድ ነበረ፡፡አንድ ሰነፍ ተማሪ ነበረ ይባላል፡፡ይኼ ተማሪ አራተኛ ክፍል ይደርስና እንዴት እንደሚያደርግ ግራ ይገባዋል፡፡በመጨረሻም በፈተና ሰዓት አነጣጥሮ ተኳሽ መሆን እንደሚያዋጣው ራሱን አሳምኖ ፈተና ክፍል ይገባል፡፡ከዚያም እያነጣጠረ ከጎበዙ ተማሪ መኮረጅ ይጀምራል፡፡አንዲትም ጥያቄ ሳታመልጠው ይኮርጃል፡፡በመጨረሻም ፈተና በሚመለስበት ቀን ግቢው ሁሉ በሳቅ አወካ::ለካስ ያሰነፍ ተማሪ ከጎበዙ ተማሪ ሲኮርጅ ከነ ስሙ እና ከነቁጥሩ ኑሯል የኮረጀው፡፡

የኛም አኮራረጅ የዚህን ሰነፍ ተማሪ ዓይነት ሆነ፡፡ቢያንስ ቢያንስ የአዲስ ዓመት በዓል አከባበራቸውን ወስደን የኛ አዲስ ዓመት በሚከበርበት ሰዓት ብናደርገው ከሰነፉ ተማሪ አኮራረጅ የተሻለ በኮረጅን ነበር፡፡ምናልባትም ደግሞ ነገሮችን በአራቱም አቅጣጫ ካለ ማየት የመጣም ይሆናል፡፡ዕውቀት ማለት ነገሮችን ከአራት አቅጣጫ ማየት መቻል ነው፡: ማንበብ፣መጠየቅ፣መመራመር፣ማነፃፀር፣ማወዳደር፣መተንተን የሚባሉት ነገሮች የሚመጡት ነገሮችን ከአራቱም አቅጣጫዎች ለማየት ሲሞከር ነው፡፡

በእኩለ ሌሊት ተነሥተው አዲስ ዓመት ገብቷል ብለው የሚያውጁ አካላት ሌላው ቀርቶ የእጅ ሰዓታቸውን እንኳን ቢያዩት በታረሙ ነበር፡፡ «ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት» ነበር የሚለው፡፡በዚያ ሰዓት ስድስት ሰዓት ካለ ደግሞ ሌሎች አምስት ሰዓታት ከፊቱ ሄደዋል፤ወይንም ደግሞ ሌሎች ስድስት ሰዓታት ከኋላው ይቀሩታል ማለት ነው፡፡በዚያ ሰዓት ስድስት ሰዓት ከተባለ ደግሞ ያሰዓት ያለፈው ቀን ቅጣይ እንጂ የአዲስ ቀን መጀመርያ አለመሆኑን መረዳት ይገባ ነበር፡፡

አንዳንዶች ይህንን የአዲስ ዓመት ጉዳይ ከገና እና ፋሲካ በዓላት ጋርም ያያይዙታል፡፡በገና እና ፋሲካ በዓላትጊዜ በዓሉ የሚበሰረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ከዚህ አያይዘውም አዲስ ዓመትም በእኩለ ሌሊት ይበሠራል ይላሉ፡፡ገና እና ፋሲካ በእኩለ ሌሊት የሚበሠሩት በበዓላቱ ታሪካዊ ምክንያት የተነሣ እንጂ የበዓሉ ቀን በእኩለ ሌሊት ስለገባ አይደለም፡፡ክርስቶስ የተወለደውም ሆነ ከሙታን የተነሣው በእኩለ ሌሊት ነው ተብሎ በቤተክርስቲያን ስለሚታመን በዓሉ በእኩለ ሌሊት ተከበረ እንጂ ዕለታቱ በስድስት ሰዓት ስለሚገቡ አይደለም፡፡

ታድያ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚብተው ስንት ሰዓት ነው?

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንችል ዘንድ አራት ነገሮችን እናንሣ፡፡የመጀመርያው በኛ አቆጣጠር ዕለት የሚባለው ምንድንነው? የሚለው ነው፡፡ዕለት ሁለት ነገሮችን ይይዛል፡፡ቀን እና ሌሊት፡፡በፈረንጆቹ አቆጣጠር ዕለት የሚባለው ከመንፈቀ ሌሊት እስከ ማለዳ ያለውን ግማሽ ሌሊት፣ከዚያም ከማለዳ እስከ ማታ ያለውን ቀን እና ከማታ እስከ እኩለ ሌሊት ያለውን ግማሽ ሌሊት የያዘው ክፍል ነው፡፡በኛ ግን አንድ ቀን እና አንድ ሌሊትን ብቻ የያዘ አቆጣጠር ነው፡፡

ይህ የሚያመለክተን በመስከረም አንድ ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል የሆነ አንድ ቀን እንጂ በግማሽ ሌሊት እና በሙሉ ቀን የሚቆጠር አይደለም ማለት ነው፡፡ምንም እንኳን በየወራቱ የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት ልዩነት ቢኖረውም ሰዓቱ ግን እኩል አሥራ ሁለት ሰዓት ቀን እና ሌሊት ነው፡፡ለምሳሌ አሜሪካውያን በዓመት ሁለት ጊዜ የሰዓት ማስተካከያ ወደፊት እና ወደኋላ ያደርጋሉ፡፡አውሮፓውያን፣በተለይም ሰሜኖቹ ደግሞ ከአንድ ሰዓት ሌሊት እስከ ሁለት ሰዓት ቀን የሚደርሱበትጊዜ አለ፡፡በኛ ግን የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመትብዙም ልዩነት የለውም፡፡

            ቀኑ                        ሌሊ

መስከረም                                 12 ሰዐት                     12

ጥቅምት                                   11                             13

ኅዳር                                       10                             14

ታኅሣሥ                                     9                              15

ጥር                                         10                             14

 የካቲት                                     11                            13

መጋቢት                                   12                            12

ሚያዝያ                                    13                            11

ግንቦት                                     14                             10

  ሰኔ                                          15                                9

ሐምሌ                                     14                             10

ነሐሴ                                       13                             11

ይሆናሉ፡፡ይህም የሚያሳየን ቀኑም ሆነ ሌሊቱ ከአሥራ አምስት እንደማይረዝም፤ከዘጠኝ እንደማያንስ ነው፡፡እንግዲህ አዲስ ዓመት በመስከረም ወር እንዲብት የተደረገበት አንዱ ምክንያት ቀኑ እ ናሌሊቱ እኩል የሚሆንበትጊዜ ስለሆነም ነው::

ሁለተኛው ነገር ደግሞ የዓመቱን ወራት የምናወጣው በምን አቆጣጠር ነው የሚለው ነው፡፡ቀደም ብለን እንዳየነው የዓመቱን ወራት የምንቆጥረው በፀሐይ አቆጣጠር ነው፡፡በፀሐይ አቆጣጠር ደግሞ መዓልቱ ሌሊቱ ይስበዋል፡፡ምክንያቱም ፀሐይ የሚሠለጥነው በቀንነውና /ዘፍ 1፤14፣16/፡፡ያከሆነ ደግሞ በአቆጣጠራችን ቀኑ ቀድሞ ይጀምራል ማለት ነው፡፡በመሆኑም የኛ አንድ ሰዓት ማለዳ ላይ እንጂ እኩለ ሌሊት ላይ ሊጀምር አይችልም፡፡

ሦስተኛው ደግሞ የሰዓት አቆጣጠራችን ነው፡፡በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር አንድ ብሎ የሚጀምረው መቼ ነው? አዲሱን ዓመት በእኩለ ሌሊት የሚያውጁት ሚዲያዎች እንኳን መልሰው ጠዋት ይነሡና «መስከረም አንድ ቀን ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ነው» ይሉናል፡፡የፈረንጆቹ ሰዓት ግን በዚያ ሰዓት 7 ሰዓት ነው ሚለው፡፡ምክንያቱም እኩለ ሌሊት ላይ አንድ ብሎ ጀምሯልና፡፡አንድ ሰዓት ደግሞ ስድሳ ደቂቃዎች እና 3600 ሰኮንዶች ነው፡፡ስለዚህም አንድ ሰዓት ለማለት እነዚህ ተቆጥረው ማለቅ አለባቸው፡፡እነዚህ መቆጠር የሚጀምሩት ደግሞ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡አሥራ ሁለት ሰዓት የሌሊቱ ማጠናቀቂያ ነውና፡፡

Filed in: Amharic